ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኦሮሞ ተማሪዎች — ፊንፊኔ

ቀን  16 /04/ 2004  ዓ.ም

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አስተዳደር

ለክልሉ ፕሬዚዳን  ት ጽ/ቤት

ፊንፊኔ

                                                        ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኦሮሞ ተማሪዎች

                                                                          ፊንፊኔ

 

ጉዳዩ:   የሰብኣዊ መብት አያያዝና ሌሎች አስተዳደራዊና የባለቤትነት መብቶች ላይ ያሉትን ችግሮች

      በማንሳት አስቾካይ መልስ መጠየቅን ይመለከታል፡፡

እኛ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኦሮሞ ተማሪዎች በአሁኑ ጊዜ የኦሮሞ ህዝብ ያለበትና ለወደ ፊት ሁኔታውም አስፈሪ የሆኑ ዘርፈ-ብዙና ውስበስብ ችግሮችን ከግንዛቤ በማስገባት ከዚህ በታች ለዘረዘርናቸው የመብትና የባለቤትናት ጥያቄዎች አፋጣኝ መልስ እንድሰጠን እንጠይቃለን፡፡ እነዚህ የምናነሳቸው ጥያቄዎች የኦሮሞ ህዝብ በሀገሩ ሊኖራቸው የሚገቡ ተፈጥሮኣዊ  የባለቤትነት መብቶችና አስተዳደራዊ መብቶች ስለሆኑ ጥያቄዎቹና ለጥያቄዎቹም የሚሰጥ መልስ ለመላው የኦሮሞ ህዝብ መሆኑን እያስገነዘብን እነዚህን ለህዝባችን እንደ አንድ ህዝብ መኖር ወይም ላለመኖር ወሳኝ የሆኑ ጥያቄዎችን ስንጠይቅ አዎንታዊና ፍትሓዊ መልስ በመስጠጥ ታሪካዊ ግዴታን ይወጣሉ የሚል ተስፋ በማድረግ ነው፡፡

I. የኦሮሞ ህዝብ በፊንፊኔ ሊያገኘው የሚገቡ መብቶች/ልዩ ጥቅም/ እና ባለቤትነት በተመለከተ፡ 

1. ‹‹አዲስ አበባ›› የሚለው ስያሜ የኦሮሞን መሬት ባለቤትነትና ማንነት ለመደበቅ ታስቦ በወራሪው የሚኒልክ ገዢ መደብ የተሰየመ በመሆኑና ህዝባችን የባለቤትነት ስሜት እንዳይሰመው  ከፍተኛ ስነ-ልቦናዊ ጫና ስላለው ስያሜው ወደ መጀመሪያው ማለትም የኦሮሞ ህዝብ ቦታው/መሬቱ ካለው ተፈጠሮኣዊ ውበትና እሴት በመነሳት በቋንቋው ‹‹ፊንፊኔ›› ብለው በሰየመው ስም በሀገር አቀፍም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ እንድትጠራ  አበክረን እንጠይቃለን፡፡

2. አፋን ኦሮሞ አሁን ባለው የፊንፊኔ አስተዳደር ውስጥ ከአማርኛ ቋንቋ ጋር ጎን ለጎን የሥራ ቋንቋ መሆን አለበት፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ይቺ መሬት የኦሮሞ ህዝብ የተፈጥሮ ሀብት ናት፡፡ በህዝባችን ላይ ከተጫነው የባሪነት ስርኣት የተነሳ በተለያዩ ተፅኖዎች ህዝቡ ተገፍትሮ አሁን በከተማዋ ያለው ቁጥር አናሳ ብሆንም አሁንም ቢሆን ከአማራ ህዝብ ቀጥሎ በከተማዋ የህዝብ ብዛት ንፅፅር በሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም አሁን በከተማዋ ያለውን አብላጫ ቁጥር በማየት ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ ህዝብ በፊንፊኔ ላይ ያለውን ተፈጥሮኣዊ መብቶች ከግንዘቤ በማስገባት አፋን ኦሮሞ(የኦሮሚኛ ቋንቋ) የከተማዋ የሥራ ቋንቋ  እንድሆን ስንጠይቅ አስቾካይ መልስ በመሻት ነው፡፡

3. በህዝብ ምርጫ ሳይሆን የኦሮሞ ህዝብ በፊንፊኔ ላይ ባለው ተፈጥሮኣዊ የባለቤትነት መብት በፊንፊኔ ምክር ቤት መቀመጫ እንድኖራው እንጠይቃለን፡፡

4. የአንድን ህዝብ ባህልና ታሪክ ለአለም ለማሰወቅም ሆነ ለማወቅ ቤተ-መፅሓፍትና ሙዚየም የመረጃና ቅርጻ-ቅርጽ/እሴቶች ምንጭ በመሆን ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ፡፡ በተላይ እንደ ፊንፊኔ ባሉት የብዙ አለም አቀፍ ድርጅቶችና ኤምባሲዎች መቀመጫ በሆኑ ታላላቅ ከተሞች ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ እስካ አሁን የዚህ ዕድል ተጠቃሚ አይደለም! ለምን???

5. የኦሮሞ ህዝብ ለሰው ልጅ መልካም ሥራ ሠርተው ያለፉ ምሁራንና ለህዝቡ ነፃነት ስፋለሙ የወደቁ ብዙ  ጀግኖች አለው፡፡ ለነዚህ ምሁራንና ጀግኖች በፊንፊኔ አንዳችም ሃውልት አልቆመላቸውም፤  አንድም መንገድም በስማቸው አልተሰየመም፡፡ ለምን?

6. የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የኦሮሞን ህዝብ ባሕልና ታሪክ የሚያንጸባርቅ የራሱ የሆነ ቤተ መንግስት የለውም፡፡ ኣብዛኛው ቢሮዎችም ከፊንፊኔ አስተዳዳርና ከግለሰቦች የተከራያቸው ናቸው፡፡ ይህ ለምን ሆነ?

7. ከፊንፊኔ በየአመቱ ከተለያዩ ዘርፎች ከግብር እና ታክሲ እንድሁም ከሌሎች ገቢዎች የሚሰበሰበው በቢሊየን የሚቆጠር ብር ነው፡፡ ይህ ገቢ የፌዴራል መንግስትን ካዝና በማደለብ ለፖለቲካ  ፍጆታ ከመዋል ውጪ ለኦሮሚያና ለኦሮሞ ህዝብ ልማት አንዳችም አስተዋጽኦ አያበረከተ አይደለም፡፡ ይበልጥኑ የፌዴራል መንግስት  በከተማዋ ዙሪያ ያሉትን አርሶ አደሮች በእንቬስትመንት ስም ከይዞታቸው በማፈናቀል መሬቱን ለውጪ ባለሀብቶች እየቸበቸበ ተጨማሪ ገቢን ከኦሮሚያ ያግበሰብሳል፡፡

በመሆኑም ከከተማዋና አከባቢዋ ከሚሰበሰበወ  ገቢ የተወሰነው ወደ ኦሮሚያ በጀት ተዛውሮ ይህም በከተማዋ ለኦሮሞ ህዝብ ልሰሩ የሚገባቸውን የልማት ሥራዎች፡ ለምሳሌ የአፋን ኦሮሞ ት/ቤቶችና የኦሮሞ ህዝብ ባህልና ሥነ-ጥበብ ማዕከላት እንድሰሩበት እንጠይቃለን፡፡

 1.                                            II.            ሌሎች አጠቃላይ የሆኑ ጥያቄዎች:

1. በእንቬስትመንት ስም እየተካሄደ ያለውን የኦሮሚያ ከተሞች የመሬት ዝርፊያ/ወረራ፣ በተላይ በፊንፌኔ ዙሪያ ያለው አስከፊ ችግር ህዝቡን ከይዞታው ማፈናቀል በአስቾካይ እንድቆም ሆነው በዚህ ሁኔታ ለተፈናቀሉት ልዩ ካሳ እንድከፈላቸው፣ እንድሁም በዚህ ሁኔታ ከማሳቸውና ከቄዬአቸው ለተፈናቀሉት አርሶ አደሮች በሙሉ በአስቾካይ በቂ ካሳ ተከፍሎኣቸው ሌላ የመኖሪያ ቦታና መተዳደሪያ እንድመቻችላቸው በአጽዕኖት እንጠይቃለን፡፡

2. በፊንፊኔና ዙሪያዋ የሚገኙ ፋብርካዎች በአከባቢው አርሶ አደሮች ማሳና ወንዞች የሚለቁትን ከፋብርካ የሚወጡ አደገኛ ኬሚካሎችና ሌሎች አደገኛ ቁሶች በአፋጣኝ እንድያቆሙና እስካአሁን ላደረሱት ከፍተኛ ውድመት ህግ ፊት ቀርባው ለህዝቡ ተመጣጠኝ ካሳ እንድከፍሉ፤ይህንንም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እንድያስፈፅም እንጠይቃለን፡፡

3. የኦሮሞ ህዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ በአሁኑ ጊዜ በገፍ ወደ እስር ቤት እየታጎረ መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት ይህ ዘመቻ በአስቾካይ እንድቆምና ላለው የፖለቲካ ችግር መንግስት ከአሸባሪዎች ጋር ማያያዙን ትተው ከሁሉም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በሰላማዊ መንገድ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በመነጋገር ለመፍታት ራሱን እንድያዘጋጅና ይህንኑ በአስቾካይ እንድያስፈፅም እንጠይቃለን፡፡

4. በቅርቡ መሬትን በሊዝ ስር ለማስገባት/ለማስተዳደር የታወጀው አዋጅ ህዝቡን ያላማከረ/ሐሳብ ያልሰጠበት/ ስለ ሆነና የሀገሪቱ ዜጎች በመሬትና በተፈጥሮ ሀብቶች ላይ ያለቸውን የባለቤትነት መብት ሙሉ በሙሉ የሚጻረር በመሆኑ፤ ይህ ህግ ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት ለህዝብ ቀርበው ህዝቡ ተወያይተው ውሳኔ እንድሰጥበት እንጠይቃለን፡፡

5. ባለፈው ዓመት ‹‹የኦሮሞ ልማት ማህበር ‹ለኦሮሚያ ልማት›!!›› በሚል መፈክር ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ጀምሮ ነበር፡፡ ህዝቡም ‹‹እውነት ለልማት ከሆነ›› በሚል በእጁ ያለውን ማዋጣት ጀምሮ ነበር፡፡ የመንግስት ሠራተኞችም (የኦሮሚያ ክልል) ከደሞዛቸው ቆራረጠዋል፡