SBO: Waxabajjii 22 bara 2018. Oduu, Ibsa Ejjennoo Walgahii Shanee Gumii ABO fi Gaaffii fi deebii Gaazexeessota Oromo Waliin Taasifame -Kutaa Xumuraa.

Aside

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስራ- ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ የኣቋም መግለጫ (ከሰኔ 9 – 19 ቀን 2018 ዓም)

Aside

(SBO/VOL- ሰኔ 21/2018ዓም): የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስራ ኣስፈጻሚ ኮምቴ የድህረ 4ኛ ጠቅላላ ጉባዔ 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ከሰኔ 9 – 19 ቀን 2018ዓም ኣካሂዶ በስኬትና በድል ኣጠናቋል። የስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴው በዚህ ስብሰባ የሊቀ-መንበሩን ጽ/ቤትና የየዘርፎቹን ሪፖርት ኣድምጦ ከመገምገሙም በተጨማሪ በስራ-ኣስፈጻሚ ኮሚቴው ስብሰባ ዋዜማ በኦሮሞ ምሁራንና በኦነግ ኣመራር መካከል በተካሄደው የፖሊሲ ጉዳዮች የምክክር ኮንፈረንስ(Policy Consultation Conference) ላይም ተወያይቶ ኣስፈላጊውን ውሳኔ ኣሳልፏል። በመቀጠልም በኦሮሞ ህዝብና በኦሮሞ የነጻነት ትግል፣ የኢትዮጵያ ኢምፓዬር ስርዓት ወቅታዊ ሁኔታ እንዲሁም በቀጠናችንና የኣለምኣቀፍ ሁኔታዎች ላይ ሰፊና በሳል ትንታኔና ውይይት ኣካሂዶ ከዚህ በታች ያለውን የኣቋም መግለጫ በማውጣት ስብሰባውን ኣጠናቋል።

የኦሮሞን ህዝብና የኦሮሞ የነጻነት ትግልን በተመለከተ

የኦሮሞ ህዝብ በጠመንጃ ኣፈሙዝ የተነፈገውን ነጻነቱን መልሶ በመጎናጸፍ በሃገሩ፡ ኦሮሚያ፡ ላይ እንደህዝብ ያለውን መብት ሙሉ በሙሉ ኣስከብሮ ለመኖር ለዓመታት የነጻነት ትግል ሲያካሄድ ነበር፥ ዛሬም በማካሄድ ላይ ይገኛል። ለነጻነት እያካሄደ በላው በዚህ ፍትሓዊ ትግልም ከጊዜ ወደ ጊዜ ኣመርቂ ድሎችን እያስመዘገበ ነው። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት፣ ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ፣ በሃገር ቤትና በውጪ ሃገራት የሚገኙ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኣባላትና ደጋፊዎች ኣልፎም ባጠቃላይ ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ የህይወት መስዋዕትነት፣ የኣካል መጉደል፣ የረጅም ዓመታ እስርና የመሳሰሉትን መስዋዕትነቶች እየከፈሉበት በከፍተኛ ቆራጥነትና ጽናት ያለማቋረጥ ያካሄዱት መራር ትግል ጠላትን ኣናግቶ፣ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች ከኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶች እንዲለቀቁ የኢሕኣዴግ መንግስትን ኣስገድዷል።
ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ ኢምፓዬር ስርዓት በህዝባችን ላይ የተዘረጋው ጭቆና፣ የመከላከያ ሃይል፣ የደህንነትና የኢኮኖሚ ዝርፊያ መዋቅር ዛሬም እንደቀጠለ ነው። ይህንን በመገንዘብ የኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ትግልን ዛሬ ከደረሰበት ደረጃ ወደፊት በማራመድ የህዝባችንን የነጻነት ዕለት ለማቅረብ ሲባል የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትንና የቄሮን እንቅስቃሴ ከማጠናከር በተጨማሪ በሁሉም ረገድ የሚካሄደው ትግል በእጥፍ ድርብ እንዲፋፋም ለማድረግ በከፍተኛ ቆራጥነት እንዲሰራ የስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴው ወስኗል።

የኢትዮጵያ መንግስትን በተመለከተ

የኢህኣዴግ መንግስት ለራሱ ጥቅም ካቋቋመው የጦርና የደህንነት ሃይል መዋቅር በተጨማሪ በተለያዩ ክልል መስተዳድሮች ውስጥ ያሰለፋቸውን ኣጫፋሪዎቹን በመጠቀም በስልጣን ዘመኑ ሙሉ በሁሉም የኢትዮጵያ ኢምፓዬር ህዝቦች ላይ ባጠቃላይ፡ በተለይም ደግሞ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ወደር የለሽ ጉዳት ሲፈጽም ቆየ። ይህ ከባድ ሰቆቃ፡ ውድ መስዋዕትነት በጠየቀ መራር ትግል ተመክቶ የኢህኣዴግን ሃይል እያዳከመና እያንበረከከ መጣ። ከዚህ ሁኔታ ውጥረት ውስጥ የገባው ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው ፓርቲ፡ ኢህኣዴግ፡ ሰሞኑን ተሃድሶ በሚል ስም ለውጥ የሚያስገኝ ኣስመስሎ እራሱን በማቅረብ ህዝቡ እውን የማይሆን ተስፋ እንዲሰንቅ ለማድረግ ኣሳሳችና ኣወናባጅ ዲስኩሮችን በስፋፍ በመንዛት ላይ ይገኛል። ይህ ፓርቲ በተግባር እየፈጸመ ያለው ግን ላለፉት 27 ዓመታት እጃቸው በደም የተጨማለቀ መሪዎቹንና ሹማምንቱን ከፊሉን እየሸለመና እያወደሰ ከግዴታቸው እያሳረፈ ከፊሉን ደግሞ ተጨማሪ ስልጣን መሾምና መንበረ-ስልጣን ላይ እንዲቀያየሩ ማድረግ ነው። እንዲህ ያለው ኣካሄድ ወደ ለውጥ የሚወስድ እርምጃ ሳይሆን ኢህኣዴግ የስልጣን ዘመኑን በማራዘም ላለፉት 27 ዓመታት በህዝቦች ላይ ሲያደርስ የነበረውን ጉዳት ኣሁንም ለማስቀጠል ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላይ መሆኑን ብቻ የሚያሳይ መሆኑ በሁሉም መታወቅ ኣለበት።

ላለፉት 27 ዓመታት የኢትዮጵያን ኢምፓዬር ህዝቦች እያሰቃየ ያለው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ችግር ምንጩ የኢህኣዴግ ፓርቲ የተመሰረተበት የጸረ-ዲሞክራሲና ጸረ-ነጻነት ዓላማና ፖሊሲ ነው። ስለሆነም ኢህኣዴግ ለሱ ብቻ እንዲሆን ብሎ የመሰረተው የጦር፣ የደህንነት፣ የኢኮኖሚና የኣስተዳደር መዋቅር በህዝቦች ትግል ተቀይሮ ህዝቦች በነጻነት የሚበጃቸውን መንግስት መርጠው ለመተዳደር የሚያስችላቸው ሁኔታ እስከሚፈጠር ድረስ በዚህ መንግስት ስርዓትና መዋቅር ውስጥ ህዝቦችን የሚጠቅም ለውጥ ሊገኝ ኣይችልም። በመሆኑም ህዝባችን መሰረታዊ ለውጥ ለማገኘት ሲል እስከዛሬ ድረስ ውድ መስዋዕትነት ከፍሎበት ኣሁን ካለበት ደረጃ ያደረሰውን ትግሉን ኣጠናክሮ በመቀጠል ከግቡ ለማድረስ በርትቶ መንቀሳቀስ ኣለበት።

ከኢትዮጵያ እስር ቤቶች የተለቀቁ የኦሮሞ ዜጎችን በተመለከተ

ህዝባችን ባጠቃላይ በተለይም ደግሞ ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኣባላት፣ ሌሎች የተጨቋኝ ህዝቦች ድርጅቶች በቀጣይነት በከፈሉት መስዋዕትነት በኦነግ ስምና ባጠቃላይ በኦሮሞ የነጻነት ትግል ስም ለዓመታት በኢህኣዴግ ወህኒ ቤቶች ውስጥ ሲሰቃዩ የነበሩ በብዚ ሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ብሄርተኞችና የሌሎችም ተጨቋኝ ህዝቦች ተወላጆች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተለያዩ እስር ቤቶች መለቀቃቸውና ኣሁንም በየእስር ቤቶቹ ውስጥ የቀሩ መኖራቸው ይታወቃል።

