ለድል ተሰማራ!!
Masarat Tulluu Irraa
ውጭ ሀገር ተቀምጦ ምን ሊፈይድ ወሬ፡
ወገን ሲጨፈጨፉ በነጋ በጠባ፡
በገዥዎች ትእዛዝ በካዲዎች ደባ፡
በስርቤት ታጒሮ በሳት ሲጠበስ፡
በውነት ፉጡራነን ለወገን ምን ደርስ?
በሳይበሩ አለም የምንኖር በአፉ፡
ዘራችን በጥይት እንደ ቅጠል ሲርግፉ፡
ሰው ሆነን ለመኖር ምንድን ነው ትርጉሙ፡
በተግባር የሌለን ሁሌ ማጉረምረሙ፡
የቡና ላይ ወሬን እርም ብለን ተፉተን፡
ለድል እንነሳ እንታገል ተግተን፡
ሁሌ ከምንኖር እንባ እያነባን፡
ለድል እንነሳ ባንድ ላይ ሆነን፡
የትላንቱ ህፃን ሞትን ሲደፉር፡
መሆናችንን አውቀን ከሞት የማንቀር፡
ዝም ብለን ከምናልፉ ለወገን ሳንሰራ፡
ሀሜት አስወግድህ ለድል ተሰማራ፡
ነፃነት አይመጣም ቁጭ ብሎ በወሬ፡
መጣላችን ያብቃ ተገለን እንዳውሬ፡
ለድል ተሰማራ
