በኢትዮጵያ ላይ የተጫነው ግፈኛና ዘረኛ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያዊያን ትከሻ ላይ ተሽቀንጥሮ ይውድቅ ዘንድ ግፊቱና ህዝብንም ለዚሁ ትግል የማያነሳሳ ጥሪ መቅረቡ ተጡዋጡፎ እንደሚገኝ ተገልጹአል::
በአዲስ አበባና በሌሎች የኦሮሚያ ዋና ከተሞች የተበተኑ ጥሪ ወረቀቶች ህዝብ ለነጻነቱ ሲል ወያኔ እያደረሰ ያለውን የጥፋት ተልዕኮ ለማስቆም ሆ ብሎ መነሳት ያለበት ጊዜው አሁን መሆኑን የሚያመለክት ነው ተብሎአል።
ከተበተኑት ጽሁፎች ውስጥ አባይ ወንዝን በላያችን ላይ ያለውን የአምባገነንነት ቀምበር ካስወገድን በሁአላ እንሰራዋለን የሚል እንደሚገኝበት ተገልጹአል::
ከበርካታ ቀናት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተለያዩ ቀስቃሽ ወረቀቶች በየግድግዳው እንደሚለጠፉና ሲበተኑም እንደነበር በተደጋጋሚ የተዘገበ ሲሆን ሰሞኑን ደግሞ በቃ የሚሉ ጽሁፎ በየመንገዱ ተበትነው እንደሚገኙ ተገልጹአል::
ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በተለይም የሰሜን አፍሪቃው ህዝባዊ አብዮት ከተቀሰቀሰ ወዲህ በሃገር ውስጥ ያለው እንቅስቃሴ እጂግ እያስፈራውና እያስጨነቀው እንደመጣ ሲዘገብ ከዚህ ጭንቀት መውጫ መንገድ አድርጎ እየወሰደ ያለው ርምጃም ንጹሃን ዜጎችን በጂምላ ወደ እስር ቤት ማጎር እንደሆነ በርካታ የዜና አውታሮች የዘገቡት መሆኑ ይታወቃል::
ባለፈው አንድ ወር ውስጥ የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ በጅምላ ካሰራቸው እና ለጊዜው ቁጥራቸው ከታወቁት 200 በላይ የኦሮሞ እስረኞች ውስጥ አንድ መቶ ሃያ አንዶቹ በሽብርተኝነት ክስ ሊመሰረትባቸው እንደሆነ መለስ ዜናዊ መጋቢት 27 በራሱ አምሳል ጠፍጥፎ ለሰራው ፓርላማ ተብዬ ሸንጎ ንግግር ባደረገበት ወቅት በሰላማዊ ትግል የፖለቲካ አላማቸውን እውን ማድረግ እንችላለን ብለው በይፋ የሚንቀሳቀሱትን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለማስፈራራት በግፍ የታሰሩት አባላቶቻቸው ሽብር ለማካሄድ የሚንቀሳቀሱ ናቸው በማለት እንደወነጀላቸው ይታወቃል።
በራሪ ወረቀት በከተማ ውስጥ የመበተኑ ሥራ ተፋፉሞ በመቀጠል ሰሞኑን በአዲስ አበባ፤ በአዋሳ፤ በኮምቦልቻ፤ በአርባምንጭ፤ በደሴ፤ በድሬደዋ እና ሌሎች ከተሞች እየተበተነ እንደሆነ ለማረጋገጥ ተችሎአል።ከስድስት ኪሎ ወደ ጊዮርጊስ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የሃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ (አፍንጮ በር ድልድይ) ላይ ሞት ለወያኔ የሚል ጽሁፍ በትላልቅ ፊደላት ተጽፈው እንደነበር ይታወሳል ፣፡

