ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር የተሰጠ መግለጫ
(ኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር,ግንቦት 24 , 2011 ዓም) ካለፈዉ ጥር 2011 ዓም አጋማሽ ጀምሮ ለስሙ “የሀገር መከላከያ ሠራዊት” በሚል ስያሜ የሚታወቀዉ የኢሕአዴግ ጦር በኦሮሞ ሕዝብና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ላይ የሚያካሄደዉን ጦርነት ወደ አየር ድብደባ ማሳደጉ የሚታወስ ነው። በዚህም መሠረት ጥር 4 እና 5 2011 ዓም በምዕራብ ኦሮምያ በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሚ ወረዳ ዉስጥ ጃል መሮ (ኩምሣ ዲሪባ)ን ለመግደል ታቅዶ የተሰነዘረዉን የአየር ድብደባ በማካሄድ በሰላማዊ (ትጥቅ-ኣልባ) ዜጎች ህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ በወቅቱ ተዘግቦ ነበር። በዚያ ጥቃት ዒላማዉን እንደሳተ ስረዳዉ ግን “የአየር ድብደባዉን ኣላካሄድኩም” ስል ኣይኑን በጨዉ ኣጥቦ ለመካድ ሞከረ።
ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ ደግሞ እጅግ ዘግናኝና ኣሳዛኝ በሆነ መልኩ ከፍተኛ የጦር ወንጀሎችን በኦሮሞ ሕዝብ ላይ እያካሄደ ይገኛል። ይህንንም እያደረገ ያለዉ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ይግኝባቸዋል ተብሎ በሚታሰቡና ሰላማዊ ሕዝብም በሚኖርባቸዉ የምዕራብ ኦሮምያ ደኖች ላይ የጦር ሄሊኮፕቴሮችን ተጠቅሞ በዓለም-ኣቀፍ ህግ የተከለከለዉን መርዛማ ጋዝ በመርጨት ጭምር ነው። በነዚህ ዘግናኝና ኣሳፋሪ ጥቃቶች እስካሁን የበርካታ የዱርና የቤት እንስሳት ህይወት የጠፋ ስሆን በኣንዳንድ ቦታዎች ደግሞ የተወሰኑ ሰዎች ላይ ያልተለመዱ ዓይነት የጤና እክሎች ታይቷል። Continue reading


