በፍትሕ እጦት ከሃገር መኮብለሉ ቀጥሏል

(ቄሮ ዜና  ፍንፍኔ  ነሃሴ 22 2011) በአቶ ብርሃን ሀይሉ የሚመራ  የወያኔ ፍትሕ ሚንስቴ ር መስሪያ ቤት በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጥብቅ ክትትል እያደረገ መወሰኑን ምንጮቻችን አገለጡ::

የቄሮ ምንጮች ከፍትሕ ሚ/ር እንዳስታወቁት በመስሪያ ቤቱ ዉስጥ በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጥብቅ ክትትል እንድደረግ የተወሰነው በፍትሕ ሚኒስቴር የሕግ ጥናት ማርቀቅና ማስረፅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ዓለሙ  ከወር በፊት ለስብሰባ አሜሪካ ሄደው በዚያው በመቅረታቸው ነው፡፡

ሚኒስትሩ አቶ ብርሃንና ዳይሬክተሩ አቶ ለገሰ ለሁለት ሣምንታት ወደ አሜሪካ ከሄዱ ቦኋላ  በሄዱበት ጉዳይ ላይ ከአሜሪካ ከፍተኛ የሕግ ኤክስፐርቶች ጋር እየተገናኙ ለተወሰኑ ቀናት ሲወያዩ ቆይተዋል፡፡

በወቅቱ አቶ ለገሰ ዘመዶቻቸውን ጠይቀው እንደሚመጡ ለሚኒስትሩ ነግረዋቸው ከሄዱ በኋላ በዚያው መቅረታቸውን የተናገሩት ምንጮ ቻችን ፣ አቶ ብርሃን ከተመለሱ  ቦኋላ  በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጥብቅ ክትትል እንድደረግ የወሰኑት ለአቶ ለገሰ መረጃ የሚያቀብሉ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞችን ለመጋለጥ በሚል ሰበብ መሆኑን ወሰኑን አስታውቀዋል፡፡

አቶ ለገሰ አሜሪካ ዉስጥ ለምን ለመቅረት እንደወሰኑ ለግዜው የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፍትህ ሚኒስቴር ኢሃዴግን በአባልነት ያልተቀላቀለም ሆነ ለመቀላቀል ፈቃደኛ ያልሆነ የህግ ባለሙያ በነጻነት እንደማይሰራ፣ የህግ ባለሙያ የጥብቅና ፈቅድ ማግኘት እንደማይችልና ሌላ ስራም ለመቀጠር እንደማማይፈቀድለት በመገንዘባቸዉ  ሳይሆን እንዳልቀረ የውስጥ ምንጮች ይናገራሉ::

በፍትህ ሚንስቴር ከፍተኛ አመራር አካላት ከመነጨ የውስጥ ሚስጥር በሚኒስትሩ የማናጅመንት አባላት ተወስኖ ተግባራዊ ከሆኑት መመሪያዎች አንዱ የመስሩያ ቤቱ የህግ ባለሙያዎች ኢህአዴግን በአባልነት መቀላቀል እንደሆነ ታውቁአል።

በመመሪያው መሰረትም ወያኔ ኢሃዴግን እንዲቀላቀሉ ተጠይቀው በተለያዩ ምክንያቶች ፈቃደኛ ያልሆኑ የህግ ባለሙያዎች በመስሪያ ቤቱ ማናጅመንት ውሳኔ የጥብቅና ፍቃድ እንዳያወጡ እንዲሁም ሌሎች ተዛማጅነት ያላቸውን ስራዎች እንዳይቀጠሩ በውሳኔ ታግደዋል።

ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ከጥቂት አመታት በፊት በጥቂት ሺሆች ይቆጠሩ የነበሩ አባሎቹን ቁጥር ከአምስት ሚሊዮን በላይ እንዳሳደገ የሚለፍፈው፣ ዜጎችን በግዳጅ አባል በማድረግ፣  በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የወያኔ ኢህአዴግ አባል የሚሆኑ ግለሰቦች በግዴታ፣ በጥቅማጥቅምና፣ አጣብቂኝ ውስጥ በመግባታቸው ነው:: ይሁንና አባል ተብዬዎቹ ለወያኔው ኢህ አዴግ አገዛዝ ምንም አይነት ፍላጎትም ሆነ ድጋፍ የሌላቸው መሆናቸውን ይናገራሉ።

አቶ ለገሰ ኦሮሚያ ክልል ዳኛ ሆነው በማገልገል ላይ እያሉ በ2000 ዓ.ም. ወደ ፍትሕ ሚኒስቴር መሥርያ ቤት ተዛውረው የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ የለውጥ አመራር ማስተባበሪያ ኃላፊና አሁን ደግሞ የሕግ ጥናት ማርቀቅና ማስረፅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆነው እየሠሩ ነበር፡፡ ከዚህ በፍትም በርካታ የሕግ ባለሙያዎችነ ዜጎች  በፍትሕ እጦት ከሃገሪቱ መኮብለላቸዉ ይታወቃል::

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s