“ኦነግ ኦሮሞ ነው። እናንተም ኦሮሞ ከሆናችሁ ለምን አንድ አት ሆኑም? እናንተ አንድ ብትሆኑ ልጆቻችን አይታሰሩም፣ አይገረፉም፣ አይሰቀ ሉም፣ የደረሱበት እየጠፋ ሃዘን አንቀመጥም፣ ኦሮሞ እስከመቼ ይታሰራል?

Aside

Roba PawelosRoobaa  Pawelos   “የኦሮሞ እንግዴ ልጅ” በሚል ስያሜ የሚጠራው ኦህዴድ በ1997 መስቀለኛ ጥያቄ ቀርቦለት ነበር። ጥያቄውን ያቀረቡት አንድ በዕድሜ ጠና ያሉ አዛውንት ነበሩ። ጥያቄው የቀረበው አዳማ /ናዝሬት/ ቀበሌ 11 አዳራሽ ውስጥ ነበር። ተጠያቂው የወቅቱ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ሳዶ ሲሆኑ ስብሰባው የተጠራው “ለምን አልመረጣችሁንም” በሚል ኦህዴድ ከህዝብ ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት ታስቦ ነበር.

በለገጣፎ ገሃነምና ገነት አየሁ!

“በኔ ዘመን የኦሮሞ ልጆች እንዳይታሰሩ አድርጌያለሁ” ጁነዲን kkkkkkkkkkkkkkkkkkk qsqsqs
legetafo 7

“የኦሮሞ እንግዴ ልጅ” በሚል ስያሜ የሚጠራው ኦህዴድ በ1997 መስቀለኛ ጥያቄ ቀርቦለት ነበር። ጥያቄውን ያቀረቡት አንድ በዕድሜ ጠና ያሉ አዛውንት ነበሩ። ጥያቄው የቀረበው አዳማ /ናዝሬት/ ቀበሌ 11 አዳራሽ ውስጥ ነበር። ተጠያቂው የወቅቱ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ሳዶ ሲሆኑ ስብሰባው የተጠራው “ለምን አልመረጣችሁንም” በሚል ኦህዴድ ከህዝብ ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት ታስቦ ነበር።
“ኦነግ ኦሮሞ ነው። እናንተም ኦሮሞ ከሆናችሁ ለምን አንድ አትሆኑም? እናንተ አንድ ብትሆኑ ልጆቻችን አይታሰሩም፣ አይገረፉም፣ አይሰቀሉም፣ የደረሱበት እየጠፋ ሃዘን አንቀመጥም፣ ኦሮሞ እስከመቼ ይታሰራል?” የሚል ጥያቄ ያቀረቡት አባት ንግግራቸውን መጨረስ አልቻሉም ቤቱ በጭብጨባ ተናወጠ።
“በኔ ዘመን የኦሮሞ ልጆች እንዳይታሰሩ አድርጌያለሁ። በድሬዳዋና በቦረና በኩል የገቡትን ኦነጎች ድጎማ በመስጠት አርሰው እንዲበሉ አድርጌያለሁ። አሁን የምትናገሩትን በሙሉ አላውቅም” የሚል መልስ ሲሰጡ ቤቱን ሁከት ሞላው። ስም እየጠቀሱ የታሰሩ፣ የተሰወሩና የተገደሉትን ተሰብሳቢዎቹ በየተራ ተናገሩ። “በሌሊት የማናውቃቸው ሰዎች በራሳችን ወንድሞች እየተመሩ ይበረብሩናል። አሁን እናንተ ለኦሮሞ ትቆረቆራላችሁ?” ጥያቄው ዘነበ። እንደፈለጉ እንዲናገሩ ክፍት በሆነው መድረክ ሙስናም ተነሳ። የአርሶ አደሩ መሬት መቸብቸቡ ተጋለጠ። ለሶላት አንሄድም በማለት አዳራሽ ውስጥ ጸሎታቸውን አድርሰው ጁነዲንን ሞገቱ። ሰሞኑን ይፋ የሆነውን ግምገማና ውሳኔ አስመልክቶ የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢዎች ያነጋገሩዋቸው ወደኋላ ተመልሰው ያነሱት አስተያየት ነበር። “መሬታችሁ አይነካም። ፊንፊኔ መቼም ቢሆን የኛ ናት። ነፍጠኛ የጫነ ሌጣ ፈረስ አትመልከቱ። ሌጣ ሌጣ ነው” ያሉት አቶ ጁነዲን ቀጣዩ እጣቸው ምን ይሆን?