ለህዝባችሁ ነጻነት ሲባል ያለኣንዳች ወንጀል በደባ ታስራችሁ ለስብዓዊ ፍጡር የማይገባ ሰቆቃ ሲፈጸምባችሁ የነበራችሁ፡ ከፊሎቻችሁ ለኣካል መጉደልና ለከፍተኛ የኣእምሮ መታወክ የተዳረጋችሁ ጀግኖች የኦሮሞ ብሄርተኞች ከእስር ቤቶች በህይወት በመውጣታችሁ እንኳን ደስ ኣላችሁ! እንኳን ደስ ኣለን! እያልን የከፈላችሁት መስዋዕትነት ከባድና ኣሰቃቂ ቢሆንም እናንተ ለጉዳት የተዳረጋችሁበት የኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ትግል ኣብቦና ጎልብቶ ደጋፊዎችን በሚሊዮኖች ኣፍርቶ ህዝባችሁ በነጻነት ዋዜማ ላይ ደርሶ ማየታችሁ ኣስደሳችና የምትጽናኑበት ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

ይሁን እንጂ በደባ ኣስሮኣችሁ ይህንን ሁሉ ሰቆቃ ያደረሱባችሁ ሰዎችና ኣካላት ህግ ፊት ቀርበው የሚገባቸውን ውሳኔ እስከሚያገኙና ለደረሰባችሁ ጉዳት ተገቢው ካሳ እስካልተሰጣችሁ ድረስ ፍትህ ኣግኝታችኋል ማለት ፈጽሞ የማይቻል መሆኑን የኦነግ ስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ኣጥብቆ ያስገነዝባል። በማከልም ዛሬም በኢህኣዴግ ወህኒ ቤቶች ውስጥ ቀርተው ሰቆቃው እየተፈጸመባቸው ያሉትና የት እንደገቡ ያልታወቁት ሁሉ ያለኣንዳች ቅድመ-ሁኔታ በኣስቸኳይ እንዲለቀቁና ሁኔታቸው ለህዝቡ ይፋ እንዲሆን የስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴው ኣጥብቆ ይጠይቃል። ህዝባችንም በበኩሉ ነጻነቱን ሊያጎናጽፉት ሲሉ ከባድ ጉዳት ሲደርስባቸው የነበረውን እነዚህን ጀግኖች ልጆቹን በሚገባቸው ፍቅርና ክብር ተንከባክቦ በመያዝ ሞራላቸውን እንዲያጠናክርና በኣስፈላጊው ሁሉ እንዲደርስላቸው የስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴው ኣጥብቆ መልእክቱን ያስተላላፋል።

ኢህኣዴግ በህዝባች መካከል እያስፋፋ ያለውን ጦርነት በተመለከተ

የኦሮሞን መሬት በሁሉም ኣቅጣጫ ቆራርሶ ለባዕዳን በማከፋፈል ኦሮሚያን የሚቻላቸውን ያህል ማጥበብና የኦሮሞን ህዝብ ዲሞግራፊ መቀየር ኢህኣዴግ እንደፖሊሲ ኣስቀምጦት በእቅድ ሲተገብረው ዛሬን የደረሰ ጉዳይ ነው። ኢህኣዴግ ይህንን ከሚያደርግበት ዓላማ መካከል ኣንዱና ዋነኛው የኦሮሞን ህዝብ የነጻነት ትግል ማዳከም ነው። በዚህ የኢህኣዴግ ፖሊሲ በኦሮሞ ህዝብ ላይ በርካታ የዘር-ማጥፋት ዘመቻ ተካሄዷል። በቁጥር ከኣንድ ሚሊዮን(1,000,000) የሚልቁ የኦሮሞ ዜጎች በኦሮሞነታቸው ብቻ ከቄዬና ከኑሮኣቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ እንዲበተኑ ተደርገዋል። የኢትዮጵያ መንግስት(ኢህኣዴግ) በተለያዩ ክልል መንግስታት ኣስተዳደር ውስጥ ያሉ ኣጋሮቹንና በብሄር ስም የተደራጁ ኣንዳንድ ድርጅቶችን በመታገዝ በሰሜን፣ በምስራቅ፣ በደቡብ-ምስራቅ፣ በደቡብና በምዕራብ ኦሮሚያ በኩል ሆን ብሎ ኦሮሞና ኣጎራባቾቹ ህዝቦችን ለማናቆር እስከ ዛሬ ድረስ እያካሄደ ያለው ጦርነት ከዚሁ የኢህኣዴግ ቋሚ ፖሊሲ የሚመነጭ ነው።
በተመሳሳይ መልኩ በሌሎች ቦታዎችም በተለያዩ ህዝቦች መካከል በዚሁ የኢህኣዴግ ፓርቲ ሴራ ውጊያ እየተስፋፋ ይገኛል። ኢህኣዴግ የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም በህዝቦች መካከል ፈጥሮ እያስፋፋ ያለው ይህ ጦርነት ዛሬ በህዝቦች ላይ እያደረሰ ካለው ከባድ ጉዳት በተጨማሪ በነዚህ ህዝቦች መጻዒ ግንኙነት ላይም በቀላሉ የማይሽር ጠባሳ እየፈጠረ ያለ ጦርነት ነው። ስለሆነም ይህ ጉዳይ የኦነግ ስራ-ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ከተወያየባቸውና በዚህ ረገድ በህዝቦች መካከል ሊፈጠር የሚችለውን ኣደጋ ለመቀነስና ለማስቀረት በርትቶ ለመስራት ከወሰናቸው ኣበይት ጉዳዮች መካከል ኣንዱ ነው።

የኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ትግል እስትራቴጂና በኦሮሞ ህዝብና በኢትዮጵያ ኢምፓዬ መካከል ያለውን የፖለቲካ ችግር በንግግር(negotiation) መፍታትን በተመለከተ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ትግሉን የሚመራበትን የኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ትግል እስትራቴጂ ለይቶ ሲቀይስ የኢትዮጵያ ኢምፓዬር ተጨባጭ የፖለቲካ ሁኔታ የተመሰረተበትንና ለዘመናት መንበረ-ስልጣኑን የተፈራረቁት መንግስታትም ተወራርሰው ሲያስቀጥሉት በነበረው ሁኔታ ተገድዶ ሌላ አማራጭ በማጣት ነው። የመጫና ቱለማ ማህበር መታገድና የማህበሩን ኣባላት የገጠመው መታሰርና መገደል ለዚህ ኣብይ ማስረጃ ነው። ያ ሁኔታ ዛሬም ኣልተቀየረም። ይህም ከሚኒሊክ ኣንስቶ ወደ መንበረስልጣን የመጡት ሁሉም ሃይሎች ያለጠመንጃ ኣፈሙዝ ሰላማዊ ቋንቋ የማያውቁ መሆናቸው ነው። የኦሮሞን ህዝብ ጨምሮ ሁሉም የኢትዮጵያ ኢምፓዬር ህዝቦች ዛሬም በጠመንጃ ኣፈሙዝ ኣገዛዝ ስር ናቸው። ስለሆነም በጠመንጃ ኣፈሙዝ ስልጣን ይዞ ህዝቡን ነጻነት የነፈገን መንግስት ከላዩ ላይ በመንቀል ህዝቡ ነጻነቱን ተጎናጽፎ የሚበጀውን መንግስት መርጦ እንዲተዳደርበት ለማድረግ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከሚከተላቸው የኦሮሞ የነጻነት ትግል እስትራቴጂዎች መካከል ኣንዱ የሆነው የትጥቅ ትግል ዛሬም ሌላ ኣማራጭ የሌለው መንገድ ነው።
ስለሆነም የግላቸውንና የቡድናቸውን ስልጣንና ጥቅም ለማስጠበቅ ብቻ ያላቸውን የጦርና የፖሊስ ሃይል ሁሉ ተጠቅመው ዓላማቸውን ከግቡ ለማድረስ ሰላማዊውን ህዝብ እያስጨረሱ የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን “የትጥቅ ትግል ጊዜው ያለፈበት ፋሽን ነው።” የሚሉት ኣካላት ንግግራቸው የኦሮሞ ህዝብን ዓላማ ከሚጻረረው ኣቋማቸው የመነጨ እንጂ በተጨባጭ መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ የማያንጸባርቅና እውነታ የሌለው እንደሆነ ህዝባችን በሚገባ መገንዘብ ኣለበት።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የኦሮሞ ህዝብ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን የፖለቲካ ችግር በንግግር(negotiation) ለመፍታት መሟላት የሚገባቸውን ነገሮች የሚገልጽ የበኩሉን ፖሊሲና ኣቋም ገልጾ ለኢትዮጵያ መንግስት ጥሪውን ያደሰው ከቅርብ ጊዜያት በፊት (በሚያዚያ ወር 2018ዓም መግቢያ) ነበር። ይህንን ጥሪውንም በተለያዩ ኣለምኣቀፍ ሚዲያዎች ላይ ግልጽ ኣድርጓል። የኢትዮጵያ መንግስት ለዚህ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጥሪ እስከ ኣሁን ድረስ ኣግባብ ያለው ምላሽ ኣልሰጠም። ጥሪውን ወደጎን በመተው በተለያዩ መድረኮች ላይ በኣፍ የፖለቲካ ችግሮችን በንግግር ስለመፍታት ማውራት የሚዲያ ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ለማዋል ካልሆነ በስተቀር ለእውነተኛ ንግግር(negotiation) ዝግጁ መሆኑን የሚያሳይ ኣይደለም። ህዝባችንም ይህንን ሴራ በሚገባ ነቅቶ በመገንዘብ በንግግር(negotiation) መፍትሄ ወደ ማስገኘት የሚያመራ ኣስተማማኝ ሁኔታ እስካልተፈጠረ ድረስ እስከኣሁን ለተገኘው ድል መሰረት የሆነውና ለወደፊቱም ኣስተማማኝ ድል ማግኘት የሚያስችለውን የነጻነት ትግል እስትራቴጂ፡ የትጥቅ ትግሉን ማጠናከርና ጋሻና መከታው የሆነውን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መንከባከብ ለነጻነቱ ቁልፍ መሆኑን በሚገባ መረዳት ኣለበት።

የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች ትብብርን በተመለከተ

ለኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ትግል ዓላማ በኣፋጣኝ ከግቡ መድረስ ያለንን የሰው ሃይል፣ እውቀትና ሃብት የህዝባችንን የጋራ ጥቅም ማስጠበቅ በሚያስችል ሁኔታ ኣንድ ላይ በማምጣት የህዝባችን ትግል ይበልጥ ሃይል እንዲኖረው ማስቻል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቋሚ ፖሊሲ ነው። ስለሆነም የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም በማስከበሩ ላይ ኣብረን ሰርተን የህዝባችንን የነጻነት ዕለት ለማቅረብ ከምንችል ሁሉም የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ተባብረን መስራት ከመቸውም ጊዜ በበለጠ በኣሁኑ ጊዜ ኣስፈላጊ መሆኑን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ያምናል። ይህንን እውን ለማድረግም ጠንክሮ ይሰራል።
ካሁን ቀደም ስምምነት ፈጥረን ኣብረን ስንንቀሳቀስ የነበርን የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች ስምምነታችንን በማፍረስ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተንቀሳቀሱበት ያለው ሁኔታ የህዝባችንን የጋራ ጥቅም ለማስጠበቅ የማይረዳ መሆኑ ከግንዛቤ ገብቶ ይህ የስህተት ኣካሄድ እንዲታረም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ድርጅቶች ቆም ብለው እራሳቸውን እንዲያዩና ህዝባችንም ድርሻውን እንዲወጣ የስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴው ያሳስባል።

የህዝቦች ትብብር ለነጻነትና ለዲሞክራሲ (PAFD) በተመለከተ

የህዝቦች ትብብር ለነጻነትና ለዲሞክራሲ(PAFD) ከተመሰረተ ኣንስቶ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሮች የፖለቲካ መፍትሄ ለማበጀት ሰፊ ስራ ሰርቷል። እውነተኛ የፖለቲካ መፍትሄ ሊሆን የሚችል ሰፊ ሃሳብ መሪ ኣቅጣጫ(Road Map) ጠቁሞ የዚህን መፍትሄና ራዕዩንም የካቲት 2018ዓም በለንደን ኣካሂዶ በስኬት ባጠናቀቀው ስብሰባ ላይ ይፋ ኣደረገ። የለንደን ስብሰባ ኣያሌ ድርጅቶችን ያቀፈ ሰፊ ተሳትፎ የታየበት፣ ምሁራን፣ ዲፕሎማቶችና የኣውሮፓ ምክር ቤት ኣባላት የተሳተፉበት ነበር።
ይህ መሪ ኣቅጣጫ(Road Map) ይበልጥ ሰፍቶ በርካታ ድርጅቶችን በማወያየትና በማሳተፍ ወደ ሁሉን-ኣቀፍ ስርዓትና የሽግግር መንግስት(All Inclusive Transitional Arrangment) እንዲያመራን እየተሰራበት ይገኛል። ይህን የመጨረሻና እውነተኛ፣ እንዲሁም ሁሉን ኣሳታፊ መፍትሄ በማጎልበት ኣሁን ላለው የፖለቲካና የደህንነት ችግር በማያዳግም ሁኔታ መፍትሄ ለማስገኘት ሁሉም እንዲተባበር የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የስራ-ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ጥሪውን ያስተላልፋል። ኦነግ ትብብሩ እያደረገ ላለው ጥረትና ለስኬታማነቱ በሙሉ ሃይሉ የበኩሉን ይወጣል።

ለሁሉም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች

ለኢትዮጵያ ኢምፓዬር የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት የፖለቲካ ሃይሎችና ሁሉንም የሚመለከታቸው ኣካላት ያሳተፈ የሽግግር ጊዜ ሁኔታ(All Inclusive Process) መፈጠር ወቅታዊ ጥያቄ መሆኑን ኦነግ ያምናል። ሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች ሃሳባቸውን በሙሉ ነጻነት ለህዝቡ ኣቅርበው ሁሉም ህዝቦች ያለኣንዳች ግፊት በመጻዒ ዕድላቸው ላይ መወሰን ሲችሉ ብቻ ነው ዘላቂ መፍትሄ ሊመጣ የሚችለው።
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በበኩሉ ሁሉን-ኣሳታፊ የሽግግር ሂደት እንዲሳካ የሕዝቦች ትብብር ለነጻነትና ለዲሞክራሲ/PAFD ኣባላት ከሆኑ የትግል ኣጋሮቹ ጋር በመሆን ይሰራል። ሌሎች መሰል መሪ ኣቅጣጫ(road map) ያላቸው ቡድኖች መኖራቸውንም ኦነግ ይገነዘባል። እንደነዚህ ያሉ ቡድኖችና ለዲሞክራሲና ለነጻነት በመስራት ላይ የሚገኙ ሁሉም ሃይሎች ይህንን ሂደት ለማሳካት እንዲሰሩና በዚያው ውስጥ ድርሻቸውን እንዲያበረክቱ ለሁሉም ድርጅቶችና ሃይሎች ጥሪውን ያስተላልፋል። እንዲሁም መላው ኣለምኣቀፍ ማህበረሰብና መንግስታት ይህንን እንዲደግፉ ጥሪያችንን ኣጥብቀን እናስተላልፍላቸዋለን።

ጥሪ:

ለሰፊው የኦሮሞ ህዝብ
ህዝባችን በሃገር ቤትና በውጪም በከፍተኛ ንቃትና ያለመታከት ከነጻነት ትግሉ ጎን ቆሞ እስከዛሬ ድረስ እያበረከተ ያለው ድርሻ የሚደነቅ ነው። ከባድ መስዋዕትነት በከፈልንበት መራር ትግል ዛሬ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ወደ ነጻነታችን ተቃርበናል። ይሁን እንጂ ህዝባችን በውድ መስዋዕትነት እያገኘ ያለውን ድልና ውጤት ቀምቶ ኣቅጣጫውን በማስሳት ለራሳቸው የፖለቲካ ዓላማ ለማዋል የሚፍጨረጨሩት እየተበራከቱ መምጣታቸው መዘንጋት የለበትም። ስለሆነም ዛሬ ያለንበት ሁኔታ ለትግላችን የምናደረውን ድጋፍና ተሳትፎ በእጥፍ ድረብ እንድንጨምርና በከፍተኛ ንቃት እንድንራመድ የሚጠይቀን ነው። በሃገር ውስጥና በውጪም ያለው ህዝባችን እየተካሄደ ያለውን ይህንን ሁኔታ በሚገባ ተገዝንቦ የልጆቹን የመስዋዕትነት ፍሬ ከፖለቲካ ነጋዴዎች ጠብቆ ትግሉን በኣፋጣኝ ከግቡ ለማድረስ ድርሻውን በብቃት እንዲወጣ የኦነግ ስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ጥሪውን ያድሳል።

ለኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኣባላትና ደጋፊዎች

ህዝባችን ነጻነቱን ለመጎናጸፍ ለዓመታት እያካሄደ ዛሬን በደረሰው ፍትሃዊ ትግል ውስጥ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኣባላት ድርሻ ከፍተኛ ነው። ዛሬ የኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ትግል እየተጎናጸፈ ላለው ድል ሁሉ መሰረት የሆነው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኣባላት ለዓላማቸው ያላቸው ትዕግስት፣ ቆራጥነትና ጽናት እንዲሁም ታማኝነትና የኦሮሞ ብሄርተኞች ድጋፍ ነው ። ዛሬ ትግላችን ከደረሰበት ደረጃ ፍልሚያውን በመቀጠል ከግባችን ለመድረስ ዛሬም የኦነግ ኣባላትና ደጋፊዎች ድርሻ የላቀ ነው። የቀረን መንገድ ኣጭር ነው። ይበልጥ ማሳጠሩ ደግሞ የኛን ቆራጥነት፣ ንቃትና እራስን መስጠት ይጠይቃል። የድርጅታችን ኣባላትና ደጋፊዎች ሁሉ ይህንን በመረዳት የሚጠበቅባቸውን ድርሻ እንዲወጡ የስራ-ኣስፈጻሚ ኮሚቴው መልዕክቱን ያስተላልፋል።

ለጀግናው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት

የኦሮሞ ህዝብ አለኝታና መከታ የሆንከው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ከሃይል፣ ከሃብትና ከእውቀትም በላይ መተኪያ የሌላትን ህይወትህን ለህዝብህ ነጻነት በመስጠት ለኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ትግል ስታበረክት የነበረውና በማበርከት ላይ የምትገኘው ድርሻ በኦሮሞ ህዝብ ታሪክ ውስጥ ዝንተዓለም ከፍተኛውን ስፍራ ይዞ ይኖራል። ኣንተ ጋሻና መከታው እንደሆንከው ሁሉ የኦሮሞ ህዝብም በኣሁኑ ወቅት ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ጥላና ከለላህ ከመሆኑም በተጨማሪ ባለው ኣቅም ሁሉ ከጎንህ ለመቆም መወሰኑን በተግባር እያሳየ ነው። እስከኣሁን በከፈልከው መስዋዕትነት ኣያሌ ኣኩሪ ታሪክና ድሎችን ኣስመዝግበሃል። የህዝብህን ነጻነት በማረጋገጥ ከዚህ የላቀ ታሪክና ድል ለማስመዝገብ እራስህን ኣዘጋጅተህ በከፍተኛ ቆራጥነትና ንቃት እንድትንቀሳቀስ የስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴው መልዕክቱን ያስተላልፋል።

ለቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ

ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ ወዳጅና ጠላትን ባስደመመ ቆራጥነትና ሚስጢራዊ ጥበብ እራስህን ኣደራጅተህ በመንቀሳቀስ የሰራሀው ኣኩሪ ታሪክ የኦሮሞን ህዝብ ታላቅ ክብር ያጎናጸፈ ነው። ንቅናቄህና መስዋዕትነትህ በኣለም ላይ ተሰሚነትና ድጋፍ ከማግኘቱም በተጨማሪ የኦሮሞን ህዝብ የነጻነት ትግል ወደ ኣዲስ ምዕራፍ ኣሸጋግሯል። ይሁን እንጂ በኣሁኑ ወቅት ትላንት መኖርህን ሲክዱ፣ መጥፋትህን ሲመኙና ኣደረጃጀትህንና ንቅናቄህን ለማጥፋት ባላቸው ሃይል ሁሉ ዘምተውብህ እስራትና ዘግናኝ ግድያ ሲፈጽሙብህ የነበሩትና ዛሬም እንዲህ ካለው ድርጊት ያልታቀቡት ሃይሎች እራሳቸውን በመስዋዕትነትህ የተገኘው ድል ባለቤት ለማድረግ ሲያጣጥሩ እያየህ ነው። ስለሆነም ይህን መሰሉን ሴራ ነቅተህ በማክሸፍ እስከኣሁን ለከፈልከው መስዋዕትነት ፍሬ ለማስገኘት በላቀ ንቃት እንድትንቀሳቀስ የስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴው መልእክቱን ያስተላልፍልሃል።

የኢትዮጵያ መንግስት ስርዓትን በማገልገል ላይ ለሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች

በኑሮ ኣስገዳጅነትና በተለያዩ ሁኔታዎች ተገፋፍታችሁ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ በፌዴራል ፖሊስና በኦሮሚያ ፖሊስ እንዲሁም በተለያዩ የመንግስቱ የስራ መዋቅሮች ውስጥ የኢህኣዴግ መንግስትን በማገልገል ላይ የምትገኙ ብሄርተኛ የኦሮሞ ልጆች የህዝባችሁ የነጻነት ትግል በኣሁኑ ወቅት ከናንተ የሚፈልገውን ግዴታ በማወቅ በያላችሁበት ቦታ ሁሉ በግልም ይሁን በመደራጀት ባመቻችሁ ሁኔታ ሁሉ የህዝባችሁን ነጻነት እውን ለማድረግ በሚረዳ ነገር ላይ የበኩላችሁን ድርሻ ለመወጣት ከመቸውም ጊዜ በላይ ዝግጁ ሆናችሁ እንድትንቀሳቀሱ የኦነግ ስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴ መልዕክቱን ኣጥብቆ ያስተላልፍላችኋል።

በኢትዮጵያ ኢምፓዬር ውስጥ ለሚገኙ ሁሉም ብሔሮችና ብሄረሰቦች

የኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ትግል ዓላማ ከግቡ መድረስ የኦሮሞን ነጻነት ለማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የኢትዮጵያ ኢምፓዬር ህዝቦች ነጻነትና መብት መከበር እንዲሁም ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ዋስትና ሊሆን እንደሚችል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጽኑዕ እምነት ነዉ። የኢሕኣዴግ መንግስት በተለያዩ ጊዜያት ህዝቦችን ለማጋጨት የሚሸርበው ሴራ የኢሕኣዴግን እድሜ ለማራዘምና እስራት፣ ግድያና የሃብት ዝርፊያን ጨምሮ በተለያየ መልኩ በህዝቦች ላይ የሚያደርሰውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ ከማስቀጠል በስተቀር የትኛውንም ህዝብ የማይፈይድ መሆኑን በሁሉም ከግንዛቤ መግባት ኣለበት። ስለሆነም በኢትዮጵያ ኢምፓዬር ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ብሄሮችና ብሄረሰቦች ይህንን ተገንዝበው የኦሮሞ ህዝብና ሌሎችም ተጨቋኝ ህዝቦች ነጻነታቸውን ለመጎናጸፍ የሚያካሄዱትን ፍትሃዊ ትግል በሚችሉት ሁሉ እንዲደግፉ የኦነግ ስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ጥሪውን ያቀርባል።

ለሁሉም የኣለም መንግስታትና ማህበረሰብ

በኢትዮጵያ ስልጣን ሲፈራረቁ የነበሩት መንግስታት ሁሉ ጸረ-ዲሞክራሲ የሆነን የጭቆናና የዝርፊያ ስርዓት በጠመንጃ ኣፈሙዝ በህዝቦች ላይ በመዘርጋት እንዳሻቸው ህዝቡን እያሰሩ፣ እየገደሉ፣ ሀብቱን እየዘረፉና ከመሬቱ ኣፈናቅለው ለድህነትና ለስደት በመዳረግ ሲጨቁኑት ኖረዋል። የኢህኣዴግ ፓርቲ በ1991ዓም ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ኣንስቶ በዲሞክራሲ ስም ምሎ፣ የሃሰት የፌዴራሊዝም ኣወቃቀር በመዘርጋት ከዓለም መንግስታትና ማህበረሰብ ድጋፍ እያገኘ ዛሬን ደርሷል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እውተኛውን የኢህኣዴግ ማንነት ለህዝቦች፣ ለመንግስታትና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ኣካላት ሁሉ ከማስገንዘብ የተቆጠበበት ጊዜ የለም።

