(ቄሮ – የኦሮሞ ወጣቶች ዜና, አዳማ, 25/05/2011) የዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ የህዝብን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር በሚል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የለቀቀው የአባይ ግድብ ዜማ እያስመረረ የሚገኝ ሲሆን፣በቀጣይ የተማሪዎች የእረፍት ወቅትን ተከትሎ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች “ስለ አብዮታዊ ዴሞክራሲ የፖለቲካ ፍልስፍና እና በኢትዮጵያ ስላስገኘው ልማት” ለተማሪዎች ሥልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አሳወቁ።
የኢህ አዴግ መንግስት በድንገት ትምህርት ሚንስቴር ዓመታዊ የትምህርት መርሃ- ግብሩን በአስቸኳይ እንዲያቋርጥና ወደ ፈተና ዝግጅትና ትግበራ እንዲገባ ባለፈው ሳምንት መመሪያ አስተላልፎለታል።
በዚህ ድንገተኛ ውሳኔ የተደናገጠው ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ ሣይውል ሳያድር ለየመሰናዶና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርእሰ መምህራን በጻፈው አስቸኳይ ደብዳቤ መምህራን የሚያስተምሩትን ትምህርት አቋርጠው ወደ ፈተና ዝግጅት እንዲጣደፉ በፋክስና በስልክ በአስተላለፈው መልዕክት ላይ አዟል፡፡
በዚህ መሰረት የመሰእናዶ ትምህርት (ፕሪፓራቶሪ ክላስ) ከግንቦት 20 ቀደም ብሎ እንዲገባደድ ; የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ደግሞ እስከ ግንቦት 30 ድረስ እንዲጠናቀቅ የሚያሳስብ አስቸኳይ መመሪያ አውርዷል።
በዚህ ውሣኔ መሠረትም ያልተጠናቀቁ ዓመታዊ የሁለተኛ መንፈቀ ዓመት የትምህርት ካሪኩለሞችን በማሟላት ላይ የነበሩ የ12ኛ ክፍል የመሰናዶ ተማሪዎች ከትላንት ሰኞ ግንቦት 15 ቀን ጀምሮ ያልተጠናቀቁ ትምህርቶቻቸው ተቋርጦ የማጠቃለያ ፈተና እንዲጀምሩ ተደርጓል።
በሌላ በኩል ደግሞ በሰሜን ሸዋ የሚገኙ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ለአባይ ግድብ ማሰሪያ የሚሆን ቦንድ ካልገዘችሁ ወይም ገንዘብ ካላዋጣችሁ ሞዴል ፈተና አትፈተኑም መባላቸውን ዘጋቢያችን ከስፍራው ባስተላለፈልን ዘገባ ገልጿል።
በዘገባዉ መሰረት ተማሪዎቹ የ8ኛ ክፍልን ሞዴል ፈተና ለመውሰድ ከመቀመጣቸዉ በፊት “ለህዳሴዉ ግድብ” ማሰሪያ የሚሆን ቦንድ ግዙ ተብለዉ ሲጠየቁ “እኛ ገንዘብ የለንም ወላጆቻችንም ገንዘብ የለንም ብለውናል” ብለዉ ሲመልሱ ፈተና አትፈተኑም በመባላቸዉ በወላጆችና በትምህርት ቤቶች መሃል ትልቅ ውዝግብ ተፈጥሮ እንደነበር የደረሰን ዜና ያመለክታል።
በሌላ በኩል ደግሞ እንደተማሪዎቹ ሁሉ ቦንድ ካልገዛችሁ ተብለዉ የተጠየቁት መምህራን በአገሪቱ ባለው የኑሮ ውድነት ምክንያት ገንዘብ ለማዋጣት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ቢገልጹም የዘረኛው አገዛዝ ካድሬዎች አሻፈረን በማለት የማስገደድ ስራቸውን መቀጠላቸውን የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።
የዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ የህዝብን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር በሚል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የለቀቀው የአባይ ግድብ ነጠላ ዜማ እጅግ እያስመረረ የሚገኝ ሲሆን፣ የአገዛዙ ቁንጮ የሆነዉ መለስ ዜናዊ ከግብጽ መንግስት ጋር ባደረገው ስምምነት የግድብ ስራው ግንባታ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ማድረጉንም አይዘነጋም።
Can you mention a reference which says the Dam construction is postponed?