አቶ ጁነዲን ብቻ ሳይሆኑ በርካታ የኦህዴድ አመራሮች መራገፋቸው እንደማይቀር የሚገልጹት አስተያየት ሰጪዎች የኦህዴድ ካድሬዎችና አመራሮች በወገኖቻቸው ላይ እየፈጸሙ ያለው ወንጀል ባዕድ ከሚፈጽመው በላይ እንደሆነ ይናገራሉ። ስርዓቱ ተጠቅሞባቸው እንደሚጥላቸው እያወቁ ስለምን ወገናቸው ላይ እንዲህ አይነት አስከፊ የተላላኪነት ተግባር ይፈጽማሉ ሲሉ ይጠይቃሉ።
ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀ ወጣት የለገጣፎ ነዋሪ አንድ አብይ ማስረጃ ላሳይህ ሲል የጎልጉልን ሪፖርተር እየመራ ወደ ካንትሪ ክለብ ግቢ ወሰደው። ካንትሪ ክለብ በግፍ፣ በሚገርም ክፍያ፣ ያለ በቂ ዝግጅት ከአርሶ አደሩ ላይ የተነጠቀ ሰፊ መሬት ነው።
የካንትሪ ክለብ ዴቨሎፐርስ (COUNTRY CLUB DEVELOPERS P.L.C. – CCD) ድረገጽ እንደሚመሰክረው ሥፍራው ከ160 ሄክታር ወይም 16 ሚሊዮን ካሬ ሜትር አካሎ ይዟል። እያንዳንዱ ቪላ 1000 ካሬ ሜትር ይዞታ ሲኖረው፣ ከ282 እስከ 513 ካሬ ስፋት ባለው ቦታ ላይ ቪላዎቹ ተኝተው ይታያሉ።
ዋናውን መግቢያ እንዳለፉ ኢትዮጵያ ለገጣፎ ውስጥ ስለመገኘትዎ ማረጋገጫ የለዎትም። ቪላዎቹ ከመሬት ብዙም ከፍ ሳይሉ ተንጣለው ሲያዩዋቸው የተሽኮረመሙ ይመስላሉ። እየቀረቡ ሲሄዱ የቤቶቹ ድርድርና አሰራር ያስገርማል። ብዙ ሪል ስቴቶች ቢኖሩም እንደ ካንትሪ ክለብ ያለ አለ ማለት አይቻልም። ፎቅና ምድር ሆነው የተሰሩት ህንጻዎች የሲሚንቶና የድንጋይ ክምር አይመስሉም። መሬቱ የተዋበት ጡብ፣ በየመንገዱ ያሉት መብራቶች፣ የመዳመቂያ እጽዋቶቹ፣ ሳርና የተመረጠ አበባ የለበሰው መስክ ቀልብ ይሰልባል። ያለማገነን በለገጣፎ ገሃነምና ገነትን አይቻለሁ። አገርቤት መሆንዎን የሚያውቁት ባሬላ ተሸክመው ከወዲያ ወዲህ የሚሉትን “ምስኪኖች” ሲመለከቱ ነው።
ወጣቱ በቀስታ እያመለከተ እነዚህ ሁሉ የምታያቸው የቀን ሰራተኞች አብዛኞቹ የመሬቱ ባለቤቶች ነበሩ። አባት፣ እናት፣ ልጅ ቤተሰቦች ንብረታቸው ላይ ተፈርዶባቸው የቀን ሰራተኛ ሆነዋል። ለንብረታቸው የተከፈላቸው ካሳ ተመጣጣኝ ቢሆን ኖሮ እዚህ ጭቃ አያቦኩም ነበር። ወጣቱ አለቀሰ። ቤቶቹ የሚሸጡት ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ ነው። እንግዲህ አንድ አባወራ አራት ጥማድ መሬት ከተወሰደበት አራት ቪላ ይሰራበታል ማለት ነው። በአምስት ሚሊዮን ብር ሂሳብ ከሃያ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ግብይት ባንድ አባወራ መሬት ላይ ተፈጽሟል። እንደ ወጣቱ ገለጻ አራት ሄክታር የተወሰደበት አባወራ 120ሺህ የማይሞላ ብር ወስዶ ከጨዋታ ውጪ ይሆናል። እናም ኩሊ ለመሆን ይገደዳል። ይህንን ወንጀል ህዝባቸው ላይ የሚፈጽሙትና “ለምን” ብሎ ሲጠይቅ አስረው የሚገርፉት ኦሮሞዎች ናቸው። እንዲህ ያለው ግፍ የት አገር ተፈጽሟል?
ሶስት ወጣቶች ሆነው ሮፓክ ሪል ስቴት ግቢ ውስጥ ገቡ። ሮፓክ “ያለ እረፍት ለአገርና ለህዝብ ሲባትቱ ኖረው ተሰው የሚባሉት ሟቹ ጠ/ሚኒስትር” ወንድም ንብረት እንደሆነ ከወሬ በላይ ነው። ወጣቶቹ ይህም ቦታ በግፍ ያለ ተመጣጣኝ ክፍያ የተወሰደ የአርሶ አደር አባቶቻቸው ንብረት ነው። አንደኛው “ልማት መልካም ነገር ነው። ቦታው ለምቶ ከተማዋ ማደጓ ደስ ይላል። እድገቱ አንዱን እየገደለ መሆኑ ግን ትርጉሙ ሌላ ነው። አንዱ ደጅ እያደረ፣ ሌላው በሞቀ ቪላ የሚኖረው እስከመቼ ነው?” ሲል በንዴት ጠየቀ። አያይዞም ሰሞኑን በለገጣፎ የተነሳው ተቃውሞና እስር የአንድ ቀን ሳይሆን የቆየ ችግርና ብሶት ውጤት መሆኑንን አስረዳ።
