
ትላንት በሚኒሊክና በጎበና በጨለንቆና በኣኖሌ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የተፈጸመው ዘግናኝ ታሪክ ዛሬም በሕወሃትና ኣጫፋሪዎቹ እየተፈጸመ ነው።
በጨለንቆ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የተፈጸመውን እልቂት ኣስመልክቶ የቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ መግለጫ
ፊንፊኔ፡ ኦሮሚያ
“በጨለንቆ ለ2ኛ ዙር ልጆቻቸው ለእልቂት ለተዳረጉባቸው የኦሮሞ ቤተሰቦች እንዲሁም በዚህ ሃዘን ቅስሙ ለተሰበረው የኦሮሞ ህዝብ መጽናናትን እንመኛለን”
ዛሬ በጨለንቆ የተከሰተው ዘግናኝ ወንጀል መላውን የኦሮሞ ህዝብና ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞን ያሳዘነና በ1880ዎቹ ውስጥ በኣኖሌና በጨለንቆ የወቅቱ ንጉስ ሚኒሊክና ጎበና በኦሮሞዎች ላይ የፈጸሙትን የታሪክ ጠባሳ የሚያስታውስ ነው።
በ1880ዎቹ ውስጥ የወቅቱ የኣማራ ንጉስ ሚኒሊክ ከሃዲውን ጎበናን ይዞ በወቅቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ዜጎችን በመግደል፣ በማሰርና በባርነት ወደ ሩቅ ሃገራት በመሸጥ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የፈጸማቸው ፍጅት፥ የኦሮሞን ህዝብ እስከዛሬ ድረስ ለገባበት ወደር የማይገኝለት የጭቆና ቀንበር የዳረገ ነው።
ዛሬም ስልጣን በተፈራረቁት የሃበሻ ገዢ ስርዓቶች በኦሮሞ ህዝብ ላይ ሲፈጸም ከነበረው ጋር በሚመሳሰል መልኩ ወያኔ/ሕወሃት ቅጥረኛ ተላላኪ ድርጅቱ ኦፒዲኦን ይዞ የጨለንቆን ታሪክ ለ2ኛ ጊዜ በመድገም የኦሮሞ ዜጎችን በጅምላ በመፍጀት የዘር-ማጥፋት ወንጀል እየፈጸመ ነው።
ባለፈው ዓመት በሀርሰዴ የኢሬቻ ክብረ-በዓል ላይ በኣንድ ቀን ያለኣንዳች ጥፋት የሕወሃት መንግስት የፈጃቸው ከ700 በላይ ኦሮሞዎች በሃገር ቤትና በውጪ ሃገራት ያለውን መላውን የኦሮሞ ህዝብ ለከፋ ሃዘን የዳረገ መሆኑ ይታወሳል። በዚህ ዓመት 2017 ውስጥም በኦሮሚያ ውስጥ ሲፈጸም የነበረው ፍጅት፣ ረሃብ፣ ሰቆቃ፣ እስራት፣ በኦሮሚያ ሃብት ላይ የሚፈጸመው ዝርፊያ ካሁን በኋላ በኦሮሞ ህዝብ ላይ እንዳይፈጸም የኦሮሚያ ክልል ኣስተዳደርን ቀይረናል በሚል የኦፒዲኦ ኣመራሮች በድጋሚ ቃል ገብተው ነበር። ይህ ሁኔታ ሳይሆን ቀርቶ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚደርሰው ጭቆና ይበልጥ እየከፋ በመሄድ ላይ ይገኛል። በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚፈጸመው እስራት፣ ግድያ፣ ሳይወድ ከትውልድ መሬቱ መፈናቀል፣ መዘረፍና ከሃገሩ መሰደድ ከቀድሞው የላቀ መሆኑ ይታወቃል። ህዝባችን በየዕለቱ ይህ ሁኔታ ከዛሬ ነገ ይቀየራል በሚል ሲጠብቅ በሚዲያ ላይ ወተት ከሰማይ ይዘንብላችኋል ብለው በውሸት ተስፋ ረሃቡን ኣሳድረውት፡ ከኢህኣዴግ/ወያኔ መንግስት ይህን የውሸት የተስፋ ለውጥ እንዲጠብቅ ለማድረግ የስርዓቱ ካድሬዎች፡ ኦፒዲኦ ህዝቡን እያሳሳቱ እንዳሉ ይታወቃል። Continue reading →
Share this:https://www.gofundme.com/8bds2wgk