ዛሬ ህዝቦች (በተለይም የኦሮሞ ህዝብ) ውድ መስዋዕትነት በመክፈል ባካሄዱት ትግል የኢህኣዴግ እውነተኛ ማንነት በሁሉም ዘንድ ተጋልጧል። ኢህኣዴግ ላለፉት 27 ዓመታት በህዝቦች ላይ ሲፈጽም የነበረው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትና የተለያዩ ወንጀሎች የሽብርተኝነት ተግባር መሆኑን የኦሮሞ ነጻነት ግንባርና የተለያዩ ኣካላት ሲገልጹት ከነበረው በተጨማሪ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር. ኣብይ ኣህመድ በኢህኣዴግ “ፓርላማ” ፊት ቆሞ በአንደበታቸው መመስከር ጀምሯል። ኢህኣዴግ በጠመንጃ ኣፈሙዝ በህዝቡ ላይ የዘረጋው የሽብርተኝነት ስርዓትና መዋቅር ዛሬም በቦታው ኣለ። የኣለም መንግስታትና ማህበረሰብ ላለፉት 27 ዓመታት መንግስታዊ ሽብርተኝነትን(State Terrorism) ሲያካሄድ የነበረውና እሱ የዘረጋው ስርዓትና መዋቅር ኣሁንም በቦታው ባለው ስርዓት ሊመጣ የሚችል ለውጥ እንደሌለ መገንዘብ ኣለባቸው።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የኣለም መንግስታትና ማህበረሰብ ኢህኣዴግ በኣፉ የሚለፍፈውን “ለውጥ” ኣምነው ስርዓቱን ከመደገፍ ተቆጥበው መብቶቻቸውን ለማስከበር ፍትሃዊ ትግል በማካሄድ ላይ ካሉ ህዝቦች ጎን እንዲቆሙና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የትግል አጋሮቹ ከሆኑት ከህዝቦች ትብብር ለነጻነትና ለዲሞክራሲ (PAFD) ኣባል ድርጅቶች ጋር በመሆን እየሰራበት ያለውን ሁሉንኣቀፍ ሽግግር እንዲሳካ ድርሻቸውን እንዲወጡ የኦነግ ስራ-ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ጥሪውን ያድሳል።
በዚህ ኣጋጣሚ ከቅርብ ጊዜ በፊት የኣሜሪካ ኮንግረስ ያሳለፈውን እንደ ኤች ኣር-128 (HR-128) የመሳሰሉ ውሳኔዎችንና የኣውሮፓ ህብረት በተለያዩ ጊዜያት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እያደነቅን የዲሞክራሲ ስርዓትንና የህዝቦችን ነጻነት እውን ለማድረግ የሚረዱ እንዲህ ያሉ እርምጃዎች ይበልጥ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የኦነግ ስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ይጠይቃል።

ዘመኑ የጭቆና ፍጻሜ ዘመን ነው !
ድል ለኦሮሞ ህዝብ !

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስራ-ኣስፈጻሚ ኮሚቴ
ሰኔ 20, 2018ዓም

Ibsa Ejjannoo Walgahii Shanee Gumii Adda Bilisummaa Oromoo, Waxabajjii 09 – 19, 2018

Aside

Shaneen Gumii Adda Bilisummaa Oromoo walgahii dhaabbataa 2ffaa kan Kora Sabaa 4ffaa boodaa Waxabajjii 09 – 19, 2018 geggeeffatee milkii fi injifannoodhaan xumurate. Shaneen Gumii Walgahii isaa kanaan Gabaasa Waajjira Hayyu-Duree fi kan Dameelee dhaggeeffatee gilgaaluutti dabalee marii dhimmoota Imaammataa (Policy Consultation Conference) kan jal-bultii Walgahii Shanee Gumii kanatti Hayyoota Oromoo fi Hoogganoota ABO gidduutti geggeeffame irrattis mari’atee murtii barbaachisu dabarse. Itti aansuudhaanis haala Ummata Oromoo fi kan Qabsoo Bilisummaa Oromoo, haala yeroo ammaa kan sirna Impaayera Itoophiyaa, akkasumas, haala naannoo keenyaa fi kan idil-addunyaa irratti xiinxalaa fi marii bal’aa fi bilchaataa geggeessee ibsa ejjennoo armaan gadii baasuudhaan walgahii isaa goolabe.

Ummata Oromoo fi Qabsoo Bilisummaa Oromoo Ilaalchisee

Ummatni Oromoo Bilisummaa afaan qawweetiin sarbame deebisee gonfachuudhaan biyya isaa Oromiyaa irratti mirga Sabummaa isaa guutuutti kabajsiifatee jiraachuuf qabsoo Bilisummaa barootaaf geggeessaa ture, har’as geggeessaa jira. Qabsoo haqaa Bilisummaaf geggeessu kanaanis injifannoolee gurguddoo yeroo irraa gara yerootti galmeessaa jira. Waraanni Bilisummaa Oromoo, Qeerroon Bilisummaa Oromoo, miseensotnii fi deggertootni Adda Bilisummaa Oromoo kan biyya keessaa fi alaa, dabreetis Ummatni bal’aan Oromoo waliigalatti qabsoon hadhaawaan, wareegama lubbuu, hir’ina qaamaa, hidhaa baroota dheeraa fi…kkf itti baasaa murannoo fi cichoomina ol’aanaadhaan walitti fufiinsaan geggeessan diina raasee, hidhamtoota siyaasaa kumoota hedduutti lakkaawaman manneen hidhaa Itoophiyaa irraa akka gadi lakkifaman mootummaa EPRDF dirqisiisee jira. Haa tahu malee roorroon sirna Impaayera Itoophiyaatiin Ummata keenya irratti diriiree jiru, caasaan humna ittisaa, tikaa fi saamicha dinagdee har’as akkuma itti fufetti jira.

Kana hubachuudhaan Qabsoo Bilisummaa Oromoo sadarkaa har’a dhaqqabe irraa fuul-duratti furgaasuudhaan guyyaa Bilisummaa Ummata keenyaa dhiheessuuf jecha Sochii WBO fi Qeerroo daran jabeessuutti dabalee hojiin qabsoo kan fuula hundaa dacha dachaadhaan akka finiinu taasisuuf murannoo ol’aanaadhaan akka irratti hojjetamu Shaneen Gumii murteesse.

Mootummaa Itoophiyaa Ilaalchisee

Mootummaan EPRDF caasaa humna waraanaa fi tikaa dantaa ofiif ijaarratetti dabalee waahiloota isaa kan Bulchiinsa Mootummaa Naannoolee adda addaa keessaa hiriirfatetti dhimma bahuudhaan bara aangoo isaa hunda Ummatoota Impaayera Itoophiyaa hunda akka waliigalaatti, addatti ammoo Ummata Oromoo irratti miidhaa dorgomaa hin qabne raaw’achaa jiraate. Roorroon ulfaataan kun qabsoo hadhaawaa wareegama qaqqaalii gaafateen dura dhaabbatamee humni EPRDF dadhabsiifamaa fi jilbeenfachiifamaa dhufe.

Haala kana irraa muddama keessa kan gale paartiin Itoophiyaa bulchu EPRDF dhiheenya kana maqaa haaromsa jedhuun waan jijjiirama argamsiisaa jiru of fakkeessee abdii hin dhugoomne Ummatatti bulchuuf olola dogoggorsaa fi afanfaajjeeysaa bal’inaan oofaa jira. Kan Paartiin kun hojiidhaan lafa irratti gochaa jiru garuu hoogganootaa fi qondaalota isaa kan waggoota 27 dabraniif harki isaanii dhiiga Ummatootaan faalame garii isaanii badhaasaa fi faaruudhaan dirqama irraa boqochiisaa garii isaanii ammoo aangoo dabalataa muuduu fi barcuma aangoo irratti akka wal jijjiiran taasisuu dha.
Adeemsi akkanaa tarkaanfii gara jijjiiramaatti geessu osoo hin taane EPRDF umrii aangoo isaa dheereffachuudhaan miidhaa waggoota 27 dabraniif Ummatoota irraan gahaa ture ammas itti fufsiisuuf haala mijeeffachaa jiraachuu isaa qofa kan mul’isu tahuun hundaan hubatamuu qaba.

Rakkoon Siyaasaa Dinagdee fi Hawaasummaa kan waggoota 27 dabraniif Ummatoota Impaayera Itoophiyaa gidirsuutti jiru maddi isaa Kaayyoo fi Imaammata farra dimokiraasii fi farra Bilisummaa Ummatootaa kan paartiin EPRDF irratti bu’uureffame dha. Waan taheef hanga caasaan waraanaa, tikaa, dinagdee fi kan bulchiinsaa EPRDF akka isa qofaaf tolutti diriirfate sun qabsoo ummatootaan jijjiiramee Ummatootni Bilisummaadhaan mootummaa isaaniif tahu filatanii ittiin buluuf haalli dandeessisu uumamutti sirnaa fi caasaa mootummaa kanaa keessatti jijjiiramni Ummatoota fayyadu argamuu hin danda’u.
Kanaafuu Ummatni keenya qabsoo isaa kan jijjiirama bu’uuraa argamsiisuudhaaf hanga har’aatti wareegama qaalii itti baasee sadarkaa kanaan gahe cimsee itti fufuudhaan galmaan gahuuf jabaatee sossohuu qaba.

Ilmaan Oromoo Manneen Hidhaa Itoophiyaa Irraa Hiikaman Ilaalchisee

Wareegama Ummatni keenya akka waliigalaatti fi addatti ammoo, Qeerroon Bilisummaa Oromoo, miseensotni Adda Bilisummaa Oromoo, Dhaabotni saboota cunqurfamoo biroo walitti fufiinsaan baasaniin sab-boontotni ilmaan Oromoo maqaa ABO fi waliigala maqaa Qabsoo Bilisummaa Oromootiin baroota dheeraaf manneen hidhaa mootummaa EPRDF keessatti gidirfamaa turanii fi ilmaan saboota cunqurfamoo biroo kanneen kumoota hedduutti lakkaawaman dhiheenya kana manneen hidhaa gara garaa keessaa gadi lakkifamuu fi ammas kan manneen hidhaatti hafan hedduun jiraachuun ni hubatama.

