የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መግለጫ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በሃገሪቷ በተለይም በኦሮሚያና በኣማራ ክልል ውስጥ ባሉ ችግሮች ላይ ከሌሎች
የኦሮሞና የኣማራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ማካሄዱ ይታወሳል።
ውይይቱም በፓርቲዎቹ ኣበይት የፖለቲካ ኣጀንዳዎች፣ በዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተለይም
በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ በተፈጸሙ ግድያና እስራት እንዲሁም በኦሮሚያና በኣማራ ክልል
በመንሰራፋት ዜጎችን ለከፋ ሰቆቃ በመዳረግ ላይ ያሉ ችግሮችን መፍታት በሚቻልበት ላይ ያተኮረ
ነበር።
ይሁንና ከሁለት ወራት ወዲህ ከኣርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ በተከሰቱ ውስብሰብ ሁኔታዎችና
ከተፈጠሩ ችግሮች የተነሳ ውይይቱ እንደታሰበው ሊሄድ ባለመቻሉ ኦነግ ከውይይቱ መካፈሉን ሊገታ
ቻለ።
የኦሮሞና የኣማራ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኦሮ-ኣማራ ስም መስከረም 23, 2020ዓም ተሰባስበው ስምምነት
ተፈራረሙ በሚል በወጣው መግለጫ ላይ ኦነግ እንደተሳተፈ ተደርጎ ስማችን መነሳቱ ተገነዘብን። ይህ
ሊታረም የሚገባው ስህተት ነው።
የውይይቱ መጀመር ያለ ቢሆንም፡ ትላንት በተካሄደውና ኦነግ ባልተካፈለበት መድረክ ላይ መቋጫ ላይ
የተደረሰ ስምምነት በሚል ኦነግ በመድረኩ ላይ እንደነበረ በማስመሰል የወጣው መግለጫ ድርጅታችንን
የማይወክል መሆኑን ለሁሉም እንገልጻለን።
ድል ለሰፊው ህዝብ!
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
መስከረም 24, 2020ዓም

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s