የእ/ህአደግን ልብ እንኳን ሰዉ እግዝያብሔርም አያዉቀዉም!
ከመተከል ቀሮዎች የተሰጠ መግለጫ!
እህአደግ ለረዥም ዘመናት ሲክዱት የነበሩትን በሀገራችን ሽብርተኛ እንጂ የፖለትካ እስረኞች የሉም ብለዉ ለአለም መንግስታት እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሰወረዉ የነበሩት በአፍርካ ቀንድ ያሉትን የተለያዩ የሽብር ሃይላትን ለመደምሰስ በሚል ሰበብ ከምዕራባዉያን የሚወስዱትን ከፍተኛ መጠን ያለዉን ዶላር በሀገራቸዉ ዉስጥ ያሉትን ብሄር ብሔረሰቦች ስያጋጩበት፣ የትጋራይን ክልል ስያለሙ፣ የወያኔ ደህንነት መስርያ ቤቱንና የመከላለያ ሃይል ስያደራጁና ለትግራይ ተወላጅ የወያኔ ቅጥረኞች በሃገራችን ህዝብ ስም ከምዕራባዉያን ስወስዱት የነበሩት ብድር ስያተረማምሱ የነበሩት እዉነተኛ የህዝብ ልጅ የሆኑትን የኦህደዴድና የብአዴን፣ የጋምበላና፣ የሶማሌና ሌሎች የኢትዮጽያ ልጆችን በማቧደን ሁለተኛ ህዊሃትን በሌሎች ድርጅቶች ዉስጥ በመፍጠር ሀገራችንን ለ26 ዓመታትና ከዚያ በላይ ሲመጣትና ስያጎሳቅሏት የኖሩ ብሔር ብሄረሰቦችን እርስበርስ ሲያጋጩና ከፍተኛ ደም ሲያፈሱ የነበሩት ብዙ ቁጥር ያላቸዉን የዪኒቨርሲቲ ተማርዎችን ሰልፍ በወጡበት በወያኔ አጋዚ ክፍለ ጦር ሰራዊትና የደህንነት ሹማምንት እራት ሲያደርጉ የነሩት ለ26 ዓመታት ሃገራዊ ስሜት የለሌላቸዉ ስለ ኢትዮጵያ አንድም ቀን አፋቸዉ ይሁን ስራቸዉ የማይመሰክር የሀገራችን ህዝብ ለእነኝህ ዓመታት አንድ ቀን ቀልብ ይገዛሉ በማለት ሲታገስ ብኖርም ቅሉ ትእግስቱን የጨረሰ የሀገር ቄሮ(Qeerroo) አና ጃኖ በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ እያደረገ ያለዉ ትግል መቋቋም ስያቅታቸዉ ቀብሰ ብስ መግለጫ እህአደግ መስጠቱ ጅብ ካለፈ ዉሻ ጮሄች ከሚባለዉ ተረት ዉጭ የሀገር ወጣት ጀግኖችን ትግል ወደ ኃላ ይመልሳል ብለዉ አስበዉ ከሆነ ዳግም የታርክ ስህተት እንዳትሳሳቱ ለእነኝህ ሆዳም የወያኔ ቅጥረኞች ላሳዉቃችሁ እፈልጋለሁ፡፡
በመቀጠልም ወደ መግለጫዉ አንዳድ አስቅኝ ንግግሮች ሳልፍ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየዉ ሲናገሩ “ሀገራዊ አንድነትን ለመፍጠር ሲባል የፖለትካ አስረኞች እንድፈቱ ተስማምተናል፣ ማዕከላዊን ዘግተን ሙዝየም እናደርጋለን” ብለዋል፡፡ ከዚህ መነሻነት በመጀመሪያ ደረጃ ሰፊ ቁጥር ያለዉ ህዝብ የታሰረበት የሞተበትን ጥያቄ መመለስ ነዉ ወይስ አስረኞችን መፍታት ነዉ ሀገራዊ አንድነትን የበለጠ የሚያጠናክር? እነኝህ ወገኖቻችን የታሰሩበት ዓላማ ለሀገራችን የሚበጅ ፖሊሲ ፍለጋ፣ የሥርዓት ለዉጥ ፍለጋ፣ ደሞክራስያዊ ስርዓት ፍለጋ መሆኑን በእዉኑ የእህአደግ ካድረዎች አጥተዉት ነዉ ወይስ አሁንም በሌላ ማልያ ህዝቡን ለመደለል ፈልገዉ ነዉ? ማዕከላዊን እንዘጋለን ሲሉ መነሻ ሃሳባቸዉስ ምን ነበር? በደርግ ጊዜ ዜጎች ብዙ ስቃይና እንግልት ሲደርስባቸዉ ስለነበር ይህ በህዝባችን ዉስጥ ጥሩ ዓመለካከት አልፈጠረም፡፡ ይህ የደርግ ማዕከላዊና ሌሎችን የእህአደግ ማዕከላዊዎች ልታወቁ ይገባል ከሆነ ትክክለኛዉሳኔ ነዉ። ነገር ግን ለሎች የህወሃት ደህንነት ሹማምንቶች ዜጎቻችን የሚያሰቃዩበት፣ ወንዶች የሚደፈሩበት፣ ሴቶች ፆታዊ ጥቃት የሚደርስባቸዉ፣ አካላዊ ጉዳት እንዲሁምለ ሎችኢሰብአዊና ግፍ የሚፈጸምበት ላዕላይ ማዕከላዊዎች በሀገራችን ዉስጥ የሉም ወይ አሁንም እህአደሀግ ይህንን ህዝብ ሞኝ ልያደርግና በለሌላ መደለያ ሊደልል ፈልጎ ከሆነ “ቀሮዎችና ጃኖዎቹ መስሚያችን ጥጥ ነዉ” ብለዋል፡፡
እነ ለማ መገርሳ እና ገዱ አንዳረጋቸው ብሎም በመከላከያና ደህንነት መስሪያ ቤት ያሉ ለ እዉነተኛ የዲሞክራሲ ግንባታ የሚታገሉትና ለኢትዮጵያ ህዝቦች የሚታገሉ ዜጎች በእዉነት ህወሀት እህአደግ ለለዉጥና የህዝብን ጥያቄ የቆረጡ ከሆነ፡-
I. በደህንነት መስሪያ ቤቱ ዉስጥ ያሉ ቁልፍ የስልጣን ክፍያዎች ለ እዉነተኛ የ ኢትዮጵያ ህዝቦች በማስረከብ የመዉጣት እርምጃ አለባቸዉ፡፡
II. በተመሳሳይ መልኩ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ዉሰጥ ያሉትን ቁልፍ የጦር መኮንን የሃላፊነት ስፍራዎችን ለንፁሀን የሀገሪቱ ልጆች በማስረከብ መዉጣት አለበቸዉ፣
III. በሀገሪቱ ዉስጥ ያሉትን ከፍተኛ የኢኮኖምና እንቨስትመንት ሴክተሮችን ለሌሎቹ የሀገርቱ ህዝቦች በፍትሃዊነት ተጠቃሚ የሚሆኑበት መንገድ መመቻቸት አለበት፣
IV. የወያኔ አጋዚ ክፍለ ጦር የሰራዊት አባላት በንጹሃን ቄሮዎችና ተቃዉሞ ባሰሙት የሀገርቱ ልጆች ላይ በመተኮስ ለተገደለባቸዉ ቤተሰቦቻቸዉና አካል ጉዳት የደረሱባቸዉ ወገኖቻችን ካሳ እንድከፈልላቸዉና ይህንን ህገ-ወ ጥ ተግባር የፈጸሙትና ትዕዛዝ የሰጡት አባላት ለፍርድ መቅረብ አለባቸዉ
