በኣዲስ መንገድ የጀመረው የኦሮሞ ህዝብ ኣመጽ ከገበያ ኣድማ ቀጣይነት ወዳለው የጭቆና ፍጻሜ ኣመጽ ይሸጋገራል!(የቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ መግለጫ የካቲት 14, 2018 ዓም)

በኣዲስ መንገድ የጀመረው የኦሮሞ ህዝብ ኣመጽ ከገበያ ኣድማ ቀጣይነት ወዳለው የጭቆና ፍጻሜ ኣመጽ ይሸጋገራል!

( የቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ መግለጫ የካቲት 14, 2018 ዓም)
የኣኩሪ ታሪክ ባለቤት የሆነው የኦሮሞ ህዝብ ከኣንድ ምዕተ– ዓመት በላይ የተጫነበትን የባእዳን ጫናና ባርነት ይብቃ! በሚል ተነስቷል። ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ ኣዲሱን ዓመት 2018 እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ ባካሄደው የኣመራር ስብሰባ ጥር 11 ቀን 2018 ዓም ለመላው የኦሮሞ ህዝብ “”ባስተላለፈው የቄሮ ቢሊሱማ ጥሪ ላይ እንዳእቅድ ከወጣቸው መካከል የኦሮሞ ህዝብ የመብት ጥያቄ ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ የጭቆና ፍጻሜ ኣመጹን ለመቀጠል ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል።
ቄሮ ቢሊሱማ ያስተላለፈውን ጥሪም መላው የኦሮሞ ምሁራን፣ ነጋዴዎች፣ ኣርሶ ኣደሮችና ተማሪዎች በኣንድነት በመነሳት በዚህ ዓመት ውስጥ የጭቆና ስርዓት ፍጻሜን ለማሳካት በስራ ላይ የሚውልና ታሪካዊ ጥሪ ኣስተላልፈናል። በዚሁ መሰረት ከየካቲት 12 ቀን 2018 ዓም ኣንስቶ እስከ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓም ድረስ በተለያዩ የንግድ ስራዎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሁሉም የኦሮሞ ነጋዴዎች የገበያ ኣድማ እንዲመቱ በብቃት ሲሰራበት ነበር። የገበያ ማቆም ኣድማው ዕለት ሳይደርስ የተሰራጩትን ወረቀቶችና የተላለፈውን ጥሪ በመቀበል በንግድ የሚተዳደረው የኦሮሞ ህዝብ ለ 3 ቀናት ላካሄደው የገበያ ኣድማ ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ ያለውን ታላቅ ኣክብሮትና ኣድናቆት ይገልጻል።

የገበያ ማቆም ኣድማው ህዝቡ ምርቱንና ኣገልግሎቱን ወያኔና ሸሪኮቹን ወደ መንፈግ በማሸገገር እስከ ነጻነት ተጠናክሮ መካሄድ ኣለበት። ይህን ቄሮ ቢሊሱማ ጥር 11 ቀን 2018 ዓም ባስተላለፈው ጥሪ መሰረት ህዝቡ በብድር መልክ የሽያጭና ግዢ ስልት እርስበራሱ መረዳዳትና መተባበር ይኖርበታል። ይህ ቡና ያላቸውና ጤፍ ለመሸጥ የሚሄዱ ሰዎች ምርቶቻቸውን መቀያየር መኖር ኣለበት ማለት ነው። የገበያ ማቆም ኣድማው እንደታቀደው ዛሬ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓም ቆሞ ቀጣይነት ባለው መልኩ የጭቆና ፍጻሜ ኣመጽ እንዲካሄድና ጨቋኙን መንግስት ለማንበርከክ ፍልሚያው እንዲፋፋም ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ ጥሪውን
ያቀርባል።
በሁሉም የኦሮሚያ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ የቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ መዋቅሮችና የቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ ንቅናቄ ኣካል ፖሊሶች በኣንድነትና በስነ– ስርዓት ህዝባዊ ኣመጹን ስታካሄዱ እንደነበራችሁት ሁሉ ኣሁንም የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ ኣመጹን በመልካም ኣመራርነት እንድትቀጥሉበት እንጠይቃለን።
ዘመኑ የጭቆና ፍጻሜ ዘመን ነው!
ድል ለኦሮሞ ህዝብ!
የቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ ኣመራር
ፊንፊኔኦሮሚያ
የካቲት 14,2018 ዓም

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s