እየተፋፋመ  ያለውን የጭቆና ፍጻሜ  ኣመጽ በተመለከተ ከቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ የተሰጠ መግለጫ

እየተፋፋመ  ያለውን የጭቆና ፍጻሜ  ኣመጽ በተመለከተ ከቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ የተሰጠ መግለጫ

ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ የኦሮሞ ህዝብ ያለበትን ኣጠቃላይ ሁኔታ፡ የወያኔ መንግስት ላለፉት 25 ዓመታት ሲገድሉንና ሲዘርፉን የነበሩትን በኢህኣዴግ ስር የመሰረታቸውን ተላላኪዎች ይዞ ከሁሉም የኦሮሚያ ድንበር ኣቅጣጫ በከፈተው ዘመቻ በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ዘግናኝ እልቂት፡ የተዘረፈውና የወደመው ንብረት፡ በተከፈተው ዘመቻ የተፈናቀሉትን ከ150,000 በላይ የሚሆኑ ወገኖቻችንን ከግምት በማስገባት፥ የኦሮሞ እስረኞች ፍትሓዊ ፍርድ ተነፍገው ለዓመታት በወህኒ ውስጥ መገደልና ለሰቆቃ መዳረግ በመቀጠሉ፥ ባጠቃላይ እነዚህና ሌሎችንም የኦሮሞ ህዝብ በሕወሃት/ኢህኣዴግ ኣስተዳደር ስር እያጋጠመው ያሉትን ኣስከፊ ሁኔታዎችን ለመቃወና ለህዝባችንና ለኣለም ለማሳወቅ እንዲሁም የመብት ጥያቄ ለማቅረብ ጥቅምት 11 ቀን 2017ዓም(ጥቅምት 1 ቀን 2010ዓም) ሰላማዊ ሰልፍ መጥራታችን ይታወሳል።

ይህ ሰላማዊ ሰልፍ ከተጠራበት ቀን(ጥቅምት 11, 2017ዓም) ኣንስቶ ከትላልቅ እስከ ትናንሽ የኦሮሚያ ከተሞች፡ በመላው ኦሮሚያ የሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ሳይቀር የኦሮሞ ህዝብ በነቂስ በኣንድነት ተነስቶ፡ ለጥሪው ምላሽ በመስጠት የሃገር ባለቤትነት መብት ጥያቄና የሉዓላዊነት ትግሉን ለመንግስትና ለዓለም በቀጣይነት ኣሰምቷል። ይህም በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይበጨቋኙ ስርዓት ላይ የተገኘ ከፍተኛ ድል መሆኑን ለሁሉም መግለጽ እንወዳለን። ለኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ትግል መስዋዕትነት በመክፈል ላይ ያላችሁትና ሰፊው ህዝባችን ይህን ከፍተኛ ድል በመጎናጸፋችን የተሰማንን ደስታ እንገልጻለን፣ ህዝባችን እየፈጸመ ባለው ጀግንነት ኩራት እንደሚሰማንም እንገልጻለን።

ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ በተገኘው በዚህ የላቀ ድልና ስኬት ውስጥ በኦፒዲኦ ውስጥ ያሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ብሄርተኞች ተሳትፎን በእጅጉ እንደሚያደንቅ እየገለጸ እንዲሁም የኦሮሚያ ፖሊሶች በበርካታ ኣካባቢዎች ላሳዩት ህዝባዊ ወገንተኝነት፡ ህዝባችንን ለመከላከልና በሰልፉ ላይ የሰልፊን ደህንነት ከማወክ በስፋት በመቆጠባቸው ያለንን ኣድናቆት እንገልጻለን። ያለን እጣ-ፈንታ ኣንድ መሆኑን በመገንዘብ እያካሄድን ላለው ለብሄራዊ የጭቆና ፍጻሜ ኣመጽ መቋጫ በማበጀት የሃገር ባለቤትነት መብታችንን ለመጎናጸፍ ኣብረን እንድንንቀሳቀስ ጥሪያችንን ለሁሉም እናድሳለን።