V. በሶማሌ፣ በኦሮሚያ እንዲሁም በቤንሻንጉል ከማሽ ዞን በተከሰተዉ ግጭት ምክንያት ለተፈጸመዉ የብዙ ህዝብ እልቂት ምክንያት የሆኑት የወያኔ ከፍተኛ አመረርና ቅጥረኞች በአስቸኳይ ለፍርድ መቅረብ አለባቸዉ፣
VI. በሀገራችን ዉስጥ ለብዙ ዓመታት ወያኔ ዜጎቻችንን ሲያስፈራራ፣ ሲያሰቃይ፣ ወደ ማረሚያ ቤትና ጊዜያዉ የማሰቃያ ማዕከሎች ሲወረውሩ የነበረሩት ትዉልድ ገዳዩ የወያኔ ጸረ ሽብር አዋጅ በፓርላማዉ በአስቸኳይ መሻር አለበት፣
VII. በኦሮሚያ ፣አማራ፣ ጋምቤላ፣ ቤንሻንጉልና በደቡብ ክልሎች የተዘረፉት የሀገርቱ ህዝቦች ሃብት በአስቸኳይ መመለስ አለባቸዉ፣
VIII. ኢ.ህ.አ.ደ.ግ ይቅርታ በጠየቀባቸዉ ችግሮች ሰበብ እንዲፈቱ የተወሰነዉ የፖለትካ እስረኞች ካሳና መቋቋሚያ በመንግስት በኩል ሊደረግላቸዉ ይገባል፣
IX. ኢ.ህ.አ.ደ.ግ በእዉኑ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ለመገንባት የወሰነና ይህንን ለማድረግ ቁርጠኛ አቋም ከያዘ፤ በሀገራችን ዉስጥ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ከተፈለገ በሀገራችንና ከሀገራችን ዉጭ በሰላማዊና በትጥቅ ትግል ነፊጥ አንግበዉ እየታገሉ ያሉትን የፖለትካ ፓርትዎችን በሙሉ ለፖለትካ ድርድር በአስቸኳይ መጥራት አለባቸዉ።
ማሳሰቢያ፤
ለረዥም ዘመን በብዙ መስዋትነት አጥንት ተከስክሶና ደም ፈሶ ዜጎች እየታሰሩበትና እየተሰቃዩበት የመጣዉን ትግል ዛሬ የእ.ህ.አ.ደ.ግ ማዕከላዊ ኮሚቴዎች እንደማናዉቃቸዉ መልአክ መስለዉ በቴለቨን መስኮት ብቅ በማለት በሰጡት ፌዝ ወይም መግለጫ እንበለዉ ብቻ ማንኛዉም ቱሪናፋ በመደለል ለድል የተቃረበንዉን ትግል ወደ ኋላ በመተዉ የታርክ ተጠቃሽ እንዳንሆን መጠንቀቅ አለብን በማለት የመተከል ቀሮዎች በሀገርቱ ዉስጥ ያሉትን ቄሮና ጃኖ ታጋዮችን እናሳስባለን፣
በመቀጠልም በኦ.ህ.ደ.ድና ብአዴን ብሔራዊ ፓርትዎች ዉስጥ ያሉት የክልሎች ልዩ ሃይል አባላትና ፖልሶች የተጀመረዉን ትግል ወደ ኃላ በመተዉ በእህአደግ መደለያ ዜጎቻቸዉ ላይ ግፍና በደል እንዳይፈጽሙ ትግሉን በጀመሩት በተለያዩት መንገዶች እንዲቀጥሉና የታርክ ተጠቃሽም እንዳይሆኑ ወንድሞቻቸዉና አባቶቻቸዉ አጥንታቸዉንና ደማቸዉን የከፈሉበት ትግል በአስቸኳይ በመቀላቀል ለወያኔ ቀብር እንዲዘጋጁ እናሳስባለን፡፡
ድል ለኦሮሞ ህዝብ!
ድል ለመላዉ የጭቁኑ ህዝብ!
ከመተከል ቀሮዎች የተሰጠ መግለጫ!