ልነጋጋ ነዉና ንቃ!

  Qeerroo  መልዕክት ዐይኖቻችሁ ላልተገለጠ፦

  1. የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለሆናችሁ የኦሮሞ ልጆች፣
  2. የፖሊስ ሠራዊት አባላት ለሆናችሁ የኦሮሞ ልጆች እንዲሁም
  3. ለኦህዴድ ካቢኔዎች ና ለደህንነት አባላት በሙሉ

በዲሮ ዘመን አንድ ባለጠጋ ሰዉ  ዝንጀሮዎችን በግዛቱ ሥር አሰባስቦ ያስተዳድር  ነበር ይባላል። በመሆኑም በግዛቱ የዝንጀሮ ዐለቃ (the Monkeys Master) በሚል ቅጽል  ይታወቅ ነበር። ታዲያ ጥዋት ጥዋት ዝንጀሮዎቹን ይሰበስብና ከማዶ ወዲያ ባለዉ ተራራ ላይ ወተዉ ከየዛፎቹና ቁጥቋጦች  ላይ ፍራፍሬ ለቅመው እንዲያመጡ ያዛል። በትዕዛዙ መሠረት እያንዳንዱ ዝንጀሮ በዕለቱ ከሰበሰበዉ ፍራፍሬ ላይ ስሶዉን ለባለጠጋዉ ዐለቃ የመገበር ጽኑ ግዴታ አለበት። ይህንን ግዴታ የማይወጣ ካለ ከፍተኛ ቅጣት ይጠብቀዋል። ይህን ግዳጅ ተቆጣጥሮ የሚያስፈጽም ደግሞ አንዱን  ጎበዝ ከመሃላቸዉ መርጦ ይሾማል። እናማ ዝንጀሮዎቹ በሙሉ በዚህ ክፉ ስርዓት በእጅጉ ይማረራሉ።  ሆኖም ግን ዉስጥ ዉስጡን ከመጉረምረም ባለፋ ደፍሮ “በቃኝ!” የሚል ጎበዝ  አልተገኘም ነበር።

ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት ሚጢጢ ዝንጀሮ በነገሩ ተገርማ ኖሮ፦

“ይህን ሁሉ የፍራፍሬ ተክል እኚህ ሰዉዬ ብቻቸዉን   አልምቷል  እንዴ ?” ስትል ያልተጠበቀ  ጥያቄ ሰነዘረች።

“አረ በፊጹም! በተፈጥሮ የበቀለ ነዉ።” ስሉ ሌሎቹም  በአግራሞት መለሱ።

“ታዲያ ያለእሳቸዉ ፈቃድ ፍራፍሬዉን መብላት አይቻለንም ማለት ነዋ!” ትንሿ ዝንጀሮ አከለች።

“እንዴታ! በደንብ እንችላለን እንጂ።” ሌሎቹ አሁንም  በአግራሞት መለሱ።

“እንግዲያዉስ  የሰዉዬዉ ባሪያ ሆነን መቅረታችን ስለምንድ ነዉ!” ብላ ሀሳቧን ሳትቋጭ የሌሎቹ ዓይን ተገለጠ። ነቁም። ቁጣቸዉም ተቀሰቀሳ።  በዚያኑ ለልት ዐለቃቸዉን እንቅልፍ እስክ ወስዳቸዉ ጠብቀዉ  ለአመታት የታጠረባቸዉን ግድግዳ  ሰብረዉ ወጡ። ነጻነታቸዉን አወጁ። የተወሰዳባቸዉንም ምርኮ አስመለሱ። ከጥንት ጀምሮ ስበዘብዛቸዉ የነበረ ሰዉዬ በረሃብ ሞታ ይባላል። ይህ የጥንታዊ ቻይኖች ታዋቂ ምሳለያዊ ተረት (parable) ነዉ። ዓይናችሁ ሲገለጥ ብርሃንን ታያላችሁ። ክፉዎችንም ታወግዛላችሁ። ነጻነትንም ትሹታላችሁ። በትግላችሁም  ኣርናት ይሆንላችኋል። ልነጋጋ ነዉና ንቃ

1 thought on “           ልነጋጋ ነዉና ንቃ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s