የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮሞ ህዝብ ላይ አላስፈላጊ ጦርነት ከማካሄድ መቆጠብ አለበት።

(የኦነግ መግለጫ ሓምሌ 20 ቀን 2018ዓም)
(የኦሮሞ ነጻነት ድምጽ/VOL – ሓምሌ 20, 2018) ከኢህኣደግ ውስጥ የተገኘ ተጨባጭ መረጃ እንደሚያመለክተው የኢትዮጵያ መንግስት እንዲሁም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳና አስተዳደሩ በኦነግና በኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ትግል ላይ ሲያካሂዱት ከነበረውና በማካሄድ ላይ ከሚገኙት ጦርነት እየቆሙ አይደሉም። አቶ ለማ መገርሳ፣ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላና ሌሎች ሰዎችም የሚገኙበት አንድ ቡድን የዚህ ጦርነት ጉዳይ በግንባር ቀደምነት እየገፉት እንዳሉም ለመረዳት ተችሏል። ይህ ቡድን ከኦነግ ጋር የተጀመረው የሰላም ድርድር በእንጥልጥል ቆይቶ ቢያንስ ለአንድ ወር በኦነሰ ላይ የሚካሄደው ዘመቻ እንዲቀጥል በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር. ዐብይ አህመድ ላይ ግፊት በማድረግ ማሳመኑምት ተሰምቷል።

ሰሞኑን በኦነግ ሊቀ-መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦነግ ልዑካን ቡድንና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር Dr ዐብይ አህመድ በአስመራ ከተነጋገሩ ወዲህ ኦነግ በበኩሉ ያለው ችግር በንግግር መፍትሄ እንዲያገኝ ሳይቆጠብ እየሰራ ነው። የተኩስ ማቆም አዋጅ እስከማወጅ የሄድነውም ለዚሁ ነው። በኦነግ በኩል ይህን መሰሉ ጥረት በመደረግ ሳለ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል በኦነግ ላይ እየተካሄደ ያለው ጦርነት አላስፈላጊና ለተጀመረው ንግግርም እንቅፋት ሊሆን የሚችል ጦርነት ነው።
ለረዥም ጊዜያት በዚህ ቀጣና የችግሮች ምንጭ ከሆኑት መካከል ኣንዱ የኢትዮጵያ መንግስት የኦሮሞን ህዝብ የነጻነት ጥያቄ በጠመንጃ አፈሙዝ አፍኖ ለማስቀረት መሞከሩ ነው። ይህ ሙከራ ደግሞ ይህን አካባቢ የጦር አውድማና የህለንተናዊ ቀውሶች ምንጭ በኣድረግ ረሃብ፣ ድህነት፣ ስራ-አጥነትና ስደተኝነትን ከማስፋፋት በስተቀር ያስገኘው ጥቅም የለም። ኦነግ ለዚህ ችግር ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት ከሚታገሉት ሃይሎች መካከል ዋነኛውና ከፍተኛ ድርሻ ሲያበረክት የነበረና በማበርከትም ላይ ያለ ድርጅት ነው። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ የለውጥ ተስፋ እንዲስነቅ ያደረገውም የኦሮሞ ህዝብ ነጻነቱን ለመጎናጸፍ በኦነግ እየተመራ በማካሄድ ላይ የሚገኘው ትግል መሆኑ አይካድም።
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ኢምፓየር ውስጥ የተለያዩ ሃይሎች የፖለቲካ ፍላጎት ተናንቆ እየተጋፈጠ ይገኛል። ከፍተኛና ውድ መስዋዕትነት ተከፍሎበት ኣሁን ካለበት ደረጃ የደረሰውን የኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ትግል ከዚህ ውስብስብ ሁኔታ ውስጥ በድል ለማውጣትም ይሁን በቀጣናው ኣጠቃላይ መፍትሔ ለማስገኘት ግለሰብም ይሁን ለኦሮሞ ህዝብ እታገላለሁ የሚል ድርጅት ሁሉ በአሁኑ ጊዜ በብስለትና በከፍተኛ የተጠያቂነት መንፈስ መነቀሳቀስ ይጠበቅበታል። ይህን እውነታ እያወቁ የአቶ ለማ መገርሳ አስተዳደርና ድርጅታቸው OPDO እንዲሁም ሌሎች ሀይሎች የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን፣ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትንና ቄሮን ካላጠፋን በሚል በኦሮሞ ህዝብ ላይ ጦርነት ለማስፋፋት የመረጡበት ምክንያት አይገባንም። እንዲህ ያለው ኣካሄድ ህዝባችን ውድ ዋጋ ከፍሎበት ከዚህ ያደረሰውን የነጻነት ትግል በድል ለመቋጨት ኣይረዳም። በኢትዮጵያ ኢምፓየርና በቀጣናው እንዲሰፍን ለሚፈለገው ዘላቂ ሰላምም ትልቅ እንቅፋት ይሆናል።
ስለሆነም የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በበኩሉ በቅርቡ ያወጀውን የተኩስ ማቆም አዋጅ ስራ ላይ ለማዋል ጥረት እያደረገ የኢትዮጵያ መንግስትም ከዚህ ጦርነትን የማስፋፋት ድርጊቱ ተቆጥቦ ያለው ችግር የተጀመረውን ንግግር በማሳካት እንዲፈታ ሃላፊነቱን እንዲወጣ አጥብቆ ይጠይቃል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s