Aside

(SBO-CAAMSAA 19, 2020)
Hayyu-dureen ABO Jaal Daawud Ibsaa kanneen gadda isaanii waliin qooddataniif galata galchu.

Aside

ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የ2012 የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ህገ መንግስታዊ አጣብቂኝን ለመሻገር የሚረዳ የመፍትሄ አቅጣጫ 

1.-የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
2-የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር
3.የኦሮሞ ፌዴራላዊ  ኮንግረስ
4.የአገው ብሔራዊ ሸንጎ
5. የሞቻ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ
6.አሬና ትግራይ ለሉዓላዊነትና ለዲሞክራሲ
7. ከፋ አረንጓዴ ፓርቲ
የጋራ መግለጫ
የኢትዮጵያ  ምርጫ  ቦርድ  በኮሮና ቫይረሰ  ወረርሽኝ  ምክንያት  የ2012  ጠቅላላ  ምርጫን  በተያዘለት  የጊዜ ሰሌዳ ማካሄድ እንደማይችል  መግለጹ ይታወሳል። ይህንኑ  ውሳኔ የሕዝብ  ተወካዮች  ምክር  ቤት አጽድቆታል።  በሕገ-መንግሥቱ  መሠረት   የመንግሥት የሥራ  ዘመን አምስት  (5) ዓመት ብቻ ስለሆነ አሁን ያለው መንግሥት  ከመስከረም  30፣ 2013 በኋላ ሕጋዊነቱ ያበቃል። ይህን ታሳቢ በማድረግ ምርጫ ከመደረጉ በፊት የመንግሥት የሥራ ዘመን የሚያበቃ መሆኑ የሚያስከትለውን  ክፍተት ለመሙላት ያስችላል ያላቸውን አራት አማራጮች መንግሥት አቅርቧል። እኛ ስማችን በዚህ መግለጫ ግርጌ የተዘረዝርን የፖለቲካ ድርጅቶች በተፈጠረው የሕገ-መንግሥት ቀውስ እና መፍትሄ ሐሳቦች ተብለው የቀረቡትን  አማራጮች ገምግመን የሚከተለውን አቋም ይዘናል።
1. ሕገ-መንግሥቱ ሥልጣን በሕገ-መንግሥቱ መሠረት ብቻ መያዝ እንደሚቻል፣ ምርጫ በየአምስት ዓመቱ መደረግ እንዳለበት፣ የመንግሥት የሥራ ዘመን አምስት ዓመት ብቻ እንደሆነ በማያሻማ መንገድ አስቀምጧል። ምርጫ ቦርድ እንዳሳወቀው አሁን በሥራ ላይ ያለው  መንግሥት የሥራ ዘመን ከማብቃቱ በፊት ምርጫ ማካሄድ እንደማይቻል ስለገለጸ፣ ከመስከረም 30 በኋላ  ሀገርን ማሥተዳደር የሚያስችል  ሕጋዊ መሰረት ሊኖረው አይችልም።

Continue reading