Fincilli Diddaa Gabrummaa Itti Fufe!

Gabroomfataan Hamma Kufu Qabsoo Itti Fufna!!  FDG Itti Fufe!!

Odeessa Qeerroo Ebla 24,2011 ,Barattooti Oromoo University Arbaminc baratan Ebala 14,2011 irraa eegalee hanga har’aatti qabsoo FDG itti fufanii jiru,barattooti kun gaaffii mirgaa gaafataniif deebii kennuu kan hanqate mootummaan Orom-nyaataa Wayyaanee reebicha,doorsisa fi hidhaan addatti barattoota Oromootti duulee jiraachuun beekamaa dha. Mooraa University Arbaminci keessatti humni Federaala gaaffii barattootaa tasgabbeessuu dhadhabe jechuun dhihoo waraana Agaazii keessaa dhalootaan Tigroota kanneen tahan gara mooraa geessuun gootota barattooa Oromoo hidhaatti geessaa ture.Sanas tahu gaaffii barattoota Oromoo ukkaamsuu hin dandeenye.

Kun kanaan osoo jiruu kanneen ammaan dura hidhamanitti dabaluun barattoota Oromoo lama Ebla 21,2011 mooraa University Arbaminci keessaa human loltuun qabanii bakka buuteen isaanii wallalamee Jiru, kan akka barataa Xilaahun Fufaa Guutuu fi Barataa Tasfayee Dhaaba bakka jiran baruu qabna gaaffii jedhuun kan walqabate gaaffii motummaa Wayyaaneetti waan dhihaatee jiruuf,deebiin isaa ammos warra gaaffii kana gaafate keessaa barattoota hidhuu tahe.

Akka kanaan Ebla 23,2011 barattoota:-

  1. Waris-yoo Bantii Management waggaa 3ffa,
  2. Biqilaa abshaloo   Economics      ”          ” ,
  3. Dhugumaa Jabeessa Chemistry    ”          ”  ,
  4. Jamaraa Tolasaa      Physics         ”         ”  ,
  5. Biqilaa tasfayee        Irrigation       ”         ”  ,

Kanneen bakka buufaman dhabamuun qeerroon Oromootaa Unversity Arbaminci gabaasu.Kana malees magaalota Oromiyaa kan akka Dirree Dawaa,Adaamaa,Finfinnee,Ambo,Geedoo,Naqamte,Shaambu,Gimbii,Asallaa fi Jimma keessaa barattooti FDG gaggeesitan jechuun jidduu kana mana hidhaatti guuraman akka gabaasi qerrolee naannoo irraa nu qaqqabeen dabarsina.

Qabsoon itti fufa!gabroomfataan ni kufa!


የአዲስ አበባ አውደ አመት የገበያ ግርግር ተዳክሟል

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በኑሮ ውድነትና በብር የመግዛት አቅም መዳከም የተነሳ  ብዙዎች  ከበዓል ገበያው ይልቅ የዕለት ተዕለት ፍጆታቸውን መግዛት ላይ አተኩረዋል; በበዓል ጊዜ የሚታየው የ አውደ አመት የገበያ ግርግር ተዳክሟል።

ለወትሮው በኢትዮጵያ በፋሲካ በዓል አቅራቢያእና ዋዜማ የዶሮና እንቁላል፣ የበግና ፍየል፣ ለቅርጫ ሥጋ ክፍፍል የሚሆን የወይፈንእና በሬ፣ እንዲሁም የሽንኩርትና የዳቦ ዱቄት ግብይት ይደራ ነበር።

በዘንድሮው በዓል ግን በሸቀጦች ላይ የዋጋ ተመን ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ከገበያ የጠፉትን ዘይትና ስኳር በኮታ ለማግኘት በቀበሌ፣ በሸማቾች ማህበራትና በኢትፍሩት ኮንቴነር ሱቆች ላይ በጠራራ ፀሐይ ረጃጅም ሰልፎች ላይ ወረፋ ይዘው ሲጠብቁና ሲጨቃጨቁ ነው የሚታየው፡፡

