ቀን ፡ – 12/07/2012 ዓ. ም
Ref No. /ቁጥር ፡ – 59/03/20

HRLHAለክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ፡
የኢ.ፈ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስቴር እና የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ፡
አዲስ አበባ፡
ጉዳዩ፦ በዋናነት በምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ አከባቢዎቸ ስላለው የሰብዓዊ መብቶች
አያያዝን ይመለከታል።

ክቡር ጠ/ሚኒስትር፤
በመጀመሪያ በሃላፍነት በሚመራው የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ (The Human Rights
League of the Horn of Africa- HRLHA) ድርጅት ሥም የከበረ ሠላምምታዬ ይድረስዎ።
ይህንን ዴብዳቤ ልፅፍልዎ የወደድኩት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በአጠቃላይ በተለይ ደግሞ
በምዕራብ እና በደቡብ ኦሮሚያ ዞኖች ውስጥ ስለሚታየዉ የሰቢአዊ መብቶች አያያዝ አሳሳብነት
መሰረት በማድረግ ነው።
ክቡር ጠ/ሚኒስትር፤
ክቡርነትዎ እንደምገነዘቡት፤ የኢትዮጵያ ህዝቦች እና ብሔር ብሐረሰቦች ለአመታት ባደረጉት እልህ
አስጨራሽ ትግሎች በሀገሪቱ ወስጥ ለዘመናት ተንሰራፍቶ የቆየዉን ኢ-ሰብዓዊነት እና ኢዲሞክራሳዊ የሰፈነበትን ሥርዓቶችን በማስወገድ ለዉጦቸን አስመዝግበዋል፡፡
ባለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ኢትዮጵያን ስመራ የነበረው የኢህአዲግ መንግሥት ከፍተኛ
የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እና በደል ስፈፅም የነበረዉን ከባድ መስዋዕት ከፍሎ ማስወገዱ ከማንም
የተደበቀ አይደለም። የኢህአዲግ የግፍ አገዛዝ ያንገሸገሸው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጫፍ እስከ ጫፍ
መብቱ እና ሉዓላዊነቱ እንድከበርለት ከፍተኛ ተጋድሎ አድርጓል። በተለይ ከ2006 ዓ.ም ወዲህ
የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ
The Human Rights League of the Horn of Africa (HRLHA)
http://www.humanrightsleague.org
______________________________________________________________________________
2
በኦሮሚያ እና በለሎቸ ክልሎቸ በተደረጉት ህዝባዊ እምብተኛነቶች ከፍተኛ መስዋዕት ተከፍሎበታል።
እርስዎን ጨምሮ የለውጥ ሃይል በኢህአዲግ ውስጥ እንዲፈጠር ምክንያት የሆነዉ ይሄው የህዝብ
ትግል እንደሆነ እሙን ነው።
ክቡር ጠ/ሚኒስትር፤
እርስዎ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው ከተሾሙበት ግንቦት 2010 ዓ.ም ጀምሮ በነበሩት
ተከታታይ ወራት ህዝብ ለዘመናት ጥያቄ ስያነሳባቸው የነበሩት በርካታ ኢ-ፍትህዊ የነበሩ ፣ የሕግ
እና የፍትሕ ማሻሻዎች ላይ ለውጦች ተደርገዋል። በተለይ ኢትዮጵያ ከጎረበት አገር ኤርትሪያ ጋር
የነበራትን ቅራኔ ለመፍታት የወሰዱትን እርምጃ እና ለዚህ ጥረትዎ የ2019 (እአአ) የአለም የሠላም
ሎረት ለመሆን ስለበቁ በዚህ አጋጣሚ በአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ ሥም ያለኝን አድናቆት
ልገልፅልዎ እወዳለሁ።
የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ ከተመሠረተበት 2007 እአአ ጀምሮ ስሰራበት ከነበረው ካናዳ
አገር ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የወሰነውም በመጀመሪያ ወራት የታየውን የለውጥ ሂደት ውስጥ
የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዓላማ አንግቦ ነው። በዚህም መሠረት፡ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ሲቪል
ሰርቪስ ኢጀንሲ ተመዝገቦ ህጋዊ ሰውነት ከተጎናፀፈበት ጊዜ አንስቶ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብዓዊ
መብቶች እንዲከበሩ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።
ክቡር ጠ/ሚኒስትር፤
ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ እርስዎ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሃላፍነት
በተረከቡበት ዕለት በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ፍት ቆመው ካደረጉት ንግግር እና ከዚያ ወዲህ
በተከታታይ ባደረጓቸው ንግግሮች እንዲሁም ከወሰዷቸው አበረታች እርምጃዎች ጋር ፈፅሞ
የሚቃረን ነው። በተለይ ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ዉስጥ በምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ (አራቱ
የወለጋ ዞኖች፣ ሁለቱ የጉጂ ዞኖች እና ቦራና ዞን) በየዕለቱ እየተፈፀመ ያለው የሰብዓዊ መብቶች
ጥሰት እና በደል አሳሳብ ደረጃ ላይ ደርሷል። እነዚህ አከባቢዎች ኦፍሰላዊ ባልሆነው የአስቸኳይ ጊዜ
አስተዳደር ወይም በተለምዶ “ኮማንድ ፖስት” በሚባለው ወታደራዊ አስተዳደር ሥር
እንዲተዳደሩ ተደርጓል። በዚህ ምክንያት ዘጎች በሠላሙ ጊዜ ይከበርላቸው የነበረውን መሠረታዊ
ሰብዓዊ መብቶቻቸውን ተነፍገው ይህ ነው ለማይባል የመብት ጥሰት ተጋልጧል። በሕገ
የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ
The Human Rights League of the Horn of Africa (HRLHA)
http://www.humanrightsleague.org
______________________________________________________________________________
3
መንግሥቱ የተደነገገላቸውና ኢትዮጵያ ፈርማ ባጸደቀቻቸው አህጉር እና ዓለም አቀፋዊ ውሎች
የተደነገጉትን እና በማንኛውም ሁኔታ ገደብ ሊጣልባችተው የማይገቡ በህይወት የመኖር መብት፣
ከኢሰብዓዊ እና አስከፍ አያያዝ ነጻ የመሆን እና የመሳሰሉ መሠረታዊ መብቶቻቸው በአያሌው
ተጥሰው ይገኛሉ።
ክቡር ጠ/ሚኒስትር፤
በአሁኑ ጊዜ በመላው ኦሮሚያ ክልል፡ በዋናነት ደግሞ በ“ኮማንድ ፖስት” ሥር በሚተዳደሩት
ዞኖች ውስጥ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታን በሚመለከት አገር አቀፍም ሆኑ አለም አቀፍ
ሚዲያዎች እንዲሁም የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች በሠፍው በመዘገብ ላይ ይገኛሉ።
የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግም ቢሆን ያለውን ሁኔታ ከመነሻው ጀምሮ በመከታተል ላይ
የሚገኝ ሲሆን መንግሥት ከሃይል እርምጃ እንድቆጠብ፣ ግጭቶች በሠላማዊ መንገድ እንድፈቱ እና
ተጠያቂነት እንዲሰፍን ለሚመለከታቸው የፌዴራል እና ክልል መንግሥት አካላት በተለያየ ጊዜ
በደብዳቤ የተደገፈ ሀሳብ ያቀረበ ቢሆንም ሰሚ ጆሮ አላገኘም። በመሆኑም፡ በክትትል ሂዴት
ያሰባሰብናቸውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት መረጃዎችን እና ማስረጃዎችን በማደራጀት በተለያየ
ወቅት በርካታ ሪፖሪቶችን ይፋ አድርገናል።
ክቡር ጠ/ሚኒስትር፤

የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ በየካትት 21 ቀን 2012 ዓ.ም በኦሮሚያ ውስጥ ያለዉን
የሰብዓዊ መብቶች አያያዝን በሚመለከት ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያሳተፈ ህዝባዊ ምክክር
