ቡልቻ ደመቅሳ፡- “አንድነት ፓርቲ የገዢዎች ልጆች ናቸው”
ቡልቻ ደመቅሳ ለሰንደቅ ጋዚጣ ከሰጠው ቃለ ምልልስ የተወሰደ
- ዶ/ር ነጋሶ….. “አማራም ቢሆኑ ውስጡ ገብቼ አንድነትን አጠናክራለው” የሚል አቋም አላቸው።
- አፄ ኃይለስላሴ ኦሮሞነት አለባቸው ይባላል። ኦሮሞነት ስላላቸው የኦሮሞን ታሪክና ባህል አላቸው ማለት ግን አይደለም።
- ቡልቻ “አማራ” የሚለውን ቃል ተጠቀመ ብለው [አንድነቶች] ሊከፋቸው አይገባም። ታዲያ እኔ ምን ብዬ ልግለጣቸው? እዛ ያሉትን እኔ የማውቃቸው በአማራነታቸው ነው።
- በአንድነት ውስጥ ያሉ አማራዎች ግን የጀነራል፣ የሀገረ ገዢ፣ የአምባሳደር የአስተማሪና የሲቪል ሰርቪስ ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው።
- አፄ ቴዎድሮስም ቢሆን በጀግንነቱና ወንድነቱ እኛ ኢትዮያውያን ብቻ ሳይሆን መላ አፍሪካ ሊኮራ ይችላል። ነገር ግን እንደ ኦሮሞና ደቡብ ከእሳቸው ጋር አንተዋወቅም።
- አቢሲኒያ የሚባል ሀገር ነበር። ምናልባት ሶስት ሺው ከዚያ ጋር ተያይዞ ሊገለፅ ይችላል። የዛሬው ደቡብ፣ ምስራቅ ምዕራብ አቢሲኒያ አልነበረም።
- [አፄ ምኒልክ ወኪሎቻቸውን በመላክ] ዛሬ የምናውቃትን ኢትዮጵያን ፈጥረዋል።…..ነገሩ ሁሉ የሆነው በጉልበት ነው። በእርግጥ ጀርመንም፣ ጣሊያንም ይሄው ልምድ በመኖሩ በዚህ ላይ እኔ ቅሬታ የለኝም
Source: http://danielberhane.com

I have read so many articles or reviews about the blogger
lovers but this post is in fact a fastidious post, keep
it up.
Article writing is also a excitement, if you know afterward
you can write if not it is complex to write.