Gootowwan Sab-boontotni ilmaan Oromoo Bilisummaa Saba keessaniif jecha yakka tokkoon maleetti dabaan hidhamtanii gidiraa dhala namaaf hin malle argaa turtan kan gariin keessan hir’ina qaamaa fi dhibee sammuu ulfaataaf saaxilamtan manneen hidhaa irraa lubbuudhaan bahuu keessaniif Baga gammaddan ! Baga gammadne ! jechaa, wareegamni baastan hedduu ulfaataa fi suukanneessaa tahus Qabsoon Bilisummaa Oromoo isin itti miidhamtan lalisee dagaagee hordoftoota miliyoonotaan horatee Ummatni keessan jal-bultii Bilisummaa gahee arguun keessan gammachiisaa fi kan itti obsitan taha jennee abdanna.

Haa tahu malee hanga namootnii fi qaamotni dabaan isin hidhanii gidiraa kana hunda isin irraan gahan seera duratti dhihaatanii murtii isaaniif malu hin argatinitti fi hanga miidhama isin irra gahe kanaaf beenyaan malu isiniif hin kennaminitti haqa argattanii jirtu jechuun gonkumaa kan hin danda’amne tahuu Shaneen Gumii gadi jabeessee hubachiisa.
Itti dabalees kanneen har’a illee manneen hidhaa EPRDF keessatti hafanii gidiraa sana dhandhamaa jiranii fi kanneen achi buuteen isaanii wallaalamee jiru hundi haal-duree tokko malee hatattamaan akka gadi lakkifamanii fi haalli isaanii Ummataaf ifa taasifamu Shaneen Gumii cimsee gaafata.

Ummatni keenyas gama isaatiin gootowwan ilmaan isaa kanneen bilisummaa isa gonfachiisuuf jecha miidhaan ulfaataan irra gahaa ture kanneen jaalalaa fi kabaja isaaniif maluun qabaa godheefii hamilee isaanii jajjabeessuu fi dirmachuu isaaniif feesisu hundaas akka taasisuuf Shaneen Gumii jabeessee dhaama.

Lola EPRDF Ummatoota Gidduutti Babal’isaa Jiru Laalchisee

Lafa Oromoo gama hundaan cicciranii alagaaf qooduudhaan Oromiyaa hanga danda’an dhiphisuu fi demography Ummata Oromoos jijjiiruun waan EPRDF akka imaammataatti lafa kaawwatee karooraan irratti dalagaa yoona gahe dha. Akeeka EPRDF kana godhuuf keessaa guddaan tokko Qabsoo Bilisummaa Oromoo dadhabsiisuu dha. Imaammata EPRDF kanaan duulli shanyi-duguuggii hedduun Ummata Oromoo irratti geggeeffamee jira. Ilmaan Oromoo lakkoofsaan miliyoona tokko (1,000,000) caalan Oromummaa isaanii qofaan qe’ee fi jireenya isaanii irraa humnaan buqqaafamanii dirree irratti akka faca’an taasifameera.

Lolli Mootummaan Itoophiyaa (EPRDF) waahiloottan isaa Bulchiinsa Mootummoota Naannoo adda addaa keessa jiranii fi Dhaabota maqaa Sabootaan ijaaraman garii gargaarsifachuudhaan karaa Kaabaa, Bahaa, Kibba-Bahaa, Kibbaa fi Dhiha Oromiyaa irraan tahe jedhee Oromoo fi Ummatoota ollaa isaa walitti diruudhaan hanga har’aatti geggeessaa jiru imaammata dhaabbataa EPRDF kana irraa kan maddu dha.

Haaluma wal fakkaatuun bakkoota biroottis Ummatoota adda addaa gidduutti shiruma Paartii EPRDF kanaan lolli babal’ifamaa jira. Lolli EPRDF umrii aangoo isaa dheereffachuudhaaf Ummatoota gidduutti uumee babal’isaa jiru kun miidhaa ulfaataa har’a Ummatoota irraan gahaa jirutti dabalee hariiroo Ummatoota kanaa kan hegeree irrattis godaannisa laaftuutti hin fayyine kan uumaa jiru dha.

Waan taheef dhimmi kun dhimmoota jajjaboo Shaneen Gumii irratti mari’atee fi balaa gama kanaan Ummatoota gidduutti dhalachuu malu xiqqeessuu fi hanqisuufis ciminaan irratti hojjechuuf murteeesse keessaa isa tokko.

Tarsiimoo Qabsoo Bilisummaa Oromoo fi Rakkoo Siyaasaa Ummata Oromoo fi Impaayera Itoophiyaa gidduu jiru haasawaan (negotiation) furuu laalchisee

Addi Bilisummaa Oromoo Tarsiimoo Qabsoo Bilisummaa Oromoo kan ittiin masakamee qabsicha hoogganu oggaa filate haala qabatamaa siyaasni Impaayera Itoophiyaa irratti bu’uurfame kan mootummootni dhufaa-dabraan barcuma aangoo sana irratti wal jijjiiranis dhaalanii itti fufsiisaa turaniin dirqamee filmaata biraa dhabuudhaani. Ugguramuun Waldaa Maccaa fi Tuulamaa fi hidhaa fi ajjeechaan miseensota Waldichaa mudate kanaaf ragaa guddaa dha. Haalli sun har’as hin geeddaramne. Innis Minilik irraa eegalee humnootni aangootti dhufan hunduu afaan qawwee malee afaan nagaa/dadaa kan hin beekne tahuu isaanii ti.

Ummata Oromoo dabalatee Ummatootni Impaayera Itoophiyaa hundi har’as bulchiinsa afaan qawwee jala jiru. Waan taheef mootummaa afaan qawweetiin aangoo qabatee Bilisummaa Ummataa sarbe of irraa buqqisuudhaan Ummatni Bilisummaa gonfatee mootummaa isaaf tahu filatee akka ittiin bulu taasisuuf tarsiimoo Qabsoo Bilisummaa Oromoo kan Addi Bilisummaa Oromoo hordofu keessaa tokko kan tahe Qabsoon Hidhannoo har’as daandii filmaata biraa hin qabne dha.

Waan taheef warri aangoo fi dantaa dhuunfaa fi murna isaanii tikfachuu qofaaf humna waraanaa fi poolisaa qaban hundatti dhimma bahanii kaayyoo ofii galmaan gahachuuf Ummata nagaa ficcisiisaa Adda Bilisummaa Oromootiin “Qabsoon Hidhannoo faashina yeroon itti dabree dha.” jedhan, jechi isaanii ejjennoo isaanii kan faallaa dantaa Saba Oromoo irraa kan maddu malee haala qabatamaa lafa irra jiru kan hin ibsinee fi dhugaa kan of keessaa hin qabne akka tahe Ummatni keenya tolchee hubahcuu qaba.

Addi Bilisummaa Oromoo rakkoo siyaasaa Ummatni Oromoo mootummaa Itoophiyaa waliin qabu haasawaan (negotiation) furuuf wanneen guutamuu qaban kan ibsu imaammataa fi ejjennoo gama isaa ibsee mootummaa Itoophiyaaf yaamicha kan haaromse dhiheenyuma kana (jalqaba baatii Eblaa 2018) ture. Yaamicha isaa kanas miidiyaalee addunyaa adda addaa irratti ifa taasisee jira.
Mootummaan Itoophiyaa hanga har’aatti yaamicha kanaaf deebii sirnaa hin kennine. Yaamicha sana maddiitti dhiisuudhaan wal-tajjii adda addaa irratti afaaniin waa’ee rakkoo siyaasaa haasawaan furachuu odeessuun olola miidiyaa irraa tolfachuuf yoo tahe malee haasawa (negotiation) dhugaatiif qophii tahuu kan agarsiisu miti.

Ummatni keenya shira kana sirriitti itti dammaqee hubachuudhaan hanga furmaata karaa haasawaa (negotiation) argamsiisuuf haalli amansiisaan hin uumaminitti Tarsiimoo Qabsoo Bilisumma kan injifannoo hanga ammaatti argameef bu’uura tahee fi fuula duraafis injifannoo waaraa gonfachuuf isa dandeessisu Qabsoo Hidhannoo jabeeffachuu fi Irree fi Gaachana isaa kan tahe Waraana Bilisummaa Oromoo kunuunfachuun furtuu Bilisummaa isaa tahuu tolchee hubachuu qaba.

