እየተፋፋመ  ያለውን የጭቆና ፍጻሜ  ኣመጽ በተመለከተ ከቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ የተሰጠ መግለጫ

Aside

እየተፋፋመ  ያለውን የጭቆና ፍጻሜ  ኣመጽ በተመለከተ ከቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ የተሰጠ መግለጫ

ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ የኦሮሞ ህዝብ ያለበትን ኣጠቃላይ ሁኔታ፡ የወያኔ መንግስት ላለፉት 25 ዓመታት ሲገድሉንና ሲዘርፉን የነበሩትን በኢህኣዴግ ስር የመሰረታቸውን ተላላኪዎች ይዞ ከሁሉም የኦሮሚያ ድንበር ኣቅጣጫ በከፈተው ዘመቻ በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ዘግናኝ እልቂት፡ የተዘረፈውና የወደመው ንብረት፡ በተከፈተው ዘመቻ የተፈናቀሉትን ከ150,000 በላይ የሚሆኑ ወገኖቻችንን ከግምት በማስገባት፥ የኦሮሞ እስረኞች ፍትሓዊ ፍርድ ተነፍገው ለዓመታት በወህኒ ውስጥ መገደልና ለሰቆቃ መዳረግ በመቀጠሉ፥ ባጠቃላይ እነዚህና ሌሎችንም የኦሮሞ ህዝብ በሕወሃት/ኢህኣዴግ ኣስተዳደር ስር እያጋጠመው ያሉትን ኣስከፊ ሁኔታዎችን ለመቃወና ለህዝባችንና ለኣለም ለማሳወቅ እንዲሁም የመብት ጥያቄ ለማቅረብ ጥቅምት 11 ቀን 2017ዓም(ጥቅምት 1 ቀን 2010ዓም) ሰላማዊ ሰልፍ መጥራታችን ይታወሳል።

ይህ ሰላማዊ ሰልፍ ከተጠራበት ቀን(ጥቅምት 11, 2017ዓም) ኣንስቶ ከትላልቅ እስከ ትናንሽ የኦሮሚያ ከተሞች፡ በመላው ኦሮሚያ የሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ሳይቀር የኦሮሞ ህዝብ በነቂስ በኣንድነት ተነስቶ፡ ለጥሪው ምላሽ በመስጠት የሃገር ባለቤትነት መብት ጥያቄና የሉዓላዊነት ትግሉን ለመንግስትና ለዓለም በቀጣይነት ኣሰምቷል። ይህም በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይበጨቋኙ ስርዓት ላይ የተገኘ ከፍተኛ ድል መሆኑን ለሁሉም መግለጽ እንወዳለን። ለኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ትግል መስዋዕትነት በመክፈል ላይ ያላችሁትና ሰፊው ህዝባችን ይህን ከፍተኛ ድል በመጎናጸፋችን የተሰማንን ደስታ እንገልጻለን፣ ህዝባችን እየፈጸመ ባለው ጀግንነት ኩራት እንደሚሰማንም እንገልጻለን። Continue reading