ለገጣፎ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ የኦሮሚያ ከተሞች አርሶ አደሩ በሳንቲም ቤት የሚሰላ ካሳ እየተከፈለው ለልመና ተዳርጓል። ከከንቲባዎችና ከኦሮሚያ ባለስልጣናት ጋር በመሻረክ መሬት ንግድ ውስጥ የዋኙ ወደፊት የሚመጣው ችግር ሊታያቸው አልቻለም። ወጣቶቹ እንደሚሉት ከመሬት ንጥቂያና በቂ ካሳ ካለማግኘት ጋር በተያያዘ ገምጋሚም ተገምጋሚም የለም። ስለዚህ ህዝብ ፍርድ የሚሰጥበት ቀን ተቃርቧል። የሚያሳዝኑት የለፉበትን ሃብት አሟጠው “ማረፊያና መጦሪያ ገዛን” የሚሉት ናቸው።
በካንትሪ ክለብ መግቢያ ዋና የጥበቃ ማማ በር ፊትለፊት በተሰሩ የሳጠራ ታዛዎች ውስጥ ሽልጦ እየገመጡ የሚታዩት የቀን ሰራተኞች ዛሬ ርስት የላቸውም። አርሶ መሰብሰብ አቁመዋል። የተሰጣቸውን ገንዘብ አራግፈው በቀን ስራ መተዳደር እድላቸው ሆኗል። የጎልጉል ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንድ አዛውንት “ሲያልቅ አያምር አሉና” ዝም አሉ።
ዋናው ጉዳይ ይህንን ውሳኔ ማን ወሰነ የሚለው ነው። አቶ ጁነዲን በቀጥታ ትዕዛዝ ካላይ የተጠቀሰው መጠን ያለው መሬት ለካንትሪ ክለብ እንዲሰጥ ማዘዛቸውን ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ። ማዘዛቸው ብቻ ሳይሆን ለመሬቱ እንዲሰጥ የወሰኑት ካሳ በሳንቲም ቤት በካሬ መሆኑ ባለንብረቶቹን እስካሁን የሚያቃጥል ጉዳይ ነው። ከሁሉም በላይ የሚያንገበግበው ደግሞ አቶ ጁነዲን በስጦታ መልክ አንድ ቪላ ተበርክቶላቸዋል መባሉና “መነ ሞቲ” የሚል ቅጽል ስም የተሰጠውን ቪላ ሁሉም ማወቃቸው ነው። የጎልጉል ዘጋቢ ቤቱን ቢመለከተውም ቤቱ የአቶ ጁነዲን ስለመሆኑ በማስረጃ የቀረበ ማረጋገጫ አላየም።
ክሊኒክ፣ ሱፐር ማርኬት፣ መዋዕለ ህጻናት፣ ትምህርት ቤት፣ ቤተ መጽሃፍት፣ ጅምናዚየም፣ የጎልፍ ሜዳ፣ መዋኛ፣ የቴኒስ መጫወቻ፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የጤና ማዕከል፣ የተለያዩ የህዝብ መገልገያዎች ያሉት የካንትሪ ክለብ መኖሪያ መንደር ማዳበሪያ የማይነካው አትክልት ማዘጋጃ ቦታም አለው። በአዲስ አበባና በክልል የተመረጡ ባላብቶችና ታዋቂ አትሌቶች፣ባለስልጣናትና የዘመኑ ነገስታቶች የተሰገሰጉበት የካንትሪ ክለብ በዋና ባለቤትነት የሚያንቀሳቅሱት የአቶ መለስ አማካሪ መሃንዲስ ናቸው። ሸሪካቸው አንድ በመንገድ ስራ የተሰማራ መሬት ደላላና ኮንትራክተር እንደሆነም ለማወቅ ተችላል።
ለነዋሪዎቹ ሁሉን አሟልቶ ለማቅረብ በ1998 ዓም የተቋቋመው ካንትሪ ክለብ ለወሰደው መሬት በአግባቡ ካሳ ተከፍሎ የተሰራ ከተማ ቢሆን ኖሮ ያሰኛል። አንድ ሺህ የተለያዩ ቅርጽ ያላቸው ቪላዎችና ዘመናዊ ህንጻዎች የያዘው የመኖሪያ መንደር በርካታ የራባቸው በየቀኑ ጥርስ ይነክሱበታል። በመሬት ንግድ የጠገቡ ባለስልጣናት መጨረሻ ላይ የመደብ ትግል ውስጥ ገብተዋል። በመደብ ትግሉ ጅማሬ ለጊዜው አቶ ጁነዲን ግንባር ይሁኑ እንጂ የሚከተሉዋቸው እንዳሉ አንዳንድ መረጃዎች እየወጡ ነው።
ጁነዲን ሳዶ

