የኦሮሞ ወጣቶች

Ka’i, Qeeroo

የኦሮሞ ወጣቶች ንቅናቄ መግለጫ

የኦሮሞ ወጣቶች ንቅናቄ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ፖለቲካ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ በቱኒዚያ፡ በግብፅና  በሌሎችም በመካከለኛዉ ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪቃ በመካሄድ ላይ ያሉት የህዝብ  አመጾች በተመሳሳይ ጭቆና ሥር ላሉ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ የአለም ክፍሎች  አርዓያነት ያለው መልዕክት መስተላለፉን ገልጿል።

በኢትዮጵያ ለሚታየዉ የለዉጥ ፍላጎት መነሳሳት እነዚሁ የሕዝብ አመጾች ምክንያት  እንደሆኑና ወቅቱ የአምባገነንና የፈላጭ ቆራጭ የፖለቲካ ስርኣቶች ተወግደዉ  ዲሞክራሲያዊና የህዝቦች ሉኣላዊነት  የሚሰፍንበት እንደሆነ አመልክቷል።

በኢትዮጵያ ለሚቀጣጠለዉ አመፅ መሰረታዊ ምክንያት የሚሆኑትና የሚያጎለብቱት  የሚያደርጉት በአገሪቱ ዉስጥ የሚታዩት ሁኔታዎች እንደሆኑ በመግለጫዉ  ተጠቅሷል። በመሆኑም ይላል መግለጫዉ “እኛ የኦሮሞና የሌሎችም ጭቁን ሕዝቦች ተማሪዎች የህዝባዊ አመፁን ለመለኮስ የመጀመሪያዎቹ ለመሆን ቁርጠኝነት እንዳለን  ለአለምና ለኢትዮጵያ ህዝብ እናረጋግጣለን። በባርነት ከመኖር በነፃነት መሞትን  መርጠናል የሚለዉ መግለጫ “‘ ስቃይና ባርነቱ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አሁኑኑ  እንዲወገድና ነፃነትና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ያቀጣጠልነዉን ችቦ ቀሪዉ የኢትዮጵያ  ህዝብ ይዞ እንደሚከተለን አምነት አለን”‘ የሚለዉ መግለጫ ሰባት ንጥቦችን አስቀምጧል።

1. የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በስታሊናዊ ድርጅታዊ መዋቅሩም ሆነ  በሚያራምዳቸዉ ማህበራዊና ፖለቲካዊ አጀንዳዎች  በጠባብ ጎሰኝነት ላይ  የተመሰረተ፡ በአገሪቱ ዘረጋሁ የሚለዉ የፌዴራል መዋቅር ለከፋፍለህ ግዛዉ  አላማዉ ካልሆነ በስተቀር ምንም ትርጉም የሌለዉ፡ የኦሮሞ፡ የኦጋዴን፡ የሲዳማ  እና የሌሎችንም የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች በዋና ጠላትነት ያነጣጠረ  መሆኑን  በመግለፅ… ላለፉት 20′ አመታት በኦሮሞ፡ በኦጋዴንና በሌሎችም ጭቆና  ላለፉት 20′ አመታት በኦሮሞ፡ በኦጋዴንና በሌሎችም ጭቆና  በበዘባቸዉ አካባቢዎች የሚገኙ ህዝቦች የሚያነሱትን ጥያቄ በሃይልና በህገ ወጥ  መንገድ ለማፈን የሚደረገዉ ወታደራዊ ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲቆም

2.  መለስ ዜናዊ በስልጣን ላይ ላለፉት 20′ አመታት በአፈናና በጭቆና የቆዩ  ከመሆኑም በላይ አገዛዙ የህዝብን ሰብኣዊ መብት በመርገጥ፡ በማንገላታት፡  በማፈናቀል፡ በማሰቃየት፡ በማሰር፡ በመግረፍና  በመግደል በአስር ሺዎች የሚቆጠሩትን በየእስር ቤቱ የህሊና እስረኛ አድርጓቸዋል። ስለሆነም የፖለቲካ  ስለሆነም የፖለቲካ  እስረኞችበአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ  እንዲፈቱ፡ በተለይም የሰዉ ልጅን  በመግረፍና በመደብደብ      ለማሰቃየት የተቋቋመዉ ማዕከላዊ የምርመራ  ድርጅት በአስቸኳይ እንዲፈርስና እስከመጨረሻዉ እንዲዘጋ

3.   የመለስ ዜናዊ መንግስት የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግቤአለሁ ይበል እንጂ በህዝቡ  ኑሮ ላይ አንዳችም ለዉጥ እንደሌለ መንግስት በሚከተለዉ የተዛባ የኢኮኖሚ  ፖሊሲ ምክንያት ይልቁንም በሽታ፡ ድንቁርና፡ እና ረሃብ የህዝቡ ማህበራዊ  ህይወት መለያ ምልክት ሆኗል። ስለሆነም መሰረታዊ የሆኑ የፍጆታ እቃዎች  ስለሆነም መሰረታዊ የሆኑ የፍጆታ እቃዎች  ስኳር፡ ዘይት እና ዳቦ የመሳሰሉትን መንግስት በአስቸኳይ ለህዝብ እንዲያቀርብና  የተሳሳቱትን የገበያና የኢኮኖሚ ፖሊሲዎቹን እንዲያስተካክል