Tumsa Dhaabota Siyaasaa Oromoo Laalchisee

Galma gahiinsa Qabsoo Bilisummaa Oromoo shaffisiisuuf humna namaa, beekumsaa fi qabeenya Ummata keenyaa akka dantaa waloo Saba keenyaa tiksisiisuu danda’utti walitti fiduudhaan qabsoo Ummata keenyaa daran humneessuun Imaammata dhaabbataa Adda Bilisummaa Oromoo ti. Waan taheef Dhaabota Siyaasaa Oromoo kan dantaa Saba Oromoo kabajsiisuu irratti waliin hojjennee guyyaa Bilisummaa Ummata keenyaa dhiheessuu dandeenyu hunda waliin wal tumsinee hojjechuun yoomuu caalaa yeroo ammaa barbaachisaa tahuu Addi Bilisummaa Oromoo ni amana. Kana dhugoomsuufis jabinaan hojjeta.

Dhaabotni siyaasaa Oromoo kanneen ammaan dura waliigaltee uummannee sossohaa turre waliigaltee keenya diiguudhaan haalli dhiheenya kana itti sossohaa jiran dantaa waloo Ummata keenyaa tiksisiisuuf kan hin gargaarre tahuun hubatamee adeemsi dogoggoraa kun akka sirratuuf Dhaabotni dhimmi kun isaan ilaalu akka dhaabbatanii of ilaalanii fi Ummatni keenyas qooda isaa akka bahatu Shaneen Gumii hubachiisa.

Tumsa Ummatootaa Bilisummaa fi Dimokiraasiif (PAFD) Ilaalchisee

Tumsi Ummatootaa Bilisummaa fi Dimokrasiif (PAFD) erga ijaaramee kaasee rakkina siyaasaa Itoophiyaa furmaata siyaasaa itti gochuuf hojii bal’aa hojjatee jira. Yaada bal’aa kan dhugaatti furmaata siyaasaa ta’uu danda’u kallattii masakaa (Road Map) akeekee furmaata kanaa fi mul’ata isaatis walgahii London kan Gurraandhala 2018 geggeeffamee milkiin xumurame irratti ifa taasise. Walgahiin London sun hirmannaa bal’aa dhaabota hedduu kan hammate, beektotni, dippilomaatotni fi Miseensotni mana Maree Awuroppaa kan keessatti hirmaatan ture. Kallattiin Masakaa (Road Map) kun caalaatti bal’atee dhaabota hedduu mariisisuu fi hirmaachisuudhaan gara Sirnaa fi Mootummaa Cehumsaa hunda hammataatti (All Inclusive Transitional Arrangment) akka nu geessuuf irratti hojjatamaa jira. Furmaata maayyii fi dhuga-qabeessa, akkasumas, hunda hirmaachisaa kana gabbifatuudhaan rakkina siyaasaa fi nageenyaa amma jiruuf akka lamuu itti nu hin deebifnetti furmaata argamsiisuuf hundi akka tumsu Shaneen Gumii yaamicha isaa dabarsa. ABO tattaaffii TUBD (PAFD) godhaa jiruu fi milkaawina isaatiif gahee isaa humna guutuudhaan kenna.

Dhaabota Siyaasaa Itoophiyaa Hundaaf

Rakkoon siyaasaa, dinagdee fi hawaasummaa Impaayera Itoophiyaatti furmaata waaraa gochuuf humnootni siyaasaa fi qaamotni dhimmi ilaalu hundi kan keessatti hirmaatan haalli yeroo cehumsaa (All Inclusive Process) uumamuun gaaffii yeroo tahuu ABOn ni amana. Humnootni siyaasaa hundi yaada isaanii Bilisummaa guutuudhaan Ummataaf dhiheessanii Ummatootni hundi dhiibbaa tokkoon maleetti waa’ee hegeree isaanii irratti murteessuu gaafa danda’an qofa furmaatni waaraan dhufuu danda’a.

Addi Bilisummaa Oromoo gama isaatiin deemsi Ceehumsaa hunda hammataa tahe akka milkaawu waahiloota isaa miseensota TUBD/PAFD waliin irratti hojjataa jira. Gartuuleen kaan kallattii masakaa (road map) fakkaataa qaban akka jiranis ABO ni hubata. Gartuuleen akkasii fi humnootiin dimokrasii fi bilsummaaf hojjataa jiran hundi adeemsa kana milkeessuuf akka hojjatanii fi achi keessattis gahee isaanii akka kennan dhaabota hundaa fi humnoota hundaaf waamicha isaa dabarsa. Akkasumas hawaasni fi mootummootni idil-addunyaa hundi kana akka deeggaran waamicha keenya gadi jabeessinee dabarsinaaf.

Yaamicha Ummata Bal’aa Oromoof

Ummatni keenya biyya keessaa fi alattis dammaqiinsaa fi of kenniinsa guddaadhaan Qabsoo Bilisummaa isaa cinaa dhaabbatee qoodni hanga har’aatti kennaa jiru kan dinqisiifamu dha. Qabsoo hadhaawaa wareegama ulfaataa itti baasneen har’a kan yeroo kamuu caalaa Bilisummaa keenyatti dhihaannee jirra. Haa tahu malee injifannoo fi bu’aa Ummatni keenya wareegama qaaliidhaan argachaa jiru saammatanii gara dabarsuudhaan akeeka siyaasaa ofiif oolfachuuf kanneen wixxifatan heddummaachaa dhufuun dagatamuu hin qabu.
Waan taheef, haalli har’a keessa jirru deggersaa fi hirmaannaa qabsoo keenyaaf taasisnu dacha dachaan akka daballuu fi dammaqiinsa ol’aanaadhaan akka tarkaanfannu kan gaafatu dha. Ummatni keenya kan biyya keessaa fi alaas haala deemaa jiru kana sirriitti hubatee firii wareegama ilmaan isaa daldaltoota siyaasaa irraa tikfatee galii isaa shaffisaan dhaqqabuuf qooda isaa gahummaadhaan akka bahatu Shaneen Gumii yaamicha isaa haaromsa.

Miseensotaa fi Deggertoota Adda Bilisummaa Oromoof

Qabsoo haqaa Ummatni keenya Bilisummaa isaa gonfachuuf barootaaf gaggeessaa yoona gahe keessatti qoodni miseensota Adda Bilisummaa Oromoo ol’aanaa dha. Obsa, murannoo fi cichoomina, akkasumas, of kenniinsaa fi amanamummaa Kaayyoo miseensota Adda Bilisummaa Oromoo fi deggersa sab-boontota Oromootu injifannoo har’a Qabsoon Bilisummaa Oromoo gonfachaa jiru kana hundaaf bu’uura tahe. Sadarkaa qabsoon keenya har’a irra geesse irraa itti fufsiisuudhaan galma keenya dhaqqabuuf har’as qoodni miseensotaa fi deggertoota ABO irraa eegamu guddaa dha. Karaan nu hafe gabaabaa dha. Caalaatti gabaabsachuun ammoo murannoo, dammaqiinsaa fi of kenniinsa keenya gaafata. Miseensotaa fi deggertootni Dhaaba keenyaa hundi kana hubachuudhaan qooda isaan irraa eegamu hunda akka bahatan Shaneen Gumii jabeessee dhaamsa dabarsa.

Gooticha Waraana Bilisummaa Oromoof

Irree fi Gaachana Ummata Oromoo kan taate Gootichi Waraana Bilisummaa Oromoo (WBO) humna, qabeenyaa fi beekumsaan olitti lubbuu jijjiirraa hin qabne Bilisummaa Saba keetiif kennuudhaan qoodni ati Qabsoo Bilisummaa Oromoof gumaachaa turtee fi jirtu seenaa Saba Oromoo keessatti bara baraan iddoo ol’aanaa qabatee jiraata. Akkuma ati Irree fi Gaachana isaa taate, Ummatni Oromoos yeroo ammaa kan yeroo kamuu caalaatti dahoo fi golgaa siif tahuutti dabalee waan qabu hundaan si cinaa dhaabbachuuf murteeffachuu isaa hojiidhaan agarsiisaa jira. Wareegama hanga ammaatti baasteen seenaa boonsaa fi injifannoo gurguddaa hedduu galmeessitee jirta. Bilisummaa Ummata keetii mirkaneessuudhaan seenaa fi injifannoo kanaa olii galmeessuuf of qopheessitee murannoo fi dammaqiinsa ol’aanaadhaan akka sossootu Shaneen Gumii dhaammata.

Qeerroo Bilisummaa Oromoof

Qeerroon Bilisummaa Oromoo murannoo fi qaroomina iccitaawaa firaa fi diina ajaa’ibsiiseen of ijaartee sochootee seenaa boonsaan hojjette kan Ummata Oromootti kabajaa guddaa hore dha. Sochii fi wareegamni kee Addunyaa irratti dhageeytii fi mararfannoo argachuutti dabalee Qabsoo Bilisummaa Oromoo boqonnaa haaraa seensisee jira.