በሃይማኖት ጣጣ፣ በሙስናና፣ በፖለቲካ የሃይል አሰላለፍ እየተናጠ ያለው ኦህዴድና አመራሮቹ ህወሓት ከጀመረው የማጥራት ዘመቻ አስመልክቶ ሪፖርተር ጋዜጣ አቶ ጁነዲን ከኦህዴድ ድርጅት አባልነታቸው ስለመባረራቸው ምንጮቹን ጠቅሶ ከመዘገቡ ውጪ በይፋ የገለጸ መንግስታዊ ተቋም የለም። ጎልጉል ኦህዴድ በመደብ ትግል መጫረስ ጀምሯል በሚል ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ክፍል አነጋግሮ ባስነበበው ዜና የኦህዴድ ግምገማ ሲጠናቀቅ ከሃይማኖትና ከሙስና ጋር በተያያዘ የተገመገሙ ስለመኖራቸው፣ አቶ ጁነዲን በግምገማው ቀዳሚ እንደሚሆኑ ጠቅሰን ዘግበን ነበር።
መሬታቸው ያለ በቂ ካሳ ክፍያ መወሰዱ ሲብስባቸው ተቃውሞ ካሰሙት መካካል ታስረው የነበሩት ሰባት የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ዋስ ጠርተው እንዲለቀቁ መደረጋቸውን ፖሊስ “ህዝብን ለጸረ ልማት በማነሳሳት” ወንጀል ክስ መስርቶባቸው እንደነበር የአሜሪካ ሬዲዮ አማርኛ ክፍል ሰኞ መስከረም 28 ቀን ተናግሯል።
በተያያዘ ዜና በህመም ምክንያት የሥራ መልቀቂያ አስገብተዋል የሚባሉት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳ
አለማየሁ አቶምሳ

