ደም እየጠጣ ያደገ እስከ ዕለተ-ሞቱ ድረስ ደም ካልጠጣ ሊኖር ኣይችልም የወያኔ ጦር ሃይል በኦሮሞ ዜጎችና በሌሎችም ብሄር ተወላጆች ላይ እየፈጸመ ያለውን ዘግናኝ ግድያ ኣጥብቀን እናወግዛለን

ደም እየጠጣ ያደገ እስከ ዕለተ-ሞቱ ድረስ ደም ካልጠጣ ሊኖር ኣይችልም

የወያኔ ጦር ሃይል በኦሮሞ ዜጎችና በሌሎችም ብሄር ተወላጆች ላይ እየፈጸመ ያለውን ዘግናኝ ግድያ ኣጥብቀን እናወግዛለን

የቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ መግለጫ

 የወያኔ መንግስት እኣአ በ1991ዓም በኣሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ሱዳንና በሌሎችም በመንግስታትና ሃይሎች እገዛ በጦር ሃይል የኢትዮጵያን ኢምፓዬር የፖለቲካ ሃይል ተቆጣጠረ። ወደ ስልጣኑ በመውጣቱና ስልጣኑን ከተቆናጠጠበት ጊዜ ኣንስቶ ውሎ ሳያድር የኦሮሞ ልጆችን ደም መጠጣትን ስራዬ ብሎ ተያያዘው። በነጌሌ ቦረና ካፈሰሰው የገመቺስ ዳባ ደም ጀምሮ በድሬደዋ የኦነግ ጽ/ቤት ውስጥ ያፈሰሰውን የኦሮሞ ልጆች ደም ጨምሮ ባለፉት 26 ዓመታት የወያኔ መንግስት ሲጠጣ ዛሬን የደረሰውን የኦሮሞ ልጆች ደም መለስ ብለን ካየን የኦሮሞ ዜጎች ደም ያልፈሰሰበት ቀን ኣልነበረም ብንል ማጋነን ኣይሆንም። ለዚህ ድርጊቱ ስርዓቱን ወደ ስልጣን ካወጡት ከፍተኛ ድጋፍ ኣግኝቷል ዛሬም በማግኘት ላይ ነው። በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ልጆችም ደም ከማፍሰስ ተቆጥቦ የማያውቀውና የዚህ መንግስት እስትንፋስ እስካለ ድረስ ደም መጠጣቱን የማያቆም መሆኑ ለሁሉም ግልጽ ነው።

ባለፉት ቅርብ ጊዜያት የኦሮሞ ልጆች ደም ከዚህ ቀጥሎ ባሉት ኣካባቢዎች በወያኔ ጦርና ደህንነት ሃይሎች መፍሰሱ ተጨባጭ እርምጃና የሰሞኑ ዘግናኝ ድርጊት ነው።