በዚህ መልኩ ሲካሄድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ የወያኔ መንግስት እንደልማዱ የጦር ሃይሉን በማዝመት ሻሸመኔ፥ ኢሉኣባቦራ፡ ሰሜን ሸገርና ምስራቅ ኦሮሚያን ጨምሮ በበርካታ የኦሮሚያ ኣካባቢዎች ሰላማዊ ሰልፍ ባካሄዱ ዜጎች ላይ የጥይት እሩምታ በማዝነብ የሰው ህይወት መቅጠፉን ኣጥብቀን እናወግዛለን። ይህንን ሰልፍ ለማወክም ነቀምቴ፡ ሻሸመኔ፡ ወሊሶ፡ ሰሜን ሸዋና በተለያዩ ኣካባቢዎች የደህንነት ሃይሎቹን ኣሰማርቶ ኣደጋ ለማስከተል ያደረገው ሙከራና ያስከተለውንም ኣደጋ ቄሮ ቢሊሱማ ያወግዛል። ቄሮ ቢሊሱማና ህዝባችን ለወደፊቱ የወያኔ የደህንነት ሃይል ለዓመታት የሚያደርሰውን ኣረመኔያዊ ሴራ በመመከት ለማክሸፍ በንቃት የሚሰራ መሆኑንም እናሳስባለን።

ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ የመብት ጥያቄ ለማቅረብ በሰላማዊ መንገድ በመላው ኦሮሚያ ውስጥ በስፋት ሲካሄድ የነበረው ሰልፍ ባገኘው ምቹ ሁኔታና ኣስፈላጊ በሁኔ ወቅት ይበልጥ ሰፍቶ እንደሚቀጥል መልዕክቱን እያስተላለፈ የመንግስት የታጠቁ ሃይሎች ባሉባቸው ኣካባቢዎች ከመጋፈጥ እንዲቆጠቡ እናሳስባለን።

ቄሮ ቢሊሱማ የኦሮሞን ህዝብ የሃገር ባለቤትነት መብትና ነጻነት እውን ለማድረግ ውድ መስዋዕትነት በመክፈል እያካሄደ ያለውን እንቅስቃሴ ኣሁንም ቀጣይነት ባለው መልኩ እንደሚያካሄድና ለዘራፊው የሕወሃት ቡድን ፍጻሜ ለማበጀት በጠንካራ ሃይል በቋሚነት እንድንንቀሳቀስ ጥሪውን ያስተላልፋል። ከዚሁ ጋር በቀጣይነት እየተካሄደ ባለው እንቅስቃሴ ውስጥ ህዝባችን የየትኛውም ሲቪል ህይወትና ንብረት  ጥበቃ እንዲያደርግ ኣበክረን እናሳስባለን።

በመጨረሻም ይህ ፋሽስት መንግስት በሰላማዊ መንገድ

  • ሁሉንም የኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞች ባስቸኳይ ኣንዲፈታ
  • ለዓመታት በህዝባችን ላይ ወንጀል ሲፈጽሙና ሲያፈጽሙ የነበሩትና ለፍርድ እንዲያቀርብ
  • ላለፉት ዓመታት ሁሉ በኛ ላይ ዘመቻ ያወጁትን የፌዴራል ጦርና ፖሊስ ሙሉ በሙሉ ከኦሮሚያ እንዲያነሳልን
  • በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያ፥ እስራትና ዝርፊያ እንዲሁም ማፈናቀል በኣስቸኳይ እንዲያቆም
  • በሰላማዊ መንገድ ላቀረብነው ኣጠቃላይ የመብት ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ምላሽ መነፈጋችንን እያሳሰብን

ህዝባችን ከኣሁን ጀምሮ ጨቋኙ መንግስት በዘረጋው መዋቅር የተተበተበብንን የባርነት ሰልሰለት በመበጣጠሱ ላይ ኣበክሮ እንዲሰራ ኣጥብቀን መልዕክታችንን እናስተላልፋለን። ስለዚህ በማንኛውም መልኩ ከመንግስት የሚሰጠውን ትዕዛዝ እንዳይቀበልና ስራ ላይም እዳያውል፡ ከመንግስት መዋቅር ጋር ያለውን ማንኛውንም ኣይነት ግንኙነት እንዲያቆም ኣጥብቀን መልዕክታችንን ያስተላልፋለን።

ዘመኑ የጭቆና ፍጻሜ ዘመን ነው!

ድል ለኦሮሞ ህዝብ!

ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ

ፊንፊኔ

ጥቅምት 20 ቀን 2017ዓም

 

1 thought on “እየተፋፋመ  ያለውን የጭቆና ፍጻሜ  ኣመጽ በተመለከተ ከቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ የተሰጠ መግለጫ

  1. Pingback: እየተፋፋመ  ያለውን የጭቆና ፍጻሜ  ኣመጽ በተመለከተ ከቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ የተሰጠ መግለጫ – OROMIYAANWANOFITIABBAATUUEGATAA

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s