ኦህዴድን አስመለክተው ማስተባበያ ሰጥተዋል። በቴሌቪዥን ባርኔጣ ለብሰው የቀረቡት አቶ አለማየሁ፣ ኦህዴድ እንደተዳከመ የሚናፈሰው አሉባልታ ከእውነት የራቀ መሆኑንን ካስታወቁ በኋላ “ከድርጅታችን ዓላማ ውጪ ሲንቀሳቀስ የነበረ አንድ አባል አግደናል” ብለዋል። አሉባልታ ስላሉት ግን ማብራሪያ አልሰጡም። ኦህዴድ ራሱን መገምገሙን ያስታወሱት ፕሬዚዳንቱ የቀጣዩን ዓመት በጀት በማጽደቅ በቆራጥነት ለመስራት ከስምምነት መደረሱን ተናግረዋል። እሳቸው ይህንን ይበሉ እንጂ ኦህዴድ ውስጥ የተፈጠረው አለመግባባት እታች ቀበሌ ድረስ መዝለቁን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ይናገራሉ።

No Oromo has constitutional or legal protection from the cruelty of the TPLF/EPRDF regime.

Aside

By Roba Pawelos | March 13, 2014

Roba Pawelos

Roba Pawelos

A country is not about its leaders but of its people. It goes without saying that the people are the symbolic mirror of their nation. That is exactly why foreigners particularly the development partners assess and evaluate a nation through its people. In other words, happy people are citizen of not only a peaceful and happy nation but one which accepts the principles of democracy, rule of law and human and people’s right. On the contrast, heartbroken, timid and unhappy people are subjects of dictatorial, callous and brutal regimes. Such people are robbed of their humanity and identity through systematic harassment, intimidation, unlawful detention, extra judicial killing and disappearance by the leaders who transformed themselves into creators of human life or lords. The largest Oromo nation in Ethiopia through the 22 years of TPLF/EPRDF repressive leadership has turned into a nation sobbing in the dark. One does not need to be a rocket scientist to figure this out. All it takes is a closer look at any Oromo in the face. The story is the same on all the faces: fear, uncertainty, and an unquenchable thirst for freedom. The disturbing melody of the sobs, in the dark echo the rhythmic, desire to break free from TPLF dictatorial shackles.

The Horn African region of Ethiopia is home to just 90 million people, it is also home to one of the world’s most ruthless, and eccentric, tyrannical regime. TPLF/EPRDF is ruling the nation particularly the Oromo with an iron fist for the past two decades and yet moving on. Today dissents in Oromia are frequently harassed, arrested, tortured, murdered and put through sham trials, while the people are kept in a constant state of terror through tight media control, as repeatedly reported by several human rights groups. It has been long time since the Woyane government bans most foreign journalists and human rights organizations and NGOs from operating in the country for the aim of hiding its brutal governance from the world. While the people in Ethiopia are being in terrorized by TPLF gangs, the western powers are yet looking at the country as a very strategic place to fight the so called terrorism in horn African region. But In today’s Ethiopia; as an Oromo, No one can speak out against the dictatorship in that country. You can be killed. You can be arrested. You can be kept in prison for a long time. Or you can disappear in thin air. Nobody will help. Intimidations, looting Oromo resources and evicting Oromo from their farm lands have become the order of the day everywhere across Oromia.