ቀደም ሲል በሊትር 15 እና 16 ብር ሲሸጥ የነበረው የሀገር ውስጥ የኑግ ዘይት በአሁኑ ጊዜ ከገበያ የጠፋ ሲሆን በሊትር እስከ 45 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡ የዘይትን ዋጋ ለማረጋጋት ከውጭ የማስመጣቱን ተግባር ሙሉ ለሙሉ ከነጋዴዎች የነጠቀው የኢህአዴግ- መንግሥት የፓልም ዘይቶችን በማስመጣት በሊትር 24 ብር ከሃምሳ ሣንቲም በማከፋፈል ላይ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጂ ፓልም ዘይት በገበያ ውስጥ በሊትር እስከ 40 ብር  ለፋሲካ በዓል በጣም ተፈላጊ የሆነው  ሸኖ ለጋ ቂቤ በኪሎ በዓይነት ከ140 ብር እስከ 170 ብር ድረስ በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡ በአንፃሩ ሸኖ በሳል ቂቤ ደግሞ ከ120 ብር እስከ 150 ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል፡፡

Kormaa Indaanqoo

በመርካቶ ዶሮ ተራ የዶሮዎች ዋጋ ከ110 ጀምሮ የዋጋ ጥሪ የሚደረግበት ቢሆንም ከ80 ብር እስከ 100 ብር ድረስ በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡ በአንፃሩ የኤልፎራና መሰል የዶሮ እርባታ “ዲቃላ” ዶሮዎች ግን በ65 ብር፣ አንድ እንቁላልም በ1ብር ከ50 ሣንቲም እየተሸጠ ነው፡፡

በበግ ተራ አካባቢ አነስተኛ የተባለ ጠቦት  እንደ ውፍረቱ እና የትውልድ ቦታው ከ700 ብር እስከ 900 ብር ድረስ ሲሸጥ፣ መካከለኛ በግ 1350 ብር ድረስ ይገኛል፤ ሙክት  የፈለገ ሰው ግን ከ2000 ሺህ ብር በላይ በኪሱ መያዝ ይጠበቅበታል፡፡

ዘረኛው የትግራይ ገዢ ጉጂሌ ባለስልጣናት፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኦነግ አባል ናቺሁ በማለት በፓርላማ ምክር ቤት ለረጂም ጊዜ ሲሳተፉ የነበሩ የመድረክ አባላትን፣ ህዝባዊ አመጽ ለማነሳሳት ትቀሰቅሳላቺሁ በማለት በርካታ የሆኑ ወጣቶችን ፣ እንዲሁም የተለያዩና ፍጹም ከባለጉዳዩቹ ጋር ተያያዥነት የሌላቸውን ውንጀላዎች በመፈብረክ በርካታ ዜጎችን ወደ እስር ቤት እየወረወሩ እንደሆነ በስፋት ሲዘገብ መቆየቱ አይዘነጋም፣ ፣

ከዚህም በተጨማሪ የዘረኛውና አምባገነኑ አገዛዝ ቁንጮ የአንድነት ፓርቲ አባላትን ህዝባዊ አመጽ እንዲነሳ እየሰሩ ለመሆኑ መረጃዎች አሉን እናም ርምጃ እንወስድባቺሁአለን በማለት በምክር ቤት ተብየ ስብሰባ ላይ መዛቱ አይዘነጋም።

በአፈና፣ በጭቆና፣ በነጻነት ዕጦት፣ በሙስና የተዘፈቀ አሠራር፣ ሥራ አጥነት እና የጥቂቶች ተጠቃሚነት የአብዛኛዎቹ በአምባገነን የሚመሩ አገራት መገለጫዎች ናቸው።

