የወያኔ ኢሕኣዴግ/ሕወሃት መንግስት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ኣውጆ ለማጽደቅ እየስራ ያለውን የጦርነት ኣዋጅ በመቃወም የተሰጠ ኣጭር መግለጫ
የካቲት 20 ቀን 2018ዓም
ኣምባገነኑ የወያኔ መንግስት፡ በኦሮሚያ ብሄራዊ የጭቆና ፍጻሜ ንቅናቄ ትግል ተንኮታኩቶ ከውድቀቱ ኣፋፍ የሚገኘው የኢህኣዴግ ስርዓት በጠመንጃ ኣፈሙዝ እራሱ ከውድቀት ለማትረፍና ሲፈጽም የነበረውንና እየፈጸመ ያለውን የዘር-ማጥፋት (ጄኖሳይ) ወንጀል ይበልጥ ለማስቀጠል በኦሮሞ ህዝብና ባጠቃላይ በሃገሪቷ ህዝቦች ላይ ያወጣውን የጦርነት ኣዋጅ ኣጽድቆ የሃገሪቷን ኣስተዳደር ከስድስት ወራት በላይ ለሚሆን ጊዜ በኮማንድ ፖስት ስር ኣስገብቷል።
ኣሁን ባወጣው የጦርነት ኣዋጅ ቀደም ሲል ለስም ብቻ የነበረውን የሃገሪቷን የኣስተዳደር ስርዓት ባጠቃላይ በወታደራዊ ኣገዛዝ ስር በማስገባት የሰብዓዊና ዲሞክራሲ መብቶችን መርገጡን እንዲሁም የዘር-ፍጅት ወንጀሉን በቀጣይነት ለማካሄድ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል። ይህ የጦርነት ኣዋጅ በህዝባችን ላይ እንዳይጸድቅ ከያለንበት ሁሉ ማውገዝና ኣስፈላጊው ጫና እንዲደረግ ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ ለኦሮሞ ህዝብና ለመላው የሃገሪቷ ህዝቦች ጥሪውን ያስተላልፋል። Continue reading
