የአቶ መለስ ወቅታዊ ዛቻ

(ቄሮ ዘጋቢ October 22, 2011)  የወያኔ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለፓርላማቸው ባቀረቡት እልህና ቁጣ የተቀላቀለበት፣ ማስፈራሪያና ዛቻ በበዛበት ንግግራቸው ጋዜጠኞቹ ወንጀለኞች መሆናቸውን ያለጥርጥር ተናግረዋል።

ሌሎች ጋዜጠኞችና አስተያየት ሰጪዎች ስለተከሳሻቹ ንጹሕነት መጻፋቸውን ጭምር ሕገ ወጥ መሆኑን የደሰኮሩት መለስ፣ እርሳቸው ግን የተጠርጣሪዎቹን ወንጀለኝነት በማያወላውል ሁኔታ አራጋግጠው ሲናገሩ ተሰምተዋል።

የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቴዎች የውሳኔ ጭብጥ ከአቶ መለስ ቢሮ እንጂ ከሕግ ፍልስፍናና መጻሕፍት አይቀዳም” ያሉ አንድ የሕግ ባለሞያ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር የፍርድ ሒደቱን መጨረሻ ከወዲሁ የሚያረጋግጥ ነው” ሲሉ ለአዲስ ነገር ተናግረዋል።

ከእስር ተርፈው በከፍተኛ ጫና ውስጥ ሥራቸውን ለማከናወን በመሞከር ላይ ያሉት ጋዜጠኞችም የአቶ መለስ መልእክት እንዲደርሳቸው ተደርጓል። የአቶ መለስ ንግግር በስም ባይጠቅሳቸውም መልእክቱ ለፍትሕ እና ለአውራምባ ታይምስ ጋዜጦች እንደሆነ ብዙዎች ተስማምተዋል።

http://youtu.be/AkY7P-ngqOY

http://youtu.be/iM4IM7cjKuM

Leave a comment