የመለስ ዜናዊ የደህንነት ሰዎች በእስር ካሉ የኦህዴድ ባለሥልጣናት ከ165 ሚሊዮን ብር በላይ ወረሱ; አባዱላ ገመዳም ባለአራት ፎቅ ቤቱን ተነጠቀ

የኢህአዴግ መንግሥት የደህንነት ሰዎች በቅርቡ  በቡራዩ በአዲስ አበባ እና በዱከም ማረሚያ ቤቶች በእስር ላይ ካቆያቸው ከ60 በላይ የኦህዴድ ባለሥልጣናት የግል ካዝና ከ165 ሚሊዮን ብር በላይ መውረሳቸውን የዜና ምንጮቻችን ገለጹ፡፡  የሰበታ ከተማን ላለፉት ስምንት ዓመታት በከንቲባነት ያስተዳደሩት አቶ ሽመልስ ሀሰኖ፣ እንዲሁም ከሰበታ ከተማ ሰራ አስኪያጅ የነበሩ ግለሰብ እና  ከሌሎች በእስር ላይ ከሚገኙ ከሌሎች ባለስልጣናት ነው ገንዘቡ የተወሰደው።

አቶ ሽመልስ ሀሰኖ በቡራዩ ወህኒ ቤት ቆይታቸው የጠበቀ “ምርመራ” ተደርጎባቸዋል።አንድ የአዲስ ነገር ምንጭ  እንደተናገረው በእስር ላይ የሚገኙ አንዳንድ  የቀድሞ የኦህዴድ የበታች ባለስልጣናት  “ ከግርፋት ብዛት ባለፉት ሁለት ወራት የካዱትን የሙስና ወንጀል በማመን  ገንዘቡን ለመንግስት መልሰዋል” ብለዋል ፡፡

አሁንም “በሙስና የተጠረጠሩ” በርካታ የኦሮሚያ ክልል የወረዳ፣ የዞንና የክፍለ ከተማ የኦህዴድ- ኢህአዴግ ባለሥልጣናትና ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር በመዋል ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ገልጸውልናል፡፡

አቶ አባዱላ ገመዳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ኾነው በቆዩባቸው አምስት አመታት በክልሉ ተወዳጅነት ነበራቸው። ይህ በአቶ መለስ ዜናዊ  አልተወደደም። የአዲስ አበባ የፖለቲካ ታዛቢዎች አቶ አባዱላ  የምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴርነትን ቦታ እንደሚያገኙ ታስቦ የነበረ ቢኾንም አፈጉባኤ ተደርገው ከሚዲያ እይታ ገሸሽ እንዲሉ ተደርገዋል።

የኢህአዴግ/ህወሀት ሰዎች አቶ አባዱላን  በኦሮሚያ ክልል ውስጥ “ኔትዎርክ “ በመዘርጋት እና የተክለ ሰብእና ግንባታ/ከልት/ ይከሷቸዋል። ይህ ኦህዴድ ላይ ያነጣጠረው “የ ሙስና” ዘመቻ የአባዱላን ደጋፊዎች የመመንጠር ሥራ  አድርገው የሚወስዱትም አሉ። የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቀሳ እና የኦህዴድ ሊቀመንበር አቶ አለማየሁ አቶምሳ ምንጠራውን እና እስሩን እያስፈጸሙ ነው።

በሃብት ምዝበራው ወንጀል የተጠመደው ዘረኛው እና አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የአገዛዝ ዘመኑን ለማራዘም ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች በትናንሽ ጥቅማ ጥቅሞች እና መደለያ በዙሪያው ያሰባሰባቸውን አንዳንድ ግለሰቦች በተለያየ ውንጀላ የማስወገድ ተግባሩን እየገፋበት እንደሆነ በዚህም ምክንያት አባዱላ ገመዳ የወቅቱ ተረኛ እንደሆነ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቁ።

