የኦሮሞ ወጣቶች ህዝባዊ የመታገያ አጀንዳዎች

1. የወያኔ/ኢህአዴግ አገዛዝ የህዝብን ፍትሃዊና ህጋዊ መብቶችና ጥያቄዎች ለማፈን ባለፉት 20 አመታት በተለያዩ የኣገሪቱ አካባቢዎች በተለይ ደግሞ በኦሮምያ፣ በኦጋዴን: በጋምቤላና በሌሎችም ክልሎች ህዝቦች ላይ የሚያካሄደውን ወታደራዊ የእመቃ ዘመቻ አሁኑኑ ያቁም።
2. በሃገሪቱ እስር ቤቶች የሚማቅቁ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አሁኑኑ ይፈቱ።የሰው ልጆች ቄራ የሆነውና የሰቆቃ ስራ መፈጸሚያ የሆነው የማእከላዊ እስርቤት ባስቸኳይ ፈረሶ ለዘላለሙ ይዘጋ
3. የአገዛዙ የተሳሳተ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማስተካካያ እስኪበጅለት ድረስ ይህ የተሳሳተ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ችግር ላይ ለጣላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ዳቦ፣ ስኳር: እህልና ዘይት የመሳሰሉት የመሰረታዊ ፍጆታ እቃዎች ባስቸኳይ ከመነሻው የመንግስት ድጎማ ተደርጎላቸው ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚደርስበት መንገድ ይመቻች::
4. የመለስ ዜናዊና የቤተሰቡ ንብረት ባስቸኳይ እንዲወረስ፤ ልኩ በውል በማይታወቀው የመለስ ቤተስብና የቅርብ ባለሟሎቹ የሙስና ተግባራት የምርመራ ስራ አሁኑኑ ይጀመር ።
5. የኢትዮጵያን ህዝብ ለአለም አቀፍ ጌቶች ባሪያ የሚያደረገው መሬት ለባእዳን አሳልፎ የመሸጥ ፐሊሲ አሁኑኑ ይቁም። በዚህ ረገድ የተደረሱ አለም አቀፍ ውሎች በሙሉ አሁኑኑ ይሰረዙ።
6. መለስ ዜናዊ ባስቸኳይ ከጠቅላይ ሚስትርነቱ ይነሳ የመንግስትን ስልጣን ባስቸኳይ ይልቀቅ።
7. ህገ ወጥ በሆነና በተጭበረበረ ምርጫ የተቋቋሙት የህዝብ መወሰኛና የፌደራል ምክር ቤቶች አሁኑኑ ይፍረሱ። ሁሉም የነጻነት ንቅናቄዎችና ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች የተሳተፉበት ዓላማው ማህበራዊ ፍትህንና ዴሞክራሲን ማንገስ የሆነና በኣጭር ጊዜ በነጻ የምርጫ ተቋምና ኣለምኣቀፍ ታዛቢዎች ሙሉ ለሙሉ በተመሰከረለት ነጻና ፍትሀዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ መንግስት የሚያቋቁም የሽግግር መንግስት ይቋቋም።

ለጋራ ጥያቄዎችን አሁኑኑ በጋራ እንነሳ!!

1 thought on “የኦሮሞ ወጣቶች ህዝባዊ የመታገያ አጀንዳዎች

Leave a comment