(Qeerroo News, Nov 5, 20110) የመለስ ወያኔ አገዛዝ የእስር ጥቃቱን በዋነኛነት በኦሮሞ፣ ኦጋዴንና አማራ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እነዲሁም ተወላጆች ላይ ለሁለተኛ ዙር ሊያካሄድ ዝግጅቱን ያጠናቀቀው መሆኑ ታውቅዋል።
ይህ እቅድ ወያኔ ከሀምሌ ወር 2011 ጀምሮ እየተገበራቸው ካሉት ግዙፍ እኩይ ድርጊቶች ኢምንቱ እነደሆነ የታወቀ ሲሆን ይህም ሀገር ውስጥ የሚገኙ የተቃዋሚ ሀይላትን ከሀገር ጠራርጎ የማውጠት አላማን የተንተራሰ ዘዴ ነው።
መለስ ዜናዊ በቅርቡ በፓርላማ ስብሰባው ላይ በሰጠው መግለጫ መንግስት በርካታ ዜጎች ላይ እስር ለመፈፀም መረጃ እየሰበሰበ እነደሆነ በግልፅ ተናግርዋል፣« ከአሸባሪ ቡድኖች ጋር እየሰሩ ያሉና ግንኙነት ያላቸው ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን፣ ከማሰራችን በፊት ጥቂት ተጨማሪ ማስረጃዎችን ብቻ ነው የምንፈልገው ፣በመቻኮል ሁሉንም ነገር ማበላሸት አንፈልግም» ነበር ያለው።
ይህ ቀጣዮ የጅምላ እስር እቅድ ያነጣጠረው ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ እነዲሁም መረጃን በማቀበል ይሰራሉ ብሎ የጠረጠራቸውን በመንግስት መስራቤቶች ውስት ተቀጥረው የሚሰሩ ሰዎችንና አገዛዙን የሚነፍቁ የመገናኛ ብዙሀኖችንም እነደሚያካትት ታውቅዋል።
የወያኔ አገዛዝ እነኚህን አካላት በትሮጃን ሆርስ ቫይረስ ነው የመሰላቸው፣ የወያኔን አገዛዝ ስራ በማጋለጥ ውድቀቱን የሚያፋጥኑ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ወያኔ በፍትህ ሚኒስተር መስሪያ ቤት አንድ ግብረ አበር ቡድን ያቋቋመ ሲሆን አላማውም በፍትህ መኒስቴር መስሪያቤት ውስጥ በፖለቲካ እስረኞች ላይ የሚደርሰውን ኢሰብአዊ ድርጊትና ስልጣንን በመጠቀም የሚፈፀመውን ወንጀል በተመለከተ ለዜና አውታሮች መረጃዎችን የሚያቀብሉ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ነው።
የውስጥ ምንጮች እንደገለፁት ይሄው ቡድን በዋነኛነት በኦሮሞ የህግ ኤክስፐርቶች ላይ እነዲሁም በአሁኑ ወቅት ወደአሜሪካ ተሰደው የሚገኙት ከዚህ ቀደም የፍትህ ሚኒስተር ዳየሬክተር የነበሩትን የአቶ ለገሰ አለሙ ጉዋደኞች ላይ ያነጣጠረ ነው፣ ይህ ቡድን እነዢህን ግለሰቦች መረጃውን ለዜና አውታሮች ወይም ደግሞ ለአቶ ለገሰ ስለማቀበላቸው በምርመራ መልክ መጠየቃቸውም ታውቅዋል።
ከዚህም ባለፈ “አቶ ለገሰ በኢትዮጵያ መንግስት በጥብቅ የሚፈለግ ግለሰብ ነው፣ ግለሰቡ እጃችን ሲገባ በዚህ ተግባር ከተሳተፋችሁ ለክህደታችሁ ከፍላችሁ የማትጨረሱት እዳ ነው የሚከተላችሁ” የሚል ማስፈራሪያ ከባለስልጣናቱ እንደደረሰባቸውም ገልፀዋል።
ወያኔ ይህን ግብረአበር ቡድን ለማቋቋም የተገደደው ከ ፍትህ ሚነሲተር በተደጋጋሚ ወጥተው በተለያዩ የዜና አውታሮች በታተሙት ሚስጢራዊ ዜናዎች ሲሆን ይህም በኦሮሞዎችና ሌሎችም ግለሰቦች ላይ የሀሰት ክስ በመመስረትና ለእስር በመዳረግ እነዲሁም ቶርች በማድረግ ትልቅ ሚና ሲጫወቱ የነበሩ የወያኔ አባለትን ያጋለጠ በመሆኑ ነው።
ሆኖም የወያኔ ጋዜጠኞች ሰሞኑን የቄሮ ዘገባን ለማስተባበል አስበዉ ሳይሳካላቸዉ የቀረ መሆኑ ተስተዉሏል::