ከማይሰለጥነዉ የዕብሪተኞች አንደበት

Aside

“እስርቤቱ  ኦሮሞ ኦሮሞ ይሸታል…”

 Jiituu Lammii Irraa

barruuዘመነ ቅኝ-ግዛት (the colonial era) ሲታሰብ ለኣፍርካ ሕዝብና ለምድሪቷ የማይሽር  መራራ ትዝታ ኣለዉ። የዚህ ክፉ ቀን የክፋቱ ልክ፣ የሕመሙ መጠንና የጸጸቱ ጥልቀት ከወሰን ያለፋ ዘመን ተሻጋሪ ነዉ።  የሀገር ባለቤትነትን ከመነጠቅ ኣልፎ ከሰብዓዊ ፍጡር ምድብ እስከ መዉረድ የደረሰ በደል የተስተናገደበት የታሪክ ጥቀርሻ በመሆኑ መቼም በጊዜ ወሰን የማይገደብ የታሪክ ትዉስታ ይዞ ይቆያል። ጥቁሩ ባለሀገር ሕዝብ (the indigenous people) በነጮቹ ወራሪዎች ዕይታ ሲመዘን እንደሳይጠን፣ ያልሰለጠነና ክፉ እንስሳ እንጂ እንደሰብዓዊ ፍጡር አይታሰብም ነበር። ይህንኑ አመለካከት ለማስረጽ ሲባልም ሁለንተናዊ ማንነቱን የሚያጥላሉ በርካታ አዋራጅ (pejorative) ስያሜዎች ተሰጥቶታል። የኣፍርካ ምድርም ቢሆን ወርቅና አልማዝ በገፍ እየታፈሰበት እንኳ የጨለማ ዕምብርት (heart of the darkness, the abode of barbarism and cruelty) ከመባል ኣላመለጠም።

በኣንጻሩ ደግሞ ነጮቹ ቅኝ ገዥዎች ለራሳቸዉ የሚሰጡት ግምትና ሁለንታናዊ ማንነታቸዉን የሚስሉት በታቃራኒዉ ገጽታ ነበር። ቋንቋቸዉ፣ ባሕላቸዉ፣ የተፈጥሮ ገፀ-ቀላማቸዉና ተክለ- ሰዉነታቸዉ በአጠቃላይ ሁለንተናዊ ማንነታቸዉ የመጠቀና የበላይ (superior) እንደሆነ ይሰብካሉ። ጥቁሩ ሕዝብ በኣእምሮ ብስለትም ሆነ በሰዉነት ብቃቱ የበታች (inferior) ሆኖ እንደተፈጠረ በጭፍኑ ይመሰክራሉ።  እንግሊዛዊዉ ታዋቂ ደራሲና ገጣሚ Rudyard Kipling ጥቁር ሕዝቦችን ማሰልጠንና ማስተዳደር የነጮቹ ዋነኛ ኃላፊነትና ሸክም እንደሆነ በድፍረት ተናግሯል። የብሪትሽ ቅኝ ግዛትን ወደ ኣፍርካ በማስፋፋቱ ሂደት ላይ ከፍተኛ ሚና የነበረዉ ፌረድሪክ ሉጋርድም (Frederick Lugard) በበኩሉ “ለዚህ ስልጣኔ ኣልባና የጭለማ ዕምብሪት ለሆነዉ ሕዝብና ምድር የባሕል ግስጋሴና የስልጣኔ ብርሃን ማምጣት ነዉ” በማለት የወረሪዎቹን ስዉር ዓለማ ምክንያታዊ ለማስመሰል ጥሯል

ይህንን ኣንዱን የበላይ ሌላዉን የበታች ማድረግን ዓላማዉ ያደረገ ኣድሎኣዊ የማንነት አሳሳል( Identity characterization) ለመተግበር ከፍተኛ የቋንቋ ምሁራንን (lexicographers, psycholinguists, editors) ወዘተ የመሳሰሉትን እንዳሳተፋ ይነገራል። ትርጉሙ ወይንም ቃላቶቹ የሚሸከሙት ምስል(connotation) ከእዉነተኛዉ ኣፍሪካዊ ማንነት ጋር ምንም ዓይነት ዝምድና ባይኖረዉም እንኳ በሂደት ግን የሥነ-ልቦና ተጽዕኖ ማሳደሩ አልቀረም። ዛሬም ቢሆን እነዚህ ሁለቱ ቀለማት በብዙዎቹ ኣእምሮ ዉስጥ የሚፈጥሩት ምስልና የሚወክሉት ቃላዊ ፍቺ የተጽዕኖዉን ጥልቀት ያመላክታል። ያም ሆኖ ግን የሕዝቦችን እዉነተኛ ማንነት ዉጦ የሚቀር ኃይል አልተገኘምና ቀኑ ሲደርስ የጭለማ ስብከት በእዉነተኛ ብርሃን ከመሸነፍ አልተረፈም።

ለመንደርደሪያ ያህል ካነሳሁት አጭር ቅኝት ሰሞኑን በእጅጉ ሲከነክነኝ ወደ ሰነበተዉ ተመሳሳይ ጉዳይ ልዝለቅ። የኦሮሞን ሕዝብ ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክና አጠቃላይ የማንነት እሴቶቹን ለመደምሰስ ዘመናትን ያስቆጠረ ዘመቻ ሲካሄድ መቆየቱ አጠያያቂ አይደለም። ሆኖም ግን ህዝቡ በዚህ ረገድ ባካሄደዉ ትግል በሚያስደንቅ ፍጥነት እዉነተኛ ማንነቱን በትዉልዱ ልብ ዉስጥ መልሶ ለመስረጽ ተችሏል። በዚህ የትግል ዕምርታ የሚደነግጡ ቀናተኛ ግለሰቦች ኣለዋቂነታቸዉን በሚያሳብቅ መልኩ በደነገጡ ቁጥር ኣላዋቂነታቸዉን የሚያጎላ አጸያፊ ቋንቋን ከመጠቀም ኣልታቀቡም። ከማይሰለጥነዉ የዕብሪተኞች አንደበት