ትግላችን ወያኔ የሚወረውረውን መከላከል ሳይሆን ማጥቃት ነው!

(ቄሮ – የኦሮሞ ወጣቶች) የነጻነትና የዲሞክራሲ ትግላችን ወያኔ የሚወረውረው ነገር ላይ የመከላከል እርምጃ መውሰድ ሳይሆን ቀጥታ የማጥቃት እርምጃ የሚወሰድበት ደረጃ ላይ በመድረሳችን ኣስፈላጊ የሆነ ህብረ ድርጅታዊ የስነልቦናና የመታገያ ኣጀንዳ ለውጥ ማድረግ ያስፈልጋል::

በፍርሀት የተዋጠዉ የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ ንጹህ ዜጎችን ማሰር ስልጣኑን የሚያራዝምለት ይመስል በኦሮሚያ ክልል መጠነ ሰፊ የእስር ዘመቻ የከፈተዉ ሰሜን አፍሪካ ዉስጥ አምባገነኖችን ለብልቦ መድረሻ ያሳጣዉን የአብዮት ሰደድ እሳት ኢትዮጵያም ውስጥ ለማቀጣጠል ተግተው የሚሠሩ ሃይሎች አሉ በሚል ሰበብ ሲሆን የጥቃት ኢላማዉ በተናጠል በኦሮሞ ተወላጆች ለምን አንዳነጣጠረ የታወቀ ነው።

በኦሮሚያ ውስጥ ለረጂም ግዜ ኦነግን ትደግፋላችሁ በሚል ሰበብ በህዝቡ ላይ የሚፈፀመዉ ሂሊናን የሚሰቀጥጥ በደል ወጣቱን ክፍል እጅግ እያስቆጣ ስለመጣ በአገራችን ውስጥ በዬትኛውም ጊዜና ቦታ ሊፈነዳ ይችላል ተብሎ የሚጠበቀዉን ህዝባዊ አብዮት ኦሮሚያ ዉስጥ ሊጀምር ይችላል የሚል ስጋት ወያኔን ስላስጨነቀዉ እንደሆነ በግልፅ ይነገራል።

ኣሁን ግን ተነሳሽነቱ መቀበልና የምንወስደው እርምጃ ሁሉ ይህንን ከስሌት ያስገባ መሆኑን በመረዳት የማጥቃት እርምጃ የሚወሰድበት ደረጃ ላይ በመድረሳችን በስነልቦና ደረጃ የነጻነትና የዲሞክራሲ ሀይሎች ሊኖራቸው የሚገባው የመንፈስ ዝግጁነት ማድረግ ያስፈልጋል:: ይህ ከተከላካይነት ወደ ኣጥቂነት የሚደረግ ሽግግር ደግሞ ጠላትን መነጠልና፣ ወዳጅን ማብዛት፣ ከያንዳንዱ እርምጃችን ጋር የተሳሰረ የሁልጊዜም ስሌታችን ኣካል ማድረግን ይጠይቅብናል::

ሁለተኛው ቁምነገር ደግሞ የዴሞክራሲ ሀይሉን በኣንድ የመታገያ ኣጀንዳ ዙሪያ ማሰለፍና ቆይቶም በዚህ መስመር ዙሪያ ላይ የታጠረ ህብረ ድርጅታዊ ኣመራር ስር ማሰባሰብ ነው:: ኣሁን ሁለቱም ጊዜ ሳይወስድ መፈጸም ያለባቸው ቢሆኑም የኋለኛው ትንሽ ጊዜ የሚወስድ ቢሆን እንኳን የመታገያ መስመሩን በተመለከተ ሁሉም በየድርጅቱ ኣሁኑኑ ሊያደርገው የሚችለው ነገር ስለሆነና ባጠቃላይ ህዝቡም ዘንድ መናበብን ማዳበር ስለሚገባ ኣሁኑኑ ማድረጉ ኣስፈላጊ ነው::

1 thought on “ትግላችን ወያኔ የሚወረውረውን መከላከል ሳይሆን ማጥቃት ነው!

  1. i’m really setisfied by the above message. and ‘Together we can’!! when all oromo’s youth are thinks as one/ please, we are always think as oromiya’s avoid divided in zone’s, woreda’s and kebeles.

Leave a comment