የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያወጀውን የጦርነት ኣዋጅ በተመለከተ የተሰጠ ኣጭር መግለጫ

የወያኔ ኢሕኣዴግ/ሕወሃት መንግስት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ኣውጆ ለማጽደቅ እየስራ ያለውን የጦርነት ኣዋጅ በመቃወም የተሰጠ ኣጭር መግለጫ

የካቲት 20 ቀን 2018ዓም

ኣምባገነኑ የወያኔ መንግስት፡ በኦሮሚያ ብሄራዊ የጭቆና ፍጻሜ ንቅናቄ ትግል ተንኮታኩቶ ከውድቀቱ ኣፋፍ የሚገኘው የኢህኣዴግ ስርዓት በጠመንጃ ኣፈሙዝ እራሱ ከውድቀት ለማትረፍና ሲፈጽም የነበረውንና እየፈጸመ ያለውን የዘር-ማጥፋት (ጄኖሳይ) ወንጀል ይበልጥ ለማስቀጠል በኦሮሞ ህዝብና ባጠቃላይ በሃገሪቷ ህዝቦች ላይ ያወጣውን የጦርነት ኣዋጅ ኣጽድቆ የሃገሪቷን ኣስተዳደር ከስድስት ወራት በላይ ለሚሆን ጊዜ በኮማንድ ፖስት ስር ኣስገብቷል።

ኣሁን ባወጣው የጦርነት ኣዋጅ ቀደም ሲል ለስም ብቻ የነበረውን የሃገሪቷን የኣስተዳደር ስርዓት ባጠቃላይ በወታደራዊ ኣገዛዝ ስር በማስገባት የሰብዓዊና ዲሞክራሲ መብቶችን መርገጡን እንዲሁም የዘር-ፍጅት ወንጀሉን በቀጣይነት ለማካሄድ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል። ይህ የጦርነት ኣዋጅ በህዝባችን ላይ እንዳይጸድቅ ከያለንበት ሁሉ ማውገዝና ኣስፈላጊው ጫና እንዲደረግ ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ ለኦሮሞ ህዝብና ለመላው የሃገሪቷ ህዝቦች ጥሪውን ያስተላልፋል።

 

 

  1. የሃይማኖት ኣባቶች፣ ኣባ-ገዳዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ባለሃብቶችና ሁሉም የሃገሪቷ ህዝቦች ይህ የጦርነት ኣዋጅ የህዝባችንን ደም ማፍሰስ፣ ዝርፊያን ለማጠናከር፣ የዘር-ማጥፋት የግድያ ወንጀልን በህዝባችን ላይ ለመፈጸምና የህዝቡን ተፈጥሮኣዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ሁሉ የሚገድብ ስለሆነ ያካለችሁበት ቦታ ሁሉ ከጎናችን ቆማችሁ በማውገዝ እንዲከሽፍ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!!

 

  1. ሁሉም የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶችና ከህዝቦቻቸው ነጻነትና የዲሞክራሲ መብቶች መከበር የሚፋለሙ ሁሉም የሃገሪቷ የፖለቲካ ድርጅቶች በያላችሁበት ቦታ ሁሉ፡ ይህ በሃገሪቷ ህዝቦች ላይ በተለይ ደግሞ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የታወጀው የጦርነት ኣዋጅ እንዳይጸድቅ ከሁሉም ኣቅጣጫ በመስራት የህዝባችን ድምጽ በመሆን እንድናከሽፍ ጥሪ እናቀርባለን።

 

  1. የሃገሪቷ ፓርላማ ኣባላት ይህ የኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ እንዲጸድቅ ልትሰበሰቡ ስለሆነ፡ በድምጻችሁ ከኣብራኩ በወጣችሁት ህዝብ ላይ የዘር-ማጥፋት ወንጀል እንዲፈጸም፣ የሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ከህዝቡ ለመግፈፍ ልትወስኑ ስለሆነ የጦርነት ኣዋጁ እንዳይጸድቅ እንድትቃወሙት እንጠይቃለን። ይህ የጦርነት ኣዋጅ ከጸደቀ በጦር ሃይል ሲፈጸሙ ለነበሩትና ለወደፊትም ለሚፈጸሙት ወንጀሎች በታሪክም በህግ ፊትም ከመጠየቅ እንደማታመልጡ እናሳስባለን!

 

  1. የጨፌ ኦሮሚያና የኦሮሚያ የኦዳ-ሸነን ምክር ቤት ኣባላት ይህንን በህዝባችን ላይ የታወጀውን የጦርነት ኣዋጅ በሙሉ ድምጽ እንዲቃወም ጥሪ እናቀርባለን። ይህ የጦርነት ኣዋጅ ከጸደቀ በጦር ሃይል ሲፈጸሙ ለነበሩትና ለወደፊትም ለሚፈጸሙት ወንጀሎች በታሪክም በህግ ፊትም ከመጠየቅ እንደማታመልጡ እናሳስባለን!!

 

  1. በኣምባገነኑ የወያኔ ኢህኣዴግ መንግስት የጦር ሃይል ውስጥ የምትገኙ የኦሮሞ ዜጎችና ሌሎችም የተጨቋኝ ህዝቦች ተወላጆች ይህ ኣዋጅ የሃገርን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ሳይሆን ለኢህኣዴግ የፖለቲካ ድርጅት ጥቅም ብቻ ተብሎ የታወጀና ስርዓቱን ከውድቀት ለመታደግ በህዝባችን ላይ የተላለፈ የጦርነት ኣዋጅ መሆኑን በመገንዘብ እየተሰጣችሁ ያለውን መመሪያና ትዕዛዝ ውድቅ በማድረግ የኣብራኩ ክፋይ ከሆናችሁት ህዝባችኑ ጎን በመቆም የነጻነትና የሃገር ባለቤትነት መብት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ሃገራዊና የዜግነት ግዴታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እያስተላልፍላችኋለን!!

ማሳሰቢያ: የኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ትግል የኦሮሞ ህዝብ ነጻነቱን እስኪጎናጸፍና የኦሮሚያ ሉዓላዊነት እስከሚረጋገጥ ድረስ(ህዝባችን  እራሱን ችሎ የራሱን እድል በራሱ እስከሚወስን ድረስ) በጦር ሃይልና በጠመንጃ ኣፈሙዝ የሚገታ ኣይደለም!!

ይህ የጦርነት ኣዋጅ ጸድቆ ስራ ላይ የሚውል ከሆነ የኦሮሚያ ብሄራዊ የጭቆና ፍጻሜ ንቅናቄ ሊከተል የሚገባውና ተጋፍጠን በመፋለም ነጻነታችንና የሃገራችንን ሉዓላዊነት የምንጎናጸፍበት እስትራቴጂ ስላለን የኦሮሞ ወጣቶች፡ ቄሮ፣ መላው የኦሮሞ ህዝብና ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ከያላችሁበት ቅድመ-ዝግጅት፣ ንቃት፣ ኣንድነታችሁንና መግባባታችሁን ይበልጥ እንድታጠናክሩ ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ መልእክቱን ያስተላልፋል!!

 

ድል ለኦሮሞ ህዝብ

ዘመኑ የጭቆና ፍጻሜ ዘመን ነው!!

የቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ ኣመራር

1 thought on “የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያወጀውን የጦርነት ኣዋጅ በተመለከተ የተሰጠ ኣጭር መግለጫ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s