የወያኔ የግፍ አገዛዝ ነባር አባላቱን በማራገፍ በአዲስ መልሶ በማደራጀት ላይ ነው

(የቀሮ ዜና ምንጭ /ፊንፍነ/ ሚያዝያ 18/2011) ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ አባሎቹን የየመልሶ ማደራጀትና የማጠናከር ሥራውን አቀላጥፎ መቀጠል እንዳለበት ከበላይ አካል ትዕዛዝ መተላለፉን ኢህአዴግ ጽ/ቤት የሚገኙ የዜና ምንጮቻችን አስታወቁ፡፡

የዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ የመልሶ ማደራጀትና ቀደም ሲል የነበረውን መዋቅር የማጠናከር ሥራው በስፋት የሚካሄድባቸው መዋቅሮች በእናት ድርጅቶች (የየአካባቢው ነዋሪዎች) በሴቶች ሊግ፣ በወጣት ሊግ፣ በመንግሥታው ተቋማት- የቢሮ አደረጃጀት እና በመምህራንና ተማሪዎች አደረጃጀት ላይ ያተኩራል ያሉን የዜና ምንጮቻችን በዕድር ምክር ቤት ፎረም እና የልማት ጣቢያዎችም ላይ አዲስ ተዘዋዋሪ መዋቅር ይዘረጋል ብለውናል፡፡

እንደ ምንጮቻችን ገለጻ ይህ የመልሶ አደረጃጀት ያስፈለገበት ሁኔታ የተዳከመውን፣ የተሰላቸውንና በሙስና የተዘፈቀውን የኢህአዴግ ፓርቲ አመራር አባላትና ተራ አባላት በማራገፍ በምትኩ አዳዲስ አባላትን በማፍራትና በኢህአዴግ ፕሮግራም “በማጥለቅ” የማስፈጸም አቅምን ማጎልበትና  የወያኔ አገዛዝ  ዕቅድን በመተግበር የህብረተሰቡን ይሁንታ ማግኘት ነው፡፡

በዚህ የፓርቲ አባላት የመልሶ ማደራጀትና የማጠናከር ሂደት በርካታ የኢህአዴግ የአመራር አባላት ከፓርቲው የሚራገፉ ሲሆን፣ በምትካቸውም አዳዲስ የወያኔ አባላትን ወደ አመራር ደረጃ ከፍ በማድረግ እነርሱም በሂደት ሌሎች አዳዲስ አባላትን ለፓርቲው እንዲመለምሉ ሥልጠናዎች ይሰጣቸዋል ሲሉ ምንጮቻችን ገልጸውልናል፡፡

የሕዝብ ኃይል ያሸንፋል!

Leave a comment