በፊንፊኔ ከተማ አዘጋጅቶ ነበር። በምክክሩ ወቅት የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ሰለባ የሆኑ ሰዎች፣
ቤቴሰቦቻቸው ኢንዲሁም የፖለትካ ፓርቲ ተወካዮች በመላው ኦሮሚያ በተለይ ደግሞ በምዕራብ
እና ደቡብ ኦሮሚያ ዞኖች ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ አፅዕኖት ሰጥቶበት ተወያይ ተዋል።
ከተነሱት ቅሬታዎች መካከል፡ ‘ሠላማዊ ሰዎች በመንግስት ወታደሮች እንደሚገደሉ፤ እናቶችና
ልጃገረዶች እንደሚደፈሩ፤ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለጅምላ እሥራት እንደሚዳረጉ፤ የታሠሩት ሰዎች
ሕግ በሚጠይቀው ጌዜ ውስጥ ፍ/ቤት እንደማይቀርቡ፤ በርካታ ሰዎች ተገደው እንደተሰወሩ እና
ያሉበት እንደማይታወቅ፤ ዘጎች መደበኛ ባልሆኑ እና ፖሊስ ጣቢያዎች (የወታደር ማሠልጠኛ
የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ
The Human Rights League of the Horn of Africa (HRLHA)
http://www.humanrightsleague.org
______________________________________________________________________________
4
ካምፖችን ጨምሮ) ውስጥ ታጉሮ ለከፍተኛ የአካል እና ሥነ ልቦና ጉዳት እየተዳረጉ እንደሆነ፤ ዜጎች
በነጻ የመዘዋወርና የመሰብሰብ መብታቸው በከፍተኛ ደረጃ መገደቡን፤ አርሶ አደሮች በባሕላዊ ደቦ
መሠረት ባንድ ላይ ሆነው ተረዳድተው ሰብላቸውን መሰብሰብ አለመቻላቸውን፤ ነዋርዎች ሠርግ፣
ለቅሶ እና መሰል ማህባራዊ ግንኙነቶችን በነጻንት መከወን አለመቻላቸውን፤ የፖለትካ ፓርትዎች እና
አባሎቻቸው በሠላም ተንቀሳቅሰው አቋማቸውን እንዳያራሚዱ በመንግሥት ፀጥታ አካላት ከፍተኛ
ጫና እንደሚደርስባቸው እና መሰል በደሎች ይገኙበታል።’
በተለይ ‘በምዕራብ ኦሮሚያ የስልክ አገልግሎት በከፍል እና እንቴርነት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ
ለወራት ተቋርጦ የሚገኝ ከመሆኑ የተነሳ የአከባብው ህብረተሰብ ለከፍተኛ ማህበራዊ እና
ኢኮኖሚያዊ ቀውስ መዳረጉን፤ ይህንን እና ሌሎች በእነዚ አከባቢዎች የሚፈፅሙ የሰብዓዊ በብቶች
ጥሰትን አስመልክቶ ቅሬታቸውን በሠላማዊ መንገድ ያሰሙትና ለሎች፣ የብዙ የዩኒቬርሲቲ ኦሮሞ
ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው የተባረሩ ሲሆን በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖባቸው ወደ
ትውልድ ሰፈራቸው እንኳ መመለስ አቅቷቸው በአዲስ አበባና ሌሎች ትላልቅ ከተሞች ለጎዳና
ተዳዳሪነት ተዳርገው እደሚገኙ’ ተገልጿል።
ክቡር ጠ/ሚኒስትር፤
በአሁኑ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) አለምን እያስጨነቀ ባለበት ወቅት እና ቫይረሱ ኢትዮጵያ
ውስጥ መግባቱን ተከትሎ እርስዎም ቢሆኑ ህብረተሰቡ ማድረግ ያለበትን ጥንቃቄ ማሳሰቢያ
እየሰጡ ባሉበት ሁኔታ በተጠቀሱት የምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች የስልክ እና እንቴርነት አገልግሎቶችን
ዘግቶ መቆየቱ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሚሆን ግልፅ ነው። በእነዚህ አከባቢዎች የግንኙነት
አገልግሎቶቹ ተቋርጦ የሚቀጥል ከሆነ ህብረተሰቡ በሽታውን ለመከላከል መውሰድ ያለበትን
ጥንቃቄ አስመልክቶ መረጃ ካለማግኘቱም በላይ ለከፍተኛ የሥነ ልቦና ጫና መጋለጡ አይቀርም።
ይህ ደግሞ ‘መረጃን የማግኘት፣ የመያዝ እና የማስተላለፍ መብት’ ጥሰት ከመሆኑም በላይ
የአገልግሎቶቹ ክልከላ በራሱ ‘በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀም ከባድ ወንጀልን’ (Crime against
Humanity) ይሆናል።
የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ
