የወያኔ አገዛዝ ፍርሃቱ ከቁጥጥሩ ውጭ እየወጣ ነው

የወያኔ አገዛዝ በአዲስ አበባና በዋና ዋና የክልል ከተሞች የደህንነትና የጸጥታ ጉዳይ አሳሳቢነትን አስመልክቶ ሕዝባዊ ስብሰባ መደረጉ የተገለጸ ሲሆን፤ የዘረኛው አምባገነን አገዛዝ ባለስልጣናትና ሆድ አደሮች ኢትዮጵያ ውስጥ ወጣቶች የሚመሩት ሕዝባዊ ንቅናቄ እንዳይከሰት ሰግተዋል ፡፡

የደህንነትና የጸጥታ ጉዳይ አሳሳቢነትን አስመልክቶ የተካሂደው ሕዝባዊ ስብሰባ የወጣት ማህበራትን፣ የሴቶች ሊግን፣ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችንና የመንግሥት ሠራተኞችን ለይቶ የጠራ ሲሆን የዘረኛው አገዛዝ ከፍተኛ አመራሮች ስብሰባውን ስብሰባዎቹን መምራታቸው ተገልጹአል::

የስብሰባው አጀንዳዎች የአካባቢና የሀገር ልማት ቁርኝት፣ የሀገርን ልማት የሚያደናቅፉ የደህንነትና የጸጥታ ጉዳዮች፣ ለወጣቶች የብድር መስፈርትና አቅርቦት፣ ወቅታዊ የዓለም ሁኔታና የኢትዮጵያ አጠቃላይ ዕድገት የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ይገኙበታል በማለት ምንጮቻችን ገልጹአል፡፡

በስብሰባው ላይ የተሳተፉት ወጣቶች ከንቁ የኢህአዴግ ፓርቲ አባላትና ካድሬዎች ጋር በአንድነት በመጠርነፍ በቅርብ ጊዜያት ውስጥ በአካባቢ ልማትና የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ተጠሪ ሆነው እንዲንቀሳቀሱና እንዲሰሩ እየተደረገ ሲሆን ይህም በምሥራቅ አፍሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ የዓረብ አገራት ላይ የተከሰተውን ዓይነት ሕዝባዊ መነቃቃት በኢትዮጵያም እንዳይከሰት ለመከላከል ያስችላሉ ከተባሉ ልዩ ልዩ ስትራቴጂዎች ውስጥ አንዱ ነው።

ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በተለይም የሰሜን አፍሪቃው ህዝባዊ አብዮት ከተቀሰቀሰ ወዲህ በሃገር ውስጥ ያለው እንቅስቃሴ እጂግ እያስፈራውና እያስጨነቀው እንደመጣ ሲዘገብ ከዚህ ጭንቀት መውጫ መንገድ አድርጎ እየወሰደ ያለው ርምጃም ንጹሃን ዜጎችን በጂምላ ወደ እስር ቤት ማጎር እንደሆነ በርካታ የዜና አውታሮች የዘገቡት መሆኑ ይታወቃል::

ከስድስት ኪሎ ወደ ጊዮርጊስ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የሃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ (አፍንጮ በር ድልድይ) ላይ ሞት ለወያኔ የሚል ጽሁፍ በትላልቅ ፊደላት ተጽፈው ነበር ፣፡ በራሪ ወረቀት በከተማ ውስጥ የመበተኑ ሥራ ተፋፉሞ በመቀጠል ሰሞኑን በመርካቶ ውስጥ እየተበተነ እንደሆነ ለማረጋገጥ ተችሎአል።

Leave a comment