የኦሮሞ ነጻነት ግንባር, ሚያዚያ 5 ቀን 2018 ዓም
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን የፖለቲካ ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ኣሁንም ዝግጁ መሆኑን እያሳወቀ፡ በኦነግና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል የሚደረግ ንግግር ሶስተኛ ወገን ባለበትና ያለኣንዳች ቅድመ-ሁኔታ እንዲከናወን ጥረት ሲደረግ ቆይቶ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ፍላጎት ከማጣት የከሸፈው ጥረት እንዲቀጥል በኢህኣዴግ ለሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት ጥሪውን ያድሳል። የወያኔ/ኢሕኣዴግ መንግስት በበኩሉ የሚጠበቅበትን እንዲያሟላ ኣጥብቆ ያሳስባል።
ኦነግ ከኣንድ ምዕተ-ዓመት ተኩል በላይ እያስቆጠረ ላለው የኦሮሞ ህዝብ የመብት ጥያቄና በህዝቡ ላይ ተዘርግቶ ከባድና ዘግናኝ ሰቆቃ እያደረሰበት ያለውን የጭቆና ስርዓት ለመፋለምና የራስን እድል በራስ ለመወሰን መብት መረጋገጥ በትግል ላይ የነበረና ያለ ድርጅት መሆኑ ለሁሉም ግልጽ ነው።
የኢትዮጵያ ኢምፓዬር የፖለቲካ ችግር በውይይት መፍትሄ እንዲያገኝ ኦነግ ያደረገው ጥረት ረዥም ዓመታትን ያስቆጠረ ነው። ይህ ተመራጭ መንገድ ግን በሃይል በሚያምኑ የኢትዮጵያ መንግስታት ዘንድ ስላልተለመደ ተቀባይነት ኣላገኘም። በሰላማዊና በዲሞክራሲያዊ መንገድ ለችግሮች መፍትሄ ከማበጀት ይልቅ ከጠላት በመፈራረጅ ለመጠፋፋት ዘመቻ ማካሄድን ነው የኢትዮጵያ ገዢዎች የመረጡት። ይህ ጸረ-ዲሞክራሲ ኣቋም ያሉ የፖለቲካ ችግሮች እንዳይፈቱ በማድረግ ከትውልድ ትውልድ ኣሸጋገረ። ለመብታቸው የሚፋለሙትን ውድ መስዋዕትነት ኣስከፈለ። Continue reading
HRLHA Press Release