የጭቆና ፍጻሜ ንቅናቄን በጠመንጃ ኣፈሙዝ ማቆም በመርፌ ቀዳዳ

ግመል ለማሹለክ ከመሞከር ጋር ኣንድ ነው!

የቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ

(ታህሳስ 17 ቀን 2018ዓም)

ወያኔ ለ27 ዓመታት የኦሮሞን ህዝብ እየገደለ፣ እያሰቃየ፣ ከመሬቱ እያፈናቀለ፣ ስደተኛ እያደረገ፣ እያሰረና ከትምህርት ገበታ እያባረረ እስከ ዛሬ ቆይቷል። ይሁን እንጂ ህዝቡ በወያኔ የጠመንጃ ኣፈሙዝ ኣገዛዝ ስር ሲያካሄድ በነበረው ጠንካራ የጸረ-ጭቆና ኣመጽ ኢምፓዬሪቷን የማትወጣበት ውጥንቅጥ ውስጥ ከቷታል። በጠመንጃ ኣፈሙዝ የሚያምነው የወያኔ ወይንም ሕወሃት ስርዓት ዕለተ ሞቱና መቀበሪያው መቃረቡን በመገንዘብ በኦሮሞ ህዝብ ላይ በገሃድ ጦርነት ኣውጆ እነዚህን ዓመታት ኣያሌ ዜጎችን ለከፋ ጉዳት ዳርጓል። ዛሬ በጨቋኙ የወያኔ መንግስት ህይወታቸው ያለፈ የኦሮሞ ዜጎችን ለመቁጠር የሚያዳግት ሲሆን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ ተወንጀለው በወያኔ እስር ቤቶች ለከፋ ሰቆቃ በመዳረግ ላይ ናቸው።

የኦሮሞ ህዝብ ትግል ለእርስ የተዳረጉትን ወገኖቹን ከወህኒ ማስፈታት ጀምሯል። የኦሮሞ ህዝብ መላውን እስረኞቹን ከእርስ ለማስለቀቅ፣ እውነተኛ የመብት ታጋዮቹን ከኣውሬው የሕወሃት ስርዓት ለማትረፍ ትግሉ ተፋፍሞ መቀጠል ኣለበት።

የኦሮሞን ህዝብ ትግል ለማክሰም የኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ እንዲታወጅ የወሰነው የሕወሃት ቡድን በኦሮሞ ህዝብ ላይ በየዕለቱ የሚፈጽመውን የዘር-ፍጅት ተግባር ይበልጥ ለማጠናክረ ከማቀድ መሆኑ ግልጽ ነው። ይሁን እንጂ ወያኔ በጠመንጃ ኣፈሙዝ ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞን ከትግሉ ወደኋላ እንደማይመልሰው ሁሉም ይገነዘባል። በሰላማዊ መንገድ ለመብቱ እየተፋለመና የሃገር ባለቤትነት መብቱን በሰላማዊ መንገድ እየጠየቀ ባለው ህዝብ ላይ በቀጥታ ጦርነት ማወጅ በህዝቡ ላይ ኣደገኛ ጥፋት ለማስከተል ያለሙ ከመሆናቸውም ባሻገር ዛሬ በእጃቸው ባለው ጥይት እያደረሱት ላለው ችግሮች የሚጠየቁ መሆኑን ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ በጥብቅ ያሳስባል።

በመጨረሻም በመሳሪያ ኣፈሙዝ የጭቆና ፍጻሜ ንቅናቄን ማቆም፣ የኣባይ ወንዝን ምንጭ መዝጋት ነው! የኣባይ ወንዝን ምንጭ ለመዝጋት ማለም ያልታሰበ ከንቱ ህልም ነው። የጭቆና ፍጻሜ ኣመጽ እስከነጻነት ድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ በድጋሚ ይገልጻል።

ድል ለኦሮሞ ህዝብ!

ዘመኑ የጭቆና ፍጻሜ ዘመን ነው!

ታህሳስ 17 ቀን2018ዓም

ፊንፊኔ-ኦሮሚያ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s