(የቄሮ ዜና ምንጭ /ቄዜም/ ፍንፍኔ ሀምሌ 12፣2011) የወያኔ ሽፍታ ቡድን በኦሮሞ ባለህብቶች ላይ የሚፈጽመዉ ዘረፋ በግልጽ እየተባባሰ መሆኑ ተዘገበ።
የቄሮ ዜና ምንጭ ከፍንፍኔ እንደዘገበው በወያኔ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዓቃቤ ሕግ ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አየለ ደበላ (አይኤምኤፍ)፣ አቶ ገብረ ኪዳን ገብረ ሥላሴ (ሞሮኮ)፣ አቶ ከበደ ተሰራ (ወርልድ ባንክ) እና አቶ ሌንጫ ዘገዬ በባንክ ያላቸው ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ወያኔ ሒሳብ እንዲዛወር መደረጉ ታወቋል፡፡
ከወያኔ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በተጻፈ ደብዳቤ ከሰኔ 23 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ አቶ አየለ ደበላ፣ ወ/ሮ አልማዝ ሁሉቃ (የአቶ አየለ ባለቤት)፣ አቶ ከበደ ተሰራ፣ ወ/ሮ አልማዝ ጫካ (የአቶ ከበደ ባለቤት)፣ ወ/ሮ አልማዝ ሁሉቃና ወ/ሮ አልማዝ ጫካ በጋራ በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማኅበር በተለያየ የሒሳብ ቁጥር አስቀምጠውት የነበረ በድምሩ 40,747,259.75 ብር፣ ወደ ወያኔ ካዝና ሒሳብ ከሰኔ 25 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ገቢ መደረጉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ታሳሪዎቹ በተከሰሱበት ወንጀል በወያኔ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የተጣለባቸውን የእስርና የገንዘብ ቅጣት በመቃወም ለወያኔ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ጠይቀዉ ጉዳዩ በመታየትም ላይ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳሌ የወያኔ ዘራፍዎች ለማንም ምንም ሳያሳውቁ የግለሰቦቹን የባንክ ሒሳብ ወደ ራሱ ሒሳብ እንዲዛወር አድርጓል ። ድርግቱ ግን በህገ_ወጥ የተደረገና ባለህብቶቹም ምክንያቱን እንደማያውቁ ለምንጫን ገልጸዋል፡፡
‹‹ገንዘቤን በአደራ አስቀምጥልኝ›› ተብሎ የተሰጠው ባንክም፣ ለባለቤቶቹ ሳያሳውቅ አድርግ የተባለውን ማድረጉ አግባብነት የሌውና በሕግም ተገቢ እንዳልሆነ እምነት እንደሌላቸው የገለጹት እነዚህ ምንጮች፣ ሁለቱንም ወገኖች ለማነጋገር ቢሞክሩም ምላሽ የሚሰጣቸው ማጣታቸውን ተናግረዋል፡፡
ምናልባት በፍትሐ ብሔር የተከሰሱበትና የተጠየቁበት ሁኔታ እንዳለ ተጠይቀው፣ ባለሥልጣኑ ከፍተኛ የሆነ ግብር እንዳለባቸው መጠየቁን አስታውሰው፣ የጠየቀው ግብር በተዘጉና ፈቃዳቸው በተመለሱ ድርጅቶች መሆኑን ቀርበው ማስረዳታቸውን ይናገራሉ፡፡
በፍትሐ ብሔር በኩል ጥያቄ የሚቀርብ ቢሆን እንኳን መጥርያ ደርሷቸው ሊከራከሩና መጨረሻው ታይቶ ውሳኔ መሰጠት ሲገባው፣ ያለምንም ማስጠንቀቂያና አፈጻጸም ሒሳብ እንዲዛወር ማዘዝ ‹‹ተገቢ ነው›› ብለው እንደማያምኑ አስረድተዋል፡፡
አቶ ገብረ ኪዳን ገብረ ሥላሴና አቶ ሌንጫ ዘገዬም ተመሳሳይ ድርጊት የተፈጸመባቸው መሆኑንና ሒሳባቸው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለያዩ ቅርንጫፎች በመሆኑ፣ ትክክለኛ የገንዘቡ መጠን ባይታወቅም ገቢ እንዲሆን መደረጉን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
አቶ ከበደ ተሰራ በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በተለያዩ ሒሳብ ቁጥሮች አስቀምጠውት የነበረው በድምሩ 6,199,387.03 ብር፣ ባለቤታቸው ወ/ሮ አልማዝ ጫካ በሦስት የተለያዩ ሒሳቦች በድምሩ 1321.95 ብር፣ ወ/ሮ አልማዝ ጫካ (የአቶ ከበደ ባለቤት) እና ወ/ሮ አልማዝ ሁለቃ (የአቶ አየለ ባለቤት) በጋራ 10 ብር ያስቀመጡ ሲሆን፣ ቀሪው በሁለት የተለያዩ ሒሳብ ቁጥሮች የተቀመጠው ገንዘብ የአቶ አየለ ደበላ ነው፡፡
“የባለሀብቶቹ ገንዘብ በፍርድ ቤት ውሳኔ ለገቢዎች ተፈርዶ ብሆን እንኳን ባንክ ቤት ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ፤ ለተፈረደበት ወገን የፍርድ ትዕዛዙን ሳያሳውቅ የገንዘብ ዝውውር ሊያደርግ አይችልም ነበር” ያሉት አስተያያት ሰጭዎች “ይህ ሁኔታ የስርዓቱን አይን ያወጣ ዘራፍነትን የሚያጋልጥ ነዉ” ብለዋል ።