የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው?

– ትላንት የነበሩት፣ ዛሬ ያሉትና ወደፊት የሚኖሩት ፈተናዎች –

ብርሃኑ ሁንዴ, Ebla 19, 2018ክፍል አስር

የዶ/ር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስተር ሆኖ መመረጥ ኦሮሞዎችን በሀሳብ ለሁለት የከፈለ ይመስላል። ባንድ በኩል ኦሮሞ አራት ኪሎ ስለገባ አሁን ለውጥ ሊመጣ ይችላል ብለው በደስታ እየፈነጠዙ ያሉትና ይህንንም ለውጥ እየጠበቁ ያሉት ሲሆኑ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ወያኔዎች በዚህ መንግስት ውስጥ እስካሉ ድረስ ለውጥ መምጣት አይችልም የሚሉ ናቸው። እኔም በሀሳቤ ሁለተኛው ቡድን ውስጥ ስለሆንኩኝ፣ በዚህኛው ፅሁፍ ውስጥ ኣንዳንድ ጉዳዮችን ኣንስቼ ለመግለፅ እሞክራለሁ።

በኦሮሞ ጠ/ሚኒስተር ስም የወያኔን ስርዓት ለመጠገን የሚደረገው ሙከራ ለውጥ ከማምጣት ይልቅ ለኦሮሞ የሚያመጣው አደጋ ይበልጣል

ከዚህ በፊት በተለያዩ ፅሁፎች ውስጥ ለመግለፅ እንደሞከርኩት፣ ኣንደኛ፥  የአገሪቷ ጠ/ሚኒስተር ኦሮሞ ስለሆነ ለኦሮሞ ሕዝብ ለውጥ መምጣት እንደማይችል እና የኦሮሞ ብሔራዊ ጥያቄ ደግሞ በፍፁም መልስ ማግኘት እንደማይችል ላሰምርበት እፈልጋለሁ። ሁለተኛ፥  ቅርብ ጊዜ በፊንፊኔ ተደርጎ በነበረው “ወገን ለወገን” ኮንዘርት ላይ የተዘፈነው የሃጫሉ ሁንዴሳ ዘፈን situ Araat Kiilootti aana”  ኣንተ ነህ ለአራት ኪሎየምትቀርበው”  የሚለው መልዕክቱ በተሳሳተ መንገድ መረዳት የለበትም። ለኔ እንደሚገባኝና እንደምረዳው ሃጫሉ ይህንን መልዕክት ማስተላለፍ የሞከረው “ቄሮ ኦሮሞ (Qeerroo Oromoo) ትግልህን ኣጠንክር፣ ከውጭ ምንም አትጠብቅ፣ ወያኔዎችን እያንበረከክ ያለሀው ኣንተ ነህና ይህንን ስርዓት ገርስሰህ ኣራት ኪሎ የምትገባው ኣንተ ነህ” ለማለት እንጂ ኣንድ ኦሮሞ ይቅርና መቶ ኦሮሞዎች ጠ/ሚኒስተር ሆነው አራት ኪሎ ስለገቡ ወያኔዎች ባሉበት፣ ይህ ሰው በላ ስርዓት በቦታው እስካለ ድረስ ኣንድም ለውጥ መምጣት አንደማይችል ለመግለፅ ነው።

አዲሱ ጠ/ሚኒስተር ዶ/ር አብይ በስራ አሳይቶ ለውጥ ማምጣት ቀርቶ፤ ጅምሩ ራሱ ጥሩ እንዳልሆነና የኦሮሞን ሕዝብ ፍላጎት ማሟላት እንደማይችል ብዙ ማስረጃዎችን መጥቅስ ይቻላል። እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ዶ/ር አብይን እሱ እያልኩ ፅሁፌ ውስጥ ስገልፅ እንደ ኣንድ የኦሮሞ ልጅና ወንድም በማየቴ ስለሆነ እንደ አገሪቷ ጠ/ሚኒስተር እሳቸው ብዬ መጥቀስ አልፈልግም። ወደ ማስረጃዎቹ በመመለስና ኣንዳንድ ምሳሌዎችን ለመጥቀስ፥

  • ) እንደ ጠ/ሚኒስተር የተመረጠበት ቀን ባደረገው ንግግር ውስጥ እጅግ የሚያሳዝኑ ነገሮችን ተናግሮ ነበር። ይህም ያለፉትን የኢትዮጵያ አፄዎችን በተለይ ደግሞ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ እጅግ የሚጠላና እንደ አውሬ የሚታይ አፄ ሚኒልክን በመጥቀስ፤ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ዘግናኝ ድርጊቶችን ያስፈፀመውን አፄ ስራውን ማድነቁ ይህ በእውነቱ የታሪክ ስህተት ነው። የምገርመው የኣኖሌንና የጨለንቆ ሀውልቶችን አምኖበት ለመታሰቢያ ያሰራው የራሱ ድርጅት ኦሕድድ (OPDO) መሆኑን ራሱ አያወቅ፣ ይህንን ታሪካዊ ኣሳዛኝ ድርጊት ረስቶ፤ የድሮው ስርዓት ናፋቂዎችን ለማስደሰትና ትኩረታቸውን ለመሳብ ብሎ የኦሮሞን ቁስል የሚነካ ንግግር ማድረግ ትልቅ ስህተት ነው።
  • ለ) የአገሪቷ ጠ/ሚኒስተር ሆኖ በሕጋዊ መንገድ ከተመረጠ በኋላም፣ ውሎ ሳያድር አዲስ ካብኔ በማቋቋም፣ ሕዝቡ ከሱ እየጠበቀ ያለውን ስራ መጀመር ነበረበት። ይህ ግን እስካሁን አልሆነም። በሱ መንግስት ስር ይሀው ዛሬም የኦሮሞ ሕዝብ በአጋዚ ታጣቂ ኃይሎች በየቦታው እንደ ዛፍ ቅጠል እየረገፈ ነው ያለው። በኦሮሞ ላይ እየደረሰ ያለው እስር፣ ስቃይና ግድያ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ሄደ እንጂ ሕዝባችን ሰላም ኣግኝቶ አያውቅም።
  • ሐ) በ ሀ) ስር እንደ ጠቀስኩት፣ ቶሎ አዲስ ካብኔ አቋቁሞ፣ በዚህ በኩል የአገሪቷን ሕገ መንግስት በመጠቀም ይህን ሕገ ወጥና ፀረ ሕዝብ የሆነውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማንሳት የመጀመሪያና አስቸኳይ ስራው መሆን ነበረበት። ይህንን የኦሮሞን ሕዝብ ሕልውና አደጋ ውስጥ የከተተው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ ከየትኛውም ጉዳይ ቅድሚያ ማግኘት ያለበትን ትቶ በየክልሎቹ ለጉብኝት መጓጓዝ በእውነቱ አሁን አስፈላጊ ኣልነበረም። ይህ መሆን የነበረበት በመጀመሪያ የሕዝቦች ስላምና ደህንነት ስረጋገጥ ነበር።
  • መ) ባንድ በኩል ወደ ሱማሌ ክልል ሄዶ፣ የኦሮሞን ሕዝብ ያስጨረሰና እያስጨረስ ካለው አብዲ ኢሌ ከሚባለው እብዱ ሰውዬ ጋር መተቃቀፍና ሰላም እንዳለ ማስመሰል ለኦሮሞ ትልቅ ሀዘን ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የአጋዚ ታጣቂዎች ሌት ተቀን በሕዝባችን ላይ አሰቃቂ ድርጊት እየፈፀሙ በሚገኙበት ወቅት ወደ ትግራይ ክልል በመሄድ ሕዝባቸውን ለማስደሰት ሁሉን ጥረት ማድረግ በምን ሞራል ይሁን? እንደ ውሃ እየፈሰሰ የነበረውና ያለው የኦሮሞ ልጆች ደም፣ እየተከሰከሰ ያለው የኦሮሞ አጥንት ትንሽ እንኳን አይሰማውም?
  • ሠ) ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስተር ሆኖ በሚመራው የወያኔ መንግስት ስር ይሀው ለሁለተኛ ዙር በሞያሌ የኦሮሞ ልጆች ደም ዳግም ፈሷል፣ ሕይወትም ኣልፏል። ምን ያህል የኦሮሞ ልጆች በተለይም ደግሞ ቄሮ ኦሮሞ በየቀኑ ወደ እስር ቤት እየተወረወሩና እየተሰቃዩ እንደሆነ፤ ምን ያህል የኦሮሞ ሴቶች በዕድሜ በጣም አነስተኛ የሆኑትን ሕፃናት ሴት ልጆችን ጨምሮ በየቀኑ እየተደፈሩ፣ እያለቀሱና እየደሙ መሆናቸውን እግዚኣብሔር ብቻ ነው የሚያውቀው። ይህንን አስቃቂ ድርጊት ማስቆም የጠ/ሚኒስተሩ የመጀመሪያ ስራው መሆን ነበረበት።

