የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርት አቆሙ

(ቄሮ – የኦሮሞ ወጣቶች, አርባ ምንጭ, 01/06/2011) በደቡብ ክልል ከአዲስ አበባ በ500 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኘው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች  በተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ውስጥ የተመገቡ 450 ያህል ተማሪዎች በጠና ታመሙ፡ተማሪዎች ባስነሱት ተቃውሞ ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸውንና ግቢው በፖሊስ ጥበቃ ሥር መዋሉና፣ ከግንቦት 22 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ትምህርት ማቆማቸውን ተማሪዎች  ገለጹ፡፡

የተማሪዎቹ ተቃውሞ  ያሳሰበው ዩኒቨርሲቲው ለአካባቢ ፖሊስ ደውሎ ኃይል እንዲመጣ በማድረግ ፖሊሶች ቢደርሱም፣ ሊቋቋሙት እንደማይችሉ በመታወቁ የፌዴራል ፖሊስ ደርሶ የተማሪዎቹ ተቃውሞ  ከግቢው እንዳይወጣ መቆጣጠር መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

ከግንቦት 22 እስከ ትናንትና ምሽት ድረስ ምግብም ሆነ ውኃ ሳያገኙ መቆየታቸውን ተማሪዎቹ ጠቁመዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ የቄሮ ምንጮች እንደገለጹት፣ ተማሪዎቹ ምሳ ከበሉ በኋላ  መታመም ጀመሩ፡፡ የሕመሙ ምልክቶች ራስ ምታት፣ ቁርጠትና ራስን እየሳቱ መውደቅ ሲሆኑ፣ በሁሉም ታማሚ ተማሪዎች ላይ ተመሳሳይ ምልክቶች ታይተዋል፡፡

በተማሪዎቹ እንቅስቃሴ ምክንያት ፌዴራል ፖሊስ ረብሻውን ለማስቆም በተከታታይ በሚተኩስበት ወቅት ራሳቸውን የሳቱ ተማሪዎች ወደ ጤና ጣቢያ መወሰዳቸውን፣ ሁለት ቀን ሙሉ ምግብ ያላገኙት ተማሪዎች ረብሻውን አባብሰዋል የተባሉ መታሰራቸውንም ተማሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

ተማሪዎቹ ከግቢ ለመውጣት ከፖሊስ ጋር በፈጠሩት ግብግብ ለፖሊስ ቆመጥ መዳረጋቸውን የዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ በግቢው ውስጥ የነበሩ የተሸከርካሪዎች መስታወት በድንጋይ ተሰባብረዋል፡፡

Leave a comment