በተስፋዬ ገብፈአብ
ለማ መገርሳ የኦሮሚያ ኢንቨስተሮችን ሰብስቦ “የጡት አባት አንፈልግም!” ሲል የተናገረውን ከሰማሁ በሁዋላ ስለዚህ ሰው ትኩረት አደረግሁ። ይህ ያልተለመደ ንግግር በቀጥታ ህወሃትን ይነካል። ህወሃት ለኦህዴድ የጡት አባት ሆኖ ኖሯል። ለማ መገርሳ በንግግር ደረጃ በግልጽ ቋንቋ “የህወሃትን የበላይነት፤ የህወሃትን ጌታነት አንፈልግም” ማለት ችሏል። “እንዲህ በል!” ተብሎ የተናገረው አይመስለኝም። ህወሃትን እስከማውቀው ድረስ “ጎረቤቱን” እንዲህ ያለ ቃላት አያለማምድም። የህወሃት የፕሮፓጋንዳ ቃላት የታወቁ ናቸው። ይህ ንግግር የለማ የራሱ አባባል እንደሚሆን ማመን ይቻላል።
“ኦቦ ለማ መገርሳ የኦሮሞ ወጣቶችን ቀልብ እንዲስብ ለጊዜው እንዲህ ያለ ንግግር እንዲናገር ተፈቅዶለታል” የሚሉ አስተያየቶችን አንብቤያለሁ። በደፈናው “ለማ የጌታቸው አሰፋ ተላላኪ ነው። ስለዚህ ከለማ ምንም በጎ ነገር መጠበቅ አይቻልም።” ብሎ መደምደም ይቻል ይሆናል። በተጨማሪ ኦሮሞ ወጣቶች በወያኔ ጥይት ሲደበደቡ ለማ መገርሳ ምንም ማድረግና ምንም ማለት አለመቻሉን አንስቶ መውቀስ ይቻል ይሆናል። Continue reading