ለረጅም ጊዜ የኦሮሚያ ክልልና የኦህዴድ ፕሬዝዳንት በመሆን በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን የአጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ሲያስተገብር የቆየው አባ ዱላ ገመዳ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ከመለስ ዜናዊ ጋር በገባበት አለመግባባት ግልጽና ስውር ተጽዕኖዎች እየደረሰበት እንደሚገኝ ለግለሰቡ ቅርበት ያላቸው ምንጮች አረጋግጠዋል።

እንደ የኦሮሚያ አካባቢ ምንጮች መረጃ በአባዱላና በመለስ ዜናዊ መካከል የነበረውን አለመግባባት የተባባሰው ሸክ አላሙዲን በኦሮሚያ ክልሉ በስሙ ይዞት የነበረውን ሰፊ የልማት ቦታ ለረጅም ጊዜ ምንም የግንባታ ሥራ አልሰራበትም በማለት እንዲወረስ ካስደረገና በኦህዲድ ሥር የሚተዳደረው የድንሾ ንግድ ድርጅት በጫት ንግድ ገቢያ የነበረውን ድርሻ የመለስ ዜናዊ ባለቤት አዜብ መስፍን ለመቆጣጠር ጣልቃ ስትገባ ለማስቆም ከተፍጨረጨረ ቦኋላ እንደሆነ ለማወቅ ተችሎአል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከመለስ ዜናዊ በቀጥታ የሚተላለፈው ቀጭን ትዕዛዝ ክልላችንን ይጎዳል በማለት ቅሬታ ያሰሙ ከከፍተኛ አስከ ተራ የኦህዲድ አባላት ያሉ ግለሰቦች በሙስናና በኦነግ አባልነት ተወንጅለው ከርቼሌ እንደወረዱ በተለያየ ሚዲያ መዘገቡ ይታወሳል ። አባዱላ ገመዳ በትርፍነት ከተመራው የከተማ ቦታ አንዱን በቅርቡ ለድርጅቱ ኦህዲድ አውርሶ እንደነበረ የሚያስታውሱ ምንጮቻችን በተጨማሪ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ቦሌ ወሎ ሰፈር አካባቢ ያስገነባውን ባለ አራት ፎቅ መኖሪያ ቤቱን በሙስና ሰበብ መነጠቁን ገልጸዋል። የአባዱላ ጣጣ በዚህ ሳያበቃ ተጨማሪ ክስ በጸረሙስና ኮሚሽን በኩል ሊመሰረትበት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

አባዱላ ገመዳ በቅርቡ ለህክምና ሰበብ ወደ ጀርመን መጥቶ እንደነበርና ከመለስ ዜናዊ የሚደርስበትን ውርደት ለመሸሽ ጥገኝነት የመጠየቅ ሃሳብ እንደነበረው ነገር ግን በስደት ህይወት ውስጥ ያለውን ውጣ ውረድ የመቋቋም ፍርሃት ገብቶት ሃሳቡን እንደቀየረና በመጣበት እግሩ እንደተመለሰ ተያይዞ የደረሰን መረጃ አረጋግጦአል።

ለመለስ ዜናዊ ባላቸው ታማኝነት ብቻ ዕውቀት እና ችሎታቸው በማይመጥናቸው የስልጣን ማማ ላይ ከተፈናጠጡት የጄሌ ድርጅቶች መሪዎች መካከል ከመለስ ዜናዊ የሚደርስባቸውን ውርደት ለማስቆም የምቾት ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡ ብዙ አይደሉም። የቤንሻንጉል እና ጉሙዝ ክልል ፕሬዝዳንት የነበረው ያረጋል አይሸሹም ከሁለት አመት በፊት በስደት ካናዳ ከደረሰ ቦኋላ ወዲያው ተጸጽቶ ይቅርታ በመጠየቅ ለመለስ ዜናዊ መልሶ እጁን እንደሰጠ ይታወሳል።