The Human Rights League of the Horn of Africa (HRLHA)
http://www.humanrightsleague.org
______________________________________________________________________________
5
ክቡር ጠ/ሚኒስትር፤
በአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ እምነት እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው አሳሳቢ ጉዳዮች በቶሎ
ካልተፈቱ በአከባቢው ቢሎም በክልሉ ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ማስከተላቸው አይቀረ ነው።
ይህን በህዝብ ላይ የተጋረጠዉን አደጋ ሠላማዊ በሆነ መንገድ በዘለቀታነት ለመፍታት
የመንግሥትዎ ቁርጠኝነት ወሳኝነት አለዉ፡፡
በመሆኑም፡ የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ በአሁኑ ጊዘ በአገርቱ ዉስጥ ያለውን መጠነ ሰፊ
ችግሮች በተለይ ደግሞ በአራቱ የወለጋ ዞኖች እና በሁለቱ የጉጂ ዞኖች እንዲሁም ቦራና ዞን እየታየ
ያለውን አሰቃቂ ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚከተለዉን ሀሳብ ያቀርባል።
እነሱም:-
1. በአራቱ የወለጋ ዞኖች እና በሁለቱ የጉጂ ዞኖች እንዲሁም ቦራና ዞን ሥራ ላይ ያለው
“የኮማንድ ፖስት” አስተዳደር ተነስቶ ሕዝቡ መሠረታዊው ሰብዓዊ መብቱ ተከብሮለት
በሠላም እንዲኖር እንዲደረግ፣
2. “ኮማንድ ፖስት” ሥር በሚተዳደሩት በእነዚህ አከባቢዎች እስካሁን የተፈፀሙትን
የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ገለልተኛ አካል መርምሮ ውጠቱን ለሕዝብ ይፋ እንድያደርግ
ማድረግ እና ተጠያቂነትን ማስፈን፣
3. በምዕራብ ኦሮሚያ በአብዛኛው ዞኖች ተዘግቶ ያለው የእንቴርነት እና የስልክ አገልግሎት
(በተለይ በአራቱ የወለጋ ዞኖች) እንዲከፈት፤ በተለይ ‘ኮሮና ቫይረስ’ አገር ውስጥ
መግባት ጋር ተያይዞ የአከባብው ህብረተሰብ ስለ በሽታው ወቅታዊ መረጃዎችን ከአለም
ዙርያ በመከታተል አስፈላጊ ጥንቃቄ ማድረግ ይቻለው ዘንድ የእንቴርነት አገልግሎት ጊዜ
ሳይሰጥበት እንድለቀቅ፣
4. እርስዎ የሚመሩት መንግሥት በምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱው
የቀድሞ“የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት” ጋር ያለውን ቅራኔ በሆዴ ሠፍነት እና ትዕግስት
በሠላማዊ መንገድ በመፍታት ቡድኑም ሀገርቷን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማሸጋገር
በሚደረግ ሂዴት ውስጥ ተሣታፍ እንድሆን ማድረግ፣
የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ
The Human Rights League of the Horn of Africa (HRLHA)
http://www.humanrightsleague.org
______________________________________________________________________________
6
5. ከዚሁ ጋር ተያይዞ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዕዛዝ ተይዞ ኢ-መደበኛ በሆኑት ማጎርያ ቤቶች
ታስረው የሚገኙ ዘጎች ተፈትተው ወደየቄያቸው እንዲመለሱ፣
6. ከየዩኒቬርሲቲዎች የተባረሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው በአስቸኳይ
ተመለሰው የወደፊት ሕልማቸውን በተግባር እንዲተረጉሙ እንዲደረግ፣ የሚሉ ናቸው።
ከታላቅ አክብሮት እና ሠላምታ ጋር,

ጋ ሮማበ ቀለ ዋቃሣ፡
የ HRLHA ዳ ይሬክ ተር -ጀኔ ራል
Tel: +251 940 47 37 60
hrldirector@mail.org

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s