የሰሜን አፍሪቃ አምባገነኖች አንድ ባንድ እየተወገዱ ነው

(ቄሮ ዘጋቢ October 22, 2011)  በቱኒዚያ ተቀጣጥሎ የሰሜን አፍሪቃ ሃገራት አምባገነኖችን እየጠራረገ ያለው የህዝብ አመጽ በሊቢያ ከተቀሰቀሰ ሰባት ወራት ቦኋላ ተቃዋሚዎቻቸውን አንዴ ሽብርተኞች፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ የውጪ ቅጥረኞች ከማለት አልፈው አይጦች እያሉ ሲሳደቡ የነበሩት ሙአመር ጋዳፊ ለተቃዋሚዎቻቸው በተመኙት የአይጥ ጉድጓድ ውስጥ ለ2 ወራት ያህል ከመሸጉ ቦኋላ የሚያሳፍር ሞት መሞታቸው መላውን የአለም ህዝብ እያነጋገረ መሆኑ ታወቀ።

ሙአመር ጋዳፊ በሥልጣን ላይ በቆዩባቸው የመጀመራዎቹ አሥር አመት የህዝብ ፍቅር የተቸራቸው መሪ የነበሩ እንደሆነ የሚናገሩት፤ ባልተገደብ የሥልጣን ዕድሜ አገሪቱን ለመምራት የተፈጠሩ ብቸኛ ሰው አድርገው እራሳቸውን ወደ መቁጠር በመሸጋገራቸው አሁን ለደረሱበት አሳፋሪ ሽንፈትና ሞት ተዳርገዋል ይላሉ።

ጋዳፊ 42 አመታት ያህል ሥልጣን ላይ ለመቆየት የተጠቀሙበት ስልት መለስ ዜናዊ በአገራችን ላይ እያደረገ እንዳለው ህዝብ እርስ በርሱ እንዳይተማመን በጎሳና በነገድ በመከፋፈል እንደሆነ ይታወቃል። በቱንዚያ የፈነዳው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደሊቢያ በተዛመተበት ወቅት ህዝብ ያነሳውን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ በመመለስ ለአገራቸውና ለራሳቸው ክብር የተሻለ አስተዋጾ ማድረግ ይችሉ የነበሩት ጋዳፊ፤ ስልጣን ላይ ለረጂም ጊዜ በመቆየት በመጣ አልደፈርም ባይነት የአምባገነኖች ትዕቢት ሲወጠሩና በባዶ ሜዳ ሲደነፉ ከሰነበቱ ቦኋላ ከተደበቁበት የቆሻሻ መተላለፊያ ቱቦ ውስጥ በውርደት ተጎትተው በመውጣት እንደተገደሉና ጦሱ ከራሳቸው አልፎ ለልጅ ልጆቻቸውም መትረፉ ብዙዎቹን ያነጋገረ ሆኖአል።
የጋዳፊ መገደል ዜና የተሰማው የሽግግሩ አስተዳደር ተዋጊዎች ሐሙስ እለት ማለዳ ሲርቲ ላይ አዲሱን የሊቢያ ሰንደቅ ዓላማ ከሰቀሉ በኋላ ነው። ከተማይቱን ለበርካታ ሣምንታት ሲያናጋት በከረመው የደፈጣ ተኩስና የከበድ መሣሪያ ድምፅ ቦታ ወደሰማይ በሚንጣጣ የደስታ መግለጫ ተኩስና የመኪና ክላክስ ተተክቷል። የሊቢያ የሽግግር መንግሥት ባለልስጣናት ጋዳፊ ሲርቲ ላይ በተካሄደ ውጊያ መገደላቸውን እንዳስታወቁ ጋዳፊ ለአርባ ዓመታት በገዛት ሀገርና ሌሎች ከተሞችም ፈንጠዚያ ሆኗል። ጋዳፊ ለሁለት ወራት ተሸሽጎ ሲሳደድ የቆየበት ወቅት መደምደሙ ለብሔራዊ የሽግግር መንግሥቱ በሀገሪቱ ላይ ቁጥጥሩን የሚያጠናክርበት ምዕራፍ ከፍቶለታል።

የሙአመር ጋዳፊን ሞት ተከትሎ የዝግጂት ክፍላችን ከተለያዩ ቦታዎች በኢሜይልና ስልክ መለክቶች የደረሱን ሲሆን ከአዲስ አበባ በኢሜይል ከተቀበልናቸው መለክቶች መካከል አንደኛው፣ እንዳሉት፣ የጋዳፊ ሞት ለሊቢያዊያን ርካታ ያስገኘላቸው ሲሆን የሊቢያዊያኑ ርካታ ደግሞ ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ይተስፋ ሰጪ ሆኖልናል ብለዋል:: ቀጥለውም፣ በፍጹም ይደፈራል ተብሎ የማይታለመው የሊቢያው አምባገነናዊ አገዛዝ እንዲህ ሲገረሰስ ማየታችን መለስናና የሱን አሽቃባጮች ከሃገራችን ምድር ጠራርገን ለማጥፋት ምንም እንደማይከብደን ነው በማለት አስተያየታቸውን አጠቃለዋል።

Diddaan Qeerroo Itti Fufee,Gandi Wanciin Dirree Waraanaa Taate

Leave a comment