የመለስ ዜናዊ አገዛዝ የኢንተርነት ግንኙነቶችን ሳንሱር በማድረግ ላይ ነው

የወያኔ አገዛዝ መሰረታዊ የሆነ በኢንተርነት መረጃ የማግኘት ነጻነትን  በመገደብ ከሳራ በታች ካሉት አገሮች ብቸኛ እንደሆነ ተቀማጭነቱ በአሜሪካን አገር በዋሽንግተን ዲስ የሆነው እና በዲሞክራሲ፤ በፖለቲካ ነጻነትና የሰብዓዊ መብትቶች ዙሪያ ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ ምርምር የሚያደርግ ፍሪደም ሃውስ ሰሞኑን ባወጣው አመታዊ ሪፖርት ከሰሰ።

እንደፊሪደም ሃውስ ሪፖርት 85 ሚሊዮን የሚገመት ህዝብ በሚኖርባት ኢትዮጵያ የኢንተርነት ስርጭት ከዜሮ ነጥብ አምስት በታች ላይ የሚገኝ ነው። በዚህ ከቁጥር በማይገባ ስርጭ ላይ አገዛዙ የኢንተርነት ግንኙነቶችን ሳንሱር በማድረግ እና የፖለቲካ ክርክሮች፤ ውይይቶች ወይም አስተያየቶች የሚካሄዱባቸውን ድህረ ገጾች ጨርሶኑ በአገር ውስጥ እንዳይታዩ የመዝጋት የአፈና እርምጃ ይወሰዳል።

በኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒከሸን አገልግሎት እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ድርሻ ያላት ቻይና፤ አገዛዙ ኢንተርኔትንና የሳታላይት ሞገዶችን ለመጥለፍ በሚያካሂደው ዘመቻ ዘመናዊ መሳሪያዎችን በማቀበል ብቸኛዋ ተባባሪ አገር እንደሆነች ሪፖርቱ አክሎ አጋልጦአል።

የአለም አቀፍ ቴሌኮሚኒኬሽን ድርጅት ባለፈው አመት ባካሄደው አለም አቀፍ ጥናት በኢትይጵያ ውስጥ ለኢንተርነት አገልግሎት የሚከፈለው ዋጋ ከዜጎች ወርሃዊ ገቢ ጋር ሲነፃጸር በአለም እጅግ ውድ ከሚባሉት ተርታ ይገኛል ያለው የፍሪደም ሃውስ ሪፖርት የዋጋውን ንረት በንፅጽር ለማሳየት ከፍተኛ የመረጋጋት ችግር ካለባቸው የመካከለኛው አፍሪካ አገሮች ተርታ እንደሚገኝ ገልጾ መንግሥት አልባ የሆነቺው ሱማሌ፤ ጎሬቤት አገር ጁቡቲ ፤ ኬንያና ሱዳን ከአገራችን በተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ከዘገባው መረዳት ተችሎአል።

እንግሊዝ አገር የሚገኘው የማንቺስተር ዩኒቨርሲት የትምህርት ክፍል ባለፈው የፈረንጆች አመት 2010 ባካሄደው ጥናት በአዲስ አበባ ውስጥ ብሮድ ባንድ በሚባለው የኢንቴርነት አገልግሎት አንድ ሰው የኢሜል መልዕክቱን ከፍቶ ለማዬት ከ6 ደቂቃ በላይ ጊዜ እንደሚፈጅበት ገልጾ የኢንተርኔት ፍጥነት እንዲህ እንዲዘገይ የሚደረገው ሆን ተብሎ አንደሆነ አጋልጦአል።

አገዛዙ ሊደርስባቸው በማይችልባቸው የውጪ አገሮች የሚኖሩ የዲያስፖራው ኮሚኒቲ ስለአገራቸው ፖለቲካ ጉዳይ የሚለዋወጡትን አስተያየቶች አቅጣጫ ለማሳት እና ለመንግሥታቸው እጅግ ቀናና በጎ የሆኑትን አስተያየቶች በምላሽ መልክ ለመስጠት በቋሚነት የሚሠሩ ደመወዝ የሚከፈላቸው ሰዎች መመደባቸውን ፍሪደም ሃውስ መረጃ እንዳለው በ2010 አመታዊ ሪፖርቱ አክሎ ገልጾአል።