 1. በወያኔ በሰለጠኑ፡ በታጠቁና በተሰማሩ የልዩ ፖሊስ ጦር ኣባላት በምስራቅ ኦሮሚያ ድንበር ኣካባቢ በሚኤሶ፡ ቦርዶዴ፡ መዩ-ሙሉቄ፡ ጃርሶ ቁምቢ፡ ጉርሱምና በሌሎችም ኣካባቢዎች በመቶዎች የሚቆጠር ህይወት ተቀጥፎ ደም ፈሷል። በደቡብ-ምስራቅ ኦሮሚያ ሳዌና፡ ቤልቶ፡ ባሌ፡ ዳዌ-ቃቸን፣ መደ-ወላቡን በመሳሰሉት ውስጥ የኦሮሞ ልጆች ህይወት ተቀጥፎ ደም ፈሷል። በደቡብ ኦሮሚያ ቦረናና ጉጂ ውስጥ በበርካታ ኣካባቢዎች ህይወት ተቀጥፎ በመቶዎች የሚቆጠር ዜጎች ደም ፈሷል።
 2. በሰሜን ሸገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ሰልፍ ወጥተው ጥይቄያቸውን ሲያቀርቡ የነበሩ የኦሮሞ ዜጎች በወያኔ ጦር ሃይል ተገድለው ደማቸው ፈስሷል።
 3. በጋረ-ሙልአታ መሳሪያ-ኣልባ የሆኑ የኦሮሞ ልጆች ደም እንዲፈስስ ተደርጓል።
 4. በሻሸመኔ የኦሮሞ ልጆች ደም በወያኔ ጦር ሃይል እንዲፈስስ ተደርጓል።
 5. በኢሉአባቦራ በቤዴሌ በጌታቸው ኣሰፋ የተሰማሩ የወያኔ ደህንነት ሃይሎች ሰላማዊ ሰልፍ የወጡትን ሰልፋቸውን ለማወክና የጥያቄያቸውን ዓላማ ለማጥቆር የቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ እንቅስቃሴ እርምጃ የወሰደ ለማስመሰል በኦሮሞ፣ በኣማራና በሌሎችም ብሄር ተወላጆች ላይ በወሰዱት እርምጃ ህይወት ተቀጥፏል፣ ቤቶች ኣቃጥለው ንብረት ኣውድመዋል።
 6. ከቅርብ ቀናት በፊት ጥቅምት 25 ቀን 2017ዓም በጉደር ውስጥ በኦሮሞ ህዝብ ሃብት ላይ የተፈጸመውን ኣይን ያወጣ ዝርፊያ በሰላማዊ መንገድ ኣቁመው በጠየቁ የኦሮሞ ዜጎች ላይ የወያኔ ጦር ሃይል ተኩስ ከፍቶ የኦሮሞ ልጆችን ደም ኣፍስሷል።
 7. ጥቅምት 26 ቀን 2017ዓም በኣምቦ ከተማ በጠራራ ጸሃይ የሚዘረፈውን የሃገር ሃብት ለመከላከልና የመብት ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ ሲያቀርቡ በነበሩ የኦሮሞ ዜጎች ላይ ጦር በማወጅ በርካታ ዜጎችን በመግደል ደም ኣፍስሷል
 8. በምዕራብ ኦሮሚያ ዳሌ-ዋበራ በኦሮሞ ልጆች ላይ በተከፈተ ተኩስ የኦሮሞ ዜጎች ደም ፈስሷል።
 9. በሌሎች ኣካባቢዎችም እንዲሁ ኣያሌ ናቸው።

በሌሎች ኣካባቢዎች የኣንድ ሰው ህይወት ሲጠፋ ለመዘገብ የሚሽቀዳደሙት ቢቢሲ፣ ሲኤኤን እና የመሳሰሉት ታላላቅ ነጻ ሚዲያዎች ይህ ሁሉ ሲፈጸም ኣንዳችም ነገር ሳይዘግቡ ይህን በኦሮሞ ህዝብ ላይ የተፈጸመውን ዘግናኝ ድርጊት እንደመንግስታቸው ሁሉ ለወያኔ መንግስት ከመልካም ተግባር እንደቆጠሩለት ለማንም ግልጽ ነው። ስለዲሞክራሲና ሰላም የሚሰብኩ መንግስታት ሁሉም እንዲሁ። ኦ.ኤም.ኤን. ከነዚህ ጋር በመሆን ይህን ጉዳይ ከመዘገብ ዝምታን መምረጡ የኦሮሞ ልጆች ለምን? በሚል እየተጠያየቁ ያለ ትልቅ ጥያቄ ነው።

ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ይህን ዘግናኝ ድርጊት በመጋፈጥና በመታገል ይህን ሁኔታ ለመቀየር፡ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ለመፋለም የቆመ መሆኑና ለዚህም የዓመታት መስዋዕትነት ሲከፍል ዛሬን መድረሱ ለማንም ግልጽ ነው። በዚህም ለከባድ መስዋዕትነትና የወያኔ መንግስት በየጊዜው ለሚፈጽመው ዘግናኝ እርምጃ ሳይንበረከክ ኣይን ያወጣ ዝርፊያና ዘግናኝ ግድያ እንዲሁም የመብት ኣፈናን ለህዝባችን ሲያጋልጥና ሲታገለውም ዛሬን ደረሰ።

በኣለም ህግ የሚወገዝ ተግባር የሆነውን ባዶ እጆቹን በሆነ ህዝብና በወጣቶች ላይ ባለፈው ሳምንት ውስጥ የወያኔ ጦር ሃይልና ደህንነት የፈጸሙት ድርጊት ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ በጽኑ ያወግዛል። ሰላም ወዳድና ለሰብዓዊ መብቶች መከበር የሚቆም ህዝብ ሁሉ ይህን ተግባር እንዲያወግም ጥሪያችንን እናቀርባለን። ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ የኦሮሞ ህዝብ መብትና ባጠቃላይ የዲሞክራሲ መብት እስከሚከበር ድረስ ትግሉን በሁሉም መስክ ማፋፋሙን እንደሚቀጥልም በዚሁ ኣጋጣሚ እናረጋግጣለን።

የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በኣምቦ ባዶ እጆቻቸውን በሆኑ ህቻናት ላይ የወያኔ ጦር ሃይል የፈጸመውን ይህን ድግያ እንደድል ቆጥሮ በፌስቡክ ገጹ ላይ ማወጁን እናወግዛለን።

የደብረጽዮን ገብረሚካኤል ፌስቡክ

 

በኣምቦ የተሰዉ የኦሮሞ ልጆች በከፊል

 

 

ጥሪ ለመላው የኦሮሞ ዜጎች:

 

 1. ከጥቅምት 30 ቀን 2017ዓም ኣንስቶ ለኣንድ ሳምንት ከቤት ሳንወጣና ከመኖሪያ ቀዬኣችን ሳንርቅ በማንኛውም ስራ ላይ ሳንሰማራና በሰላም ቤት በመዋል፥

ሀ. በድንበር ላይ ላለቁት የኦሮሞ ልጆች ሁሉ ሃዘናችንን እንገልጻለን

ለ. በጉደር፣ ኣምቦ፣ ሰሜን ሸገር፣ ሻሸመኔ እንዲሁም በሌሎችም በርካታ የኦሮሚያ ቀበሌዎችና ከተሞች     ውስጥ በወያኔ ጦር ህይወታቸው ለተቀጠፉትና ደማቸው ለፈሰሰው የኦሮሞ ልጆች ሃዘናችንን እንገልጻለን

ሐ. በቤዴሌና ኣካባቢዋ እንዲሁም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ውስጥ በወያኔ ደህንነት ሃይሎችና ተላላኪዎች እየፈሰሰ ላለው የኦሮሞ ዜጎችና የሌሎችም ብሄሮች ተወላጆች ደም ሃዘናችንን እንገጻለን

መ. ለ26 ዓመታት የኦሮሞ ልጆችን ደም እያፈሰሰ ያለውን ስርዓት እንዲነሳለን እጅ ለእጅ ተያይዘን ያንን ቆራጥነትና ጥያቄያችንን ለዓለም ለመግለጽ

ሰ. ሁሉም እንዲሳተፍ ጥሪያችንን ኣጥብቀን እናስተላልፋለን።

 

 1. በሰላም ወጥተን መግባት፣ የወያኔ ጦርና ፌዴራል ፖሊስ ከኦሮሚያ ቀዬ ሁሉ ውስጥ እስከሚቀጣና ጥያቄያችንን በሰላማዊ መንገድ ለማቅረብ እስከምንችል ድረስ በተለያየ መልኩ የኦሮሞ ህዝብ ትግል በተለያየ መልኩ ሳይቋረጥ የሚቀጥል መሆኑን በዚሁ ኣጋጣሚ ኣጥብቀን እናሳውቃለን
 2. ምንም ያህል መስዋዕትነት ቢጠይቅ ህዝባችን በድንበሩ ላይ እራሱን መከላከሉንና ለችግሩ መድረሱን ኣጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያችንን ኣጥብቀን ጥሪያችንን እናቀርባለን።
 3. መላው የኦሮሞ ህዝብ ምንም ያህል መስዋዕትነት ቢጠይቅ ንብረቱን በተለያየ መልኩ ከመዘረፍ ካሁን በኋላ ለመከላከል የዜግነት ግዴታ ኣለበት
 4. በመሬታችንና በሃብታችን ላይ የምንከፍለው መስዋዕትነት የዛሬው ህይወታችንና ለነገው ልጆቻችንን መጻዒ ህይወት ወሳኝ መሆኑ ታውቆ ባዕዳን በመሬታችንና በንብረታችን ላይ የሚፈጽሙትን ዝርፊያ ለመከላከል በጥንካሬና በጽናት መሰራት ኣለበት

ባጠቃላይ ከኣንድ ሳምንት በኋላም መብታችንን ለማስከበርና ላለፉት 26 ዓመታት የታወጀብንን ዝሪፍያ ለመከላከል በተለያየ መልኩ እያካሄድን ያለነውን ፍልሚያ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድንቀጥል እናሳስባለን።

 

ድል ለኦሮሞ ህዝብ!

ዘመኑ የጭቆና ፍጻሜ ዘመን ነው!

ጥቅምት 27 ቀን 2017ዓም

ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s