ኦሮሞና ኦሮሚያ

የዓፄዎቹን ጋኔን ያናወጣ  ታላቅ ስም

barruuእዉነትም ይህ ስም ታላቅ ነዉ። የዓፄዎቹ ጋኔኖችም ይህንን ያዉቁታል፥ ይፈሩታልም። መንፈሱ ባለበት ኣካባቢ ይህ ስም ከተጠራ ጋኔኖቹ ይንቀጠቀጣሉ፤ ይንጫጫሉ፤ ይቆጣሉ፤ ተስፋ ሲቆርጡ ደግሞ እየተራገሙም ቢሆን ከነጭፍራዎቻቸዉ ጓዛቸዉን ነቅለዉ ወደ ጥልቁ ይገባሉ። ስሙ ከስም በላይ ይሆንባቸዋልና ሊቋቋሙት አይችሉም። ለሙከራ በየካፌዉ፣ በየሬስቶራንቱ አልያም ታክሲ ዉስጥ ስትገቡ ይህንን ስም ከፍ ባለ ድምጽ ብትጠሩ የጋኔን መዓት ሲደናበር ታዩታላችሁ። አልያም ደግሞ በእረፍት ቀናችሁ በኦሮሞ ባሕላዊ ልብስ ሽክ ብላችሁ በሰፈራችሁ ወይም በመዝናኛ ቦታዎች አካባቢ ጎርደድ-ጎርደድ በሉ። የሆነ ሰዉ ባልጠበቃችሁት መልኩ ጭር ጭር ብሎ በጥላቻ ዓይን ከተከተላችሁ ያ ጋኔን እየተቃጠለ ነዉና ዘና በሉ።

ከዓጼ ኃይለስላሤ ዘመነ-ንግሥና ጀምሮ መንፈሱ ከነገሠባቸዉ ሥፍራዎች የፊንፊኔ ዩኒቨርሲቲ  ዋነኛ ሆኖ ነበር። እዚያዉ ቦታ ላይ ለመንፈሱ ሥርዓተ-ዓምልኮ ይፈጸማል። መስዋዕት ይቀርባል። ዉዳሤና ቅዳሤ ይቸራል። ጭፍራዎችና ደቀ-መዛሙርት ሰልጥነዉ፣ ተቀብተዉና ተጠምቀዉ ለመንፈሱ ሀዋርያነት ከበቁ በኋላ በየቦታዉ ይበተናሉ። አንድ ሀገር፣ አንድ ሀይማኖት፣ አንድ ቋንቋና አንድ ባሕል የመንፈሱ መሪ ቀኖናዎች ናቸው። ከዚህ ዉጪ ያሉ እዉነታዎችን አይቀበልም። በተለይ ደግሞ ኦሮሞ እና ኦሮሚያ የሚባሉ ስሞችን መስማት እንደእሳት ይለበልበዋል። ለእኔና ለወገኖቼ ደግሞ ይህ ስም ከማር ይበልጥ ለኣንደበታችን ይጣፍጠልና በሄድንበት ቦታ ሁሉ ስለታላቅነቱ እንመሰክራለን። እዉነታዉንም እናስተምራልን። እዉነትን ይዞ ዝምታ አናዉቅበትምና  “ዝም በሉ!” በተባልን ቁጥር ደግሞ ይብስብናል። የዓፄዎቹን ጋኔን ያናወጣ ታላቅ ስም

1 thought on “ኦሮሞና ኦሮሚያ

  1. Akkam jiirtu? Qeerroo.  Rabbi wanta gochaa jirtan nuuf haa dhugoomsu. Kunoo, warri akka Jiituu Lammii uumamaniiru. Kana booda, Oromoo maaltu boodatti deebisa. Diinoti keenya, ituu ijaan argani, ni bilisoomna. Sirriidhha, Jiitu. Kana qofaa miti. ”Abashaan, rabbii fi Oromoo ituu maqaa hin waamin hin oolan”, jedha, beekaan Oromoo tokko.  Nagaatti, JiituNuuf jiraadhu

Leave a reply to Belachew Ibsa Cancel reply