የወያኔ አገዛዝ በኢንቴርኔት አማካኝነት የሚተላለፉ ማናቸውንም አይነት ይዜት ያላቸው በድምጽ እና በቪዲዮ የሚተላለፉ መልዕክቶችን ሁሉ እንደዘጋ ያጋለጠው ይህ የፍሪደም ሃውስ አመታዊ ሪፖርት ከውጪ ወደ አገር ቤት የሚተላለፉ ሬዲዮኖችን በሙሉ እንደሚያፍን ለዚሁም መለስ ዜናዊ የአሜሪካ ድምጽ የአማሪኛ አገልግሎትን ለማፈን እንደተዘጋጀ በአደባባይ የሰጠውን የራሱ ቃል በማስረጃነት አቅርቦአል።

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ፖለቲካ አስመልክቶ የኦሮሞ ወጣቶች ንቅናቄ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ መግለጫ አወጣ ::

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ፖለቲካ አስመልክቶ የኦሮሞ ወጣቶች ንቅናቄ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ  መግለጫ አወጣ ::

የኦሮሞ ወጣቶች ንቅናቄ በመባል የሚታወቀው ድርጅት ነፃነትና ዲሞክራሲ  በኢትዮጵያ ይሰፍናል!’ በሚል ርዕስ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ በቱኒዚያ፡ በግብፅና  በሌሎችም በመካከለኛዉ ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪቃ በመካሄድ ላይ ያሉት የህዝብ  አመጾች በተመሳሳይ ጭቆና ሥር ላሉ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ የአለም ክፍሎች  አርዓያነት ያለው መልዕክት መስተላለፉን ገልጿል።  በኢትዮጵያ ለሚታየዉ የለዉጥ ፍላጎት መነሳሳት እነዚሁ የሕዝብ አመጾች ምክንያት  እንደሆኑና ወቅቱ የአምባገነንና የፈላጭ ቆራጭ የፖለቲካ ስርኣቶች ተወግደዉ  ዲሞክራሲያዊና የህዝቦች ሉኣላዊነት  የሚሰፍንበት እንደሆነ አመልክቷል።  በኢትዮጵያ ለሚቀጣጠለዉ አመፅ መሰረታዊ ምክንያት የሚሆኑትና የሚያጎለብቱት  የሚያደርጉት በአገሪቱ ዉስጥ የሚታዩት ሁኔታዎች እንደሆኑ በመግለጫዉ  ተጠቅሷል። በመሆኑም ይላል መግለጫዉ “እኛ የኦሮሞና የሌሎችም ጭቁን ሕዝቦች ተማሪዎች የህዝባዊ አመፁን ለመለኮስ የመጀመሪያዎቹ ለመሆን ቁርጠኝነት እንዳለን  ለአለምና ለኢትዮጵያ ህዝብ እናረጋግጣለን። በባርነት ከመኖር በነፃነት መሞትን  መርጠናል የሚለዉ መግለጫ “‘ ስቃይና ባርነቱ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አሁኑኑ  እንዲወገድና ነፃነትና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ያቀጣጠልነዉን ችቦ ቀሪዉ የኢትዮጵያ  ህዝብ ይዞ እንደሚከተለን አምነት አለን”‘ የሚለዉ መግለጫ ሰባት ንጥቦችን አስቀምጧል።

1. የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በስታሊናዊ ድርጅታዊ መዋቅሩም ሆነ  በሚያራምዳቸዉ ማህበራዊና ፖለቲካዊ አጀንዳዎች  በጠባብ ጎሰኝነት ላይ  የተመሰረተ፡ በአገሪቱ ዘረጋሁ የሚለዉ የፌዴራል መዋቅር ለከፋፍለህ ግዛዉ  አላማዉ ካልሆነ በስተቀር ምንም ትርጉም የሌለዉ፡ የኦሮሞ፡ የኦጋዴን፡ የሲዳማ  እና የሌሎችንም የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች በዋና ጠላትነት ያነጣጠረ  መሆኑን  በመግለፅ… ላለፉት 20′ አመታት በኦሮሞ፡ በኦጋዴንና በሌሎችም ጭቆና  ላለፉት 20′ አመታት በኦሮሞ፡ በኦጋዴንና በሌሎችም ጭቆና  በበዘባቸዉ አካባቢዎች የሚገኙ ህዝቦች የሚያነሱትን ጥያቄ በሃይልና በህገ ወጥ  መንገድ ለማፈን የሚደረገዉ ወታደራዊ ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲቆም

2.  መለስ ዜናዊ በስልጣን ላይ ላለፉት 20′ አመታት በአፈናና በጭቆና የቆዩ  ከመሆኑም በላይ አገዛዙ የህዝብን ሰብኣዊ መብት በመርገጥ፡ በማንገላታት፡  በማፈናቀል፡ በማሰቃየት፡ በማሰር፡ በመግረፍና  በመግደል በአስር ሺዎች የሚቆጠሩትን በየእስር ቤቱ የህሊና እስረኛ አድርጓቸዋል። ስለሆነም የፖለቲካ  ስለሆነም የፖለቲካ  እስረኞችበአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ  እንዲፈቱ፡ በተለይም የሰዉ ልጅን  በመግረፍና በመደብደብ      ለማሰቃየት የተቋቋመዉ ማዕከላዊ የምርመራ  ድርጅት በአስቸኳይ እንዲፈርስና እስከመጨረሻዉ እንዲዘጋ

3.   የመለስ ዜናዊ መንግስት የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግቤአለሁ ይበል እንጂ በህዝቡ  ኑሮ ላይ አንዳችም ለዉጥ እንደሌለ መንግስት በሚከተለዉ የተዛባ የኢኮኖሚ  ፖሊሲ ምክንያት ይልቁንም በሽታ፡ ድንቁርና፡ እና ረሃብ የህዝቡ ማህበራዊ  ህይወት መለያ ምልክት ሆኗል። ስለሆነም መሰረታዊ የሆኑ የፍጆታ እቃዎች  ስለሆነም መሰረታዊ የሆኑ የፍጆታ እቃዎች  ስኳር፡ ዘይት እና ዳቦ የመሳሰሉትን መንግስት በአስቸኳይ ለህዝብ እንዲያቀርብና  የተሳሳቱትን የገበያና የኢኮኖሚ ፖሊሲዎቹን እንዲያስተካክል

4.   የመለስ ዜናዊ አገዛዝ እጁን ያላስገባበት እንዳለመኖሩ በተለይም በኢኮኖሚዉ  ዘርፍ ባለቤታቸዉ ወ/ሮ አዜብ መስፍን የሚቆጣጠሩት ኤፈርት በሚል  የሚታወቀዉ የህወሃት የንግድ ድርጅት እንደሆነ ከህዝብ የተሰወረ አይደለም።

በመሆኑም በመለስ ዜናዊ ቤተሰብ ስም የሚገኘዉ ንብረት እንዲወረስና  በቤተሰባቸዉና በቅርብ አጋሮቻቸቸዉ  የተፈፀሙ የሙስና ተግባሮች እንዲመራመሩ;;