4.   የመለስ ዜናዊ አገዛዝ እጁን ያላስገባበት እንዳለመኖሩ በተለይም በኢኮኖሚዉ  ዘርፍ ባለቤታቸዉ ወ/ሮ አዜብ መስፍን የሚቆጣጠሩት ኤፈርት በሚል  የሚታወቀዉ የህወሃት የንግድ ድርጅት እንደሆነ ከህዝብ የተሰወረ አይደለም።

በመሆኑም በመለስ ዜናዊ ቤተሰብ ስም የሚገኘዉ ንብረት እንዲወረስና  በቤተሰባቸዉና በቅርብ አጋሮቻቸቸዉ  የተፈፀሙ የሙስና ተግባሮች እንዲመራመሩ;;

5. ከ90′ በመቶ በላይ የሚሆነዉ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ህይወት የተመሰረተዉ በግብርና ላይ ሲሆን በ1960ዎቹና በ70ዎቹ መጀመሪያ ላይ የተነሳዉና በ1974′ አብዮት እልባት ያገኘዉ የመሬት ላራሹ ጥያቄ የንጉስ ሃይለ ስላሴን አገዛዝ  ከስልጣን ያስወገደ፡ ሕዝብን በፖለቲካ ዙሪያ ያስተበበረ እንደነበር ይታወሳል።  ይሁን እንጂ የሕወሃት አገዛዝ ዳግመኛ ወደ ነበርንበት ለመመለስ የሚከተለዉ  መሬትን በገፍ ለዉጭ ባለሃብቶች የመስጠት ፖሊሲ ሕዝባችንን ከመሬቱ  የሚያፈናቅለዉ፡ ባለቤትነት የሚያሳጣዉ፡ ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች የሚያገልለዉ፡ ስራ አጥነት የሚያሰከትልና ዘመናዊ ባርነት ዉስጥ የሚጥል በመሆኑ፡ ይህ ፖሊሲ ባስቸኳይ እንዲቆምና እስከዛሬ የተደረጉት አለም አቀፍ  ይህ ፖሊሲ ባስቸኳይ እንዲቆምና እስከዛሬ የተደረጉት አለም አቀፍ ስምምነቶች ዋጋ እንደሌላቸዉ ተቆጥረዉ እንዲሰረዙ  ስምምነቶች ዋጋ እንደሌላቸዉ ተቆጥረዉ እንዲሰረዙ

6. ኢትዮጵያ ባለፉት 20′ አመታት እጅግ አስከፊ ወደ ሆነ ሁኔታ ዉስጥ በመግባት  ላይ የምትገኝ ሲሆን በህግ አዉጪዉ፡ በሕግ አስተርጓሚዉና በህግ አስፈፃሚዉ  መካከል ምንም አይነት የስልጣን ክፍፍል የማይታይበት፡ በስታሊናዊ መንግስት  እንደሚታየዉ ሁሉ ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ በህዝብ ሳይመረጡ እራሳቸዉ  ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ በህዝብ ሳይመረጡ እራሳቸዉ  በፈጠሩት መዋቅር አማካይነት ስልጣኑን ሁሉ በብቸኝነት የሚቆጣጠሩ በመሆኑ  ስልጣናቸዉን በአስቸኳይ እንዲለቁ  ስልጣናቸዉን በአስቸኳይ እንዲለቁ

7. ከ90′ የማያንሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በህግ ተመዝግበዉ  በሚንቀሳቀሱበት አገር ባለፈዉ ግንቦት 2010′ በ99.6′ በመቶ ድምፅ ህወሃት/’ ኢህአዴግ አሸነፍኩ የሚለዉ ምርጫ ተቀባይነት የሌለዉ፡ የምርጫ ቦርዱ  የመንግሰት ሌላ እጅ በመሆኑ፡ የአገሪቱ ሀብትና ንብረት፡ የመገናኛ ብዙሃን፡ የፌዴራል ፖሊስና የፀጥታ ሃይሎች የገዢዉ ፓርቲ መሳሪያ በሆኑበት የተካሄደ፡

በዚህ ምክንያት ምርጫዉ የተጭበረበረና አሳፋሪ በመሆኑ ሁለቱም ምክር ቤቶች  ምርጫዉ የተጭበረበረና አሳፋሪ በመሆኑ ሁለቱም ምክር ቤቶች በአስቸኳይ እንዲበተኑ፡ ከሁሉም የነፃነት ንቅናቄዎችና ለማህበራዊ ፍትህና ለዲሞክራሲ የቆሙ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ተሳታፊ የሚሆኑበት የሽግግር  መንግስት እንዲመሰረት  መንግስት እንዲመሰረት ብሄራዊ የኦሮሞ ወጣቶች ንቅናቄ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ  ባወጣ የአቋም መግለጫ ጠይቋል።

https://qeerroo.files.wordpress.com/2011/04/labsa-qeerroo-afaan-amaaraa-1.pdf

Labsa Qeerroo- የህዝባዊ አብዮት ጥሪ

3 thoughts on “የኦሮሞ ወጣቶች

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s