የእንጦጦ ቱሪስት ማዕከል ግንባታ ጨረታ ሊወጣ ነው:ፕሮጀክቱ 4.8 ቢሊዮን ብር እንደሚፈጅ ተገምቷል
የዳግማዊ ምኒልክና የአፄ ቴዎድሮስ አደባባይ ሊታደሱ ነው
- ፕሮጀክቱ 4.8 ቢሊዮን ብር እንደሚፈጅ ተገምቷል
- የዳግማዊ ምኒልክና የአፄ ቴዎድሮስ አደባባይ ሊታደሱ ነው
(Ethiopian Reporter) –አዲስ አበባን የቱሪስት ማዕከል ያደርጋታል የተባለው ግዙፍ የሆነው የእንጦጦ ቱሪስት መዳረሻ የንድፍና የግንባታ ሥራ ጨረታ ሊወጣ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማን በዓለም አቀፍ የቱሪስት መዳረሻ ካርታ ውስጥ እንደሚያስገባ የታመነበት በሰሜን አዲስ አበባ በእንጦጦ ጥብቅ ደን ከየካ ዋሻ ሚካኤል እስከ ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በተንሰራፋ 4,200 ሔክታር ተራራማ ቦታ ላይ፣ በ4.8 ቢሊዮን ብር ወጪ በርካታ የመዝናኛ ማዕከላትና የቱሪስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት ለመገንባት ታቅዷል፡፡
የቱሪስት ማዕከሉ በዋናነት የመዝናኛ፣ የዕደ ጥበብ መሥሪያ፣ የመሸጫና ማሠልጠኛ፣ የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የባህል ማዕከልና ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ መንደር ግንባታን አቅፎ የያዘ ነው፡፡ Continue reading