5. ከ90′ በመቶ በላይ የሚሆነዉ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ህይወት የተመሰረተዉ በግብርና ላይ ሲሆን በ1960ዎቹና በ70ዎቹ መጀመሪያ ላይ የተነሳዉና በ1974′ አብዮት እልባት ያገኘዉ የመሬት ላራሹ ጥያቄ የንጉስ ሃይለ ስላሴን አገዛዝ  ከስልጣን ያስወገደ፡ ሕዝብን በፖለቲካ ዙሪያ ያስተበበረ እንደነበር ይታወሳል።  ይሁን እንጂ የሕወሃት አገዛዝ ዳግመኛ ወደ ነበርንበት ለመመለስ የሚከተለዉ  መሬትን በገፍ ለዉጭ ባለሃብቶች የመስጠት ፖሊሲ ሕዝባችንን ከመሬቱ  የሚያፈናቅለዉ፡ ባለቤትነት የሚያሳጣዉ፡ ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች የሚያገልለዉ፡ ስራ አጥነት የሚያሰከትልና ዘመናዊ ባርነት ዉስጥ የሚጥል በመሆኑ፡ ይህ ፖሊሲ ባስቸኳይ እንዲቆምና እስከዛሬ የተደረጉት አለም አቀፍ  ይህ ፖሊሲ ባስቸኳይ እንዲቆምና እስከዛሬ የተደረጉት አለም አቀፍ ስምምነቶች ዋጋ እንደሌላቸዉ ተቆጥረዉ እንዲሰረዙ  ስምምነቶች ዋጋ እንደሌላቸዉ ተቆጥረዉ እንዲሰረዙ

6. ኢትዮጵያ ባለፉት 20′ አመታት እጅግ አስከፊ ወደ ሆነ ሁኔታ ዉስጥ በመግባት  ላይ የምትገኝ ሲሆን በህግ አዉጪዉ፡ በሕግ አስተርጓሚዉና በህግ አስፈፃሚዉ  መካከል ምንም አይነት የስልጣን ክፍፍል የማይታይበት፡ በስታሊናዊ መንግስት  እንደሚታየዉ ሁሉ ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ በህዝብ ሳይመረጡ እራሳቸዉ  ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ በህዝብ ሳይመረጡ እራሳቸዉ  በፈጠሩት መዋቅር አማካይነት ስልጣኑን ሁሉ በብቸኝነት የሚቆጣጠሩ በመሆኑ  ስልጣናቸዉን በአስቸኳይ እንዲለቁ  ስልጣናቸዉን በአስቸኳይ እንዲለቁ

7. ከ90′ የማያንሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በህግ ተመዝግበዉ  በሚንቀሳቀሱበት አገር ባለፈዉ ግንቦት 2010′ በ99.6′ በመቶ ድምፅ ህወሃት/’ ኢህአዴግ አሸነፍኩ የሚለዉ ምርጫ ተቀባይነት የሌለዉ፡ የምርጫ ቦርዱ  የመንግሰት ሌላ እጅ በመሆኑ፡ የአገሪቱ ሀብትና ንብረት፡ የመገናኛ ብዙሃን፡ የፌዴራል ፖሊስና የፀጥታ ሃይሎች የገዢዉ ፓርቲ መሳሪያ በሆኑበት የተካሄደ፡

በዚህ ምክንያት ምርጫዉ የተጭበረበረና አሳፋሪ በመሆኑ ሁለቱም ምክር ቤቶች  ምርጫዉ የተጭበረበረና አሳፋሪ በመሆኑ ሁለቱም ምክር ቤቶች በአስቸኳይ እንዲበተኑ፡ ከሁሉም የነፃነት ንቅናቄዎችና ለማህበራዊ ፍትህና ለዲሞክራሲ የቆሙ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ተሳታፊ የሚሆኑበት የሽግግር  መንግስት እንዲመሰረት  መንግስት እንዲመሰረት ብሄራዊ የኦሮሞ ወጣቶች ንቅናቄ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ  ባወጣ የአቋም መግለጫ ጠይቋል።

More:-  http://ginbot7.com/News_Paper/Ginbot_7_Dimts_Issue_No153.pdf