No Oromo has constitutional or legal protection from the killing machinery of the TPLF securities. The recent murdering of Tesfahun Chemeda in kallitti prison is a case book of the current circumstance.

Read More:- pawelos.odt

Godina addaa Finfinnee Sulultaa Keessatti Hojjettootii fi Barattooti Lammii Oromoo Ta’an Irratti Qormaati Addaa Akka Gaggeefamaa Jiru Gabaafame.Sababa Kanaan Barattooti Lamas Hidhaman.

Aside

Bitootessa 14,2014 Finfinnee

OromiaALutaContinua2011FDGQeerroo godina addaa naannowaa Finfinnee magaalaa Sulultaa irraa Bitootess 13/2014 gabaasee jiruun kanaan dura sochiilee mirga abbaa biyyummaa fi Oromommaa falmachuun Oromiyaa keessatti baldhinaan deemaa jiranii fi Yuuniversitiilee fi manneen barnootaa garagaraa keessatti FDG qabatee jiru hanga ammaatti wal harkisee itti fufaa kan jiru gabaasaan isaa bakka karaa adda addaatiin dhiyaataa jira. Gama kaaniin diddaaleen Qeerroon ona Sulultaa gaggeessaa ture addattis aanaalee Akaakoo,Gullee fi kkf gabaafamaa ture.

Kanumaan wal qabatee yeroo ammaa mootummaan Wayyaanee hojjetoota waajirtoota adda addaa irraa hojjetan kanneen lammiin Oromoo ta’an qorannaa cimaa irratti adeemsisaa ture ammas bifa hin beekamneen itti jira. Torbeewwan kana keessaa Bitooteessa gaafa 12 fi 1aanaa Galaanoo Sabooraa; mana barumsaa Galaanoo Sabooraa kutaa 11 fi 12 baratan top-ten(barattoota sadarkaa qaban) kana jechuun barattoota barumsaan dandeettii qaban kan sadarkaa qaban guyyoota lamaan kana irratti dhimma barumsaan kan wal qabate wal gayii isaan waliin adeemsisani turaniiru.

Barattootni lakoofsaa mana barumsaa kana irraa wal gayii kanaaf carraa argatan hanga nama 52 yoo ta’an barattootni dhimma wal gayii sanii ykn ajandaa jalee Wayyaanee kanaa diiguu fi akkasuma carraa argatan kanatti gaaffii gaafatamuu qaban rakkoolee mootummaan wayyaanee ilmaan Oromoo irraan gahaa jiru, saaminsa lafaa,ariyamuu barataa,hoj-dhabdummaa irratti qixa godhachuudhaan gaaffiwwan kanneen kaasuun guyyaa jedhame kana irratti barattoota kanaan gaaffii kanaan wal qabatee diddaa guddaan ka’e, barattoota kana keessaas baratoota hedduu cimoo ta’an nama lama yeroodhaaf qorannee barumsa keessaniitti deebitu jedhuudhaan mana hidhaa magaalichaatti darbamani jiru,

1. Barataa Dhugumaa Ifaa-kutaa 11ffaa
2. Barataa Geetuu Kaffaalee-kutaa 12 ffaa iraa baratan kanneen lamaan gaaffii ABOn amma fudhatee ka’ee jiru gaafachaa jirtu isintu adda dureedha jedhanii qorannoodhaan dhiyeessanii hanga ammaatti mana hidhaa keessatti akka qoratamaa jiran Qeerroon magaalaa godina addaa Finfinnee Sulultaa irraa gabaasee jira.