Haa tahu malee yeroo ammaa humnootni kaleessa jireenya kee haalaa, dhabama kee hawwaa fi jaarmayaa fi sochii kee dhabamsiisuuf humna qaban hundaan sitti duulanii hidhaa fi ajjeechaa suukanneessaa si irratti geggeessaa turanii fi har’a illee gochaa akkanaa irraa hin dhaabbatin injifannoo wareegama keetiin argametti abbaa of taasisuuf oggaa foolatan argaa jirta. Waan taheef shira akkanaa itti dammaqxee hoongessuudhaan wareegama hanga ammaa baastetti firii gochuuf dammaqiinsa cimaadhaan akka sossootu Shaneen Gumii siif dhaama.

Ilmaan Oromoo Sirna Mootummaa Itoophiyaa Tajaajilaniif

Dirqama jireenyaa fi haala adda addaatiin dhiibamtanii Raayyaa Ittisaa Itoophiyaa, Poolisa Federaalaa fi Poolisa Oromiyaa, akkasumas, caasaalee hojii mootummichaa kan gara garaa keessatti mootummaa EPRDF tajaajiluu irratti kan argamtan sab-boontotni ilmaan Oromoo dirqama lammummaa kan Qabsoon Bilisummaa Ummata keessanii yeroo ammaatti isin irraa barbaadu beekuudhaan bakka jirtan hundatti mata mataanis tahe wal gurmeessuudhaan haala isiniif danda’ame hundaan waan Bilisummaa Ummata keessanii dhugoomsuuf gargaaru irratti qooda gama keessanii bahachuudhaaf kan yeroo kamuu caalaatti qophii taatanii akka sochootan Shaneen Gumii gadi jabeessee yaamicha isiniif godha.

Sabaa fi sab-lammoota Impaayera Itoophiyaa Keessa Jiran Hundaaf

Akeekni Qabsoo Bilisummaa Oromoo galma gahuun Bilisummaa Oromoo mirkaneessuu qofaaf osoo hin taane Bilisummaa fi kabajamuu mirga Ummatoota Impaayera Itoophiyaa hundaaf, akkasumas, nagaa fi tasgabbii naannichaaf wabii tahuu akka danda’u Addi Bilisummaa Oromoo jabeessee amana. Shirri mootummaan EPRDF Ummatoota walitti buusuuf yeroo adda addaatti dalagu umrii aangoo EPRDF dheeressuu fi hidhaa, ajjeechaa fi saamicha qabeenyaa dabalatee dhiittaa mirga dhala namaa bifoota adda addaan Ummatoota irra gahu itti fufsiisuudhaan ala Ummata kamiinuu kan hin fayyadne tahuun hundaan hubatamuu qaba.
Waan taheef, Sabaa fi Sab-lammootni Impaayera Itoophiyaa keessa jiran hundi kana hubachuudhaan qabsoo haqaa Sabni Oromoo fi sabootni cunqurfamoon biroos Bilisummaa ofii gonfachuuf geggeessan waan danda’an hundaan akka tumsan Shaneen Gumii ABO yaamicha godha.

Mootummootaa fi Hawaasa Addunyaa Hundaaf

Mootummootni Ioophiyaa dhufaa-dabraan aangoo irratti wal jijjiiraa turan hundi farra dimokiraasii kan tahe sirna cunqursaa fi saaminsaa afaan qawweetiin ummatoota irratti diriirsuudhaan akka barbaadanitti ummata hidhaa, ajjeesaa, qabeenya isaa saamaa fi dachii isaa irraa buqqisanii hiyyummaa fi baqattummaaf saaxiluudhaan itti roorrisaa jiraatan. Paartiin EPRDF bara 1991 oggaa gara aangootti dhufu irraa eegalee maqaa dimokiraasiitiin kakatee, federaalizimii sobaa caasessuudhaan Mootummootaa fi Hawaasa Addunyaa irraa deggersa argachaa yoona gahe.

Addi Bilisummaa Oromoo eenyummaa EPRDF isa dhugaa Ummatoota, mootummootaa fi qaamota dhimmi ilaalu hunda hubachiisuu irraa yeroon itti of qusate hin jiru. Har’a qabsoo Ummatootni (keessattuu Ummatni Oromoo) wareegama qaalii itti baasuudhaan geggeessaniin eenyummaan EPRDF inni dhugaa hunda biratti saaxilamee jira. Dhiittaan mirga dhala namaa fi yakkootni adda addaa EPRDF waggoota 27 dabraniif Ummatoota irratti dalagaa bahe gocha shoororkeessummaa akka tahe kan Addi Bilisummaa Oromoo fi qaamotni gara garaa ibsaa turanitti dabalee yeroo ammaa Muummichi Ministeeraa Itoophiyaa Dr. Abiy Ahmed “Paarlaamaa” EPRDF dura dhaabbatee afaan isaatiin ragaa bahuu eegalee jira.

Sirnaa fi caasaan shoororkeessummaa EPRDF afaan qawweetiin Ummata irratti diriirfate har’as bakkuma jira. Mootummootni fi hawaasni Addunyaa mootummaa ganna 27 oliif shoororkeessummaa sadarkaa mootummaa (State Terrorism) geggeessaa bahee fi har’as caasaa fi sirni inni diriirfate bakkuma jiru kanaan jijjiiramni dhufuu danda’u akka hin jirre hubachuu qaban.

Addi Bilisummaa Oromoo Mootummootni fi hawaasni Addunyaa “Jijjiirama” EPRDF afaan qofaan lallabu amananii isa deggeruu irraa dhaabbatanii Ummatoota mirga isaanii kabajsiifachuuf qabsoo haqaa geggeessaa jiraniif akka tumsanii fi ceehumsi hunda hammataa tahe kan Addi Bilisummaa Oromoo Dhaabota miseensota TUBD/PAFD waliin irratti hojjechaa jiru akka milkaawuuf qooda gama isaanii akka bahatan Shaneen Gumii ABO yaamicha isaa haaromsa.

Carraa kanatti dhimma bahuudhaan murtiilee akka HR-128 kan manni marii mootummaa USA (US Congress) dhiheenya kana dabarsee fi tarkaanfiilee European Union yeroo adda addaatti fudhachaa jiru dinqisiifachaa tarkaanfiileen sirna dimokiraasii fi bilisummaa ummatootaa dhugoomsuuf gargaaran akkasii caalaatti jajjabeeffamanii akka itti fufuu qabanis Shaneen Gumii ABO gaafata.

Gadaan Gadaa Xumura Gabrummaa ti !
Injifannoo Ummata Oromoof !

Shanee Gumii ABO
Waxabajjii 20, 2018

SQ:- Injifannoo WBO

Aside

Gootichii WBO Godina Gujii Bahaa keessa socho’u guyyaa kaleessa Waxabajjii 21, 2018 humna waraana diinaa gara iddoo qubsuma ishee Ona Gooroo Doolaa, bakka qubsuma ishee magaalaa Jiddoolatti adeemaa jirtu irratti tarkaanfii laalessaa fudhatee loltootni diinaa namni kudhanii lama (12) yammuu ajjeefaman, madoon gara nama kudhanii ol ta’uu ummatni naannichaa nuuf dhaamanii jiru. Humni diinaa yeroo tarkaanfiin kun irratti fudhatametti konkolaataa lama wal duraaf duubaan adeemaa kan turan yammuu ta’u haxxee hidhuudhaan haleellaan laalessaan irratti fudhatamuun konkolaataan fuula dura adeemu erga nagaadhaan dabarfamee booda konkolaataa boodarraan deemaa ture irratti xiyyeeffatuun gaaga’ama ol aanaa irraan gahamee akka jiru gabaafamee jira.
Waraanni Wayyaanee Goninoota Gujii Bahaa fi Dhihaa keessa qubatee jiru ummata Oromoo nagaa yakka tokko malee ajjeessuun goolessaa akka jiru deddeedi’amee gabaafamaa turuun ni yaadatama.
Muummichi Minesteeraa Wayyaanee Dr. Abiyyi Ahmad dheengadda paarlaamaa Wayyaanee irratti yammuu dubbatu “Waraanni Kan faashinni isaa itti darbe dha; kottaa karaa nagaa qabsaa’aa” jechuudhaan jaarmaalee akka Adda Bilisummaa Oromoo, Adda Bilisummaa Biyyoolessa Ogaaden fi Ginbot-7 akka biyyatti galanii qabsaa’an waamicha taasisuun kan yaadatamu yammuu ta’u, yeroo amma kanatti waraanni Wayyaanee ammoo Oromiyaa keessatti bobba’ee ummata Oromoo Gujii, Booranaa, Harargee fi Wallaggaa goolessuutti bobba’ee akka argamu gabaafamaa jira.