እንግዲህ እነዚህ እውነታዎች መሬት ላይ እያሉ፤ ገና ከጅምሩ ነገሮች ጥሩ ባልሆኑበት ሁኔታ ውስጥ አንድ ለውጥ ይመጣል ብለው ማሰብ ትርጉሙ ምንድነው? ይህ ጉዳይ “ጥሩ እንጀራ በምጣድ ላይ ይታወቃል” “Biddeenni gaariin eeleerratti beekama” የሚባለውን አንድ የኦሮምኛ ተረት ያስታውሰኛል። ዶ/ር አብይ ይህ ሊወድቅ የገደል አፋፍ ላይ ያለውን የወያኔን ስርዓት ለማዳንና መልሶ ጉልበት እንዲያገኝ ለማድረግ ከልሆነ በስተቀር፤  ለኦሮሞ ሕዝብ የሚፈለገውን ለውጥ ማምጣት ቀርቶ፣ የሕዝቡን ስላምና ደህንነት እንኳን ማስጠበቅ ኣልቻለም፣ አይችልምም የምል እምነት ኣለኝ። ይህ እውነታ ለጠላትም ሆነ ለዘመድ ለሁሉም ግልፅ መሆን ኣለበት።

የኦሮሞ ሕዝብ በሚመጡና በሚያልፉት የሀበሾች መንግስታት ስር ተመሳሳይ ስቃይ ቢደርስበትም፣ በወያኔ ስርዓት ውስጥ ግን ከምን ጊዜውም የበለጠ ስቃይና መከራ እየደረሰበት እንደሆነ የማይታበል ሀቅ ነው። ሌላው እንኳን ቢቀር ሕዝባችን በሰላም ወጥቶ መግባት፣ በቀዬውና በቤቱ በሰላም መኖር ኣቅቶት፣ እንደ አውሬ እየተሰደደ፣ በየቦታው እየታሰረና አየተገደለ ይገኛል። በኦሮሞ ሕዝብ ላይ በወያኔ የተከፈተው ዘመቻ የዘር ማጥፋት ጦርነት እንደሆነ ግልፅ መሆን ኣለበት። የወያኔ ኣንደኛ ጠላት ኦሮሞ ሆኗል ማለት ነው። ይህ ሰው በላ ስርዓት በዚሁ ከቀጠለ በኦሮሞ ላይ የሚደርሰው ጥፋትና አደጋ እየጨመረ እንደሚሄድ ምንም ጥርጥር የለውም። ስለዚህ ኦሮሞ ሰላም እንዲያገኝ ይህንን ስርዓት ስሩን ነቅሎ መጣል ብቻ ነው መፍትሄ የሚሆነው።

የኦሮሞ የነፃነት ትግል በተለይም ደግሞ በቄሮ እየተደረገ ያለው ትግል የወያኔን ስርዓት ማፍረስ ላይ ማተኮር ኣለበት እንጂ ካሁን በኋላ ለውጥ ይመጣል ብለው መጠበቅ በጥፋት ላይ ጥፋት እየጨመሩ መሄድ ይሆናል። የበለጠ አደጋንም ሊያስከትል ይችላልና። በኦሮሞ ጠ/ሚኒስተር ስም ለኦሮሞ ለውጥ ይመጣል ብሎ ማሰብ ያለንበትን ሁኔታ ኣለመረዳት ነው። ኦሮሞ ከምን ጊዜውም በበለጠ ነቅቶ፣ ተደራጅቶ፣ ጉልበቱንና አቅሙን አጠናክሮ፤ ይህንን ስርዓት እስከሚያስወግድ ድረስ በየትኛውም መንገድ ይህንን መራራ ትግል መቀጠል ኣለበት እንጂ በሌሎች ነግሮች መታለል የለበትም። ይህ የወያኔ ስርዓት ከወደቀ በኋላ ደግሞ ሰፊው ሕዝብ ያለምንም ተፅዕኖ ለሱ የሚሆነውን ለመወሰን ማለትም የራሱን ዕድል በራሱና ለራሱ ለመወሰን ሙሉ መብቱ መጠበቅ ኣለበት። ይህንን ጉዳይ በሚመለከት በሚቀጥለው ፅሁፍ ውስጥ ሀሳቤን ኣቀርባለሁ።

ተመልሰን እስከምንገናኝ ደህና ሁኑ።

9. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ዘጠኝ
8. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ስምንት
7. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ሰባት
6. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ስድስት
5. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አምስት
4. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አራት
3. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ሦስት
2. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ሁለት
1. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አንድ

1 thought on “የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው?

  1. Ilaalcha haqa gaarii, wayitaawaa fi haqa qabeessadha. Jabaadhaa…qalamni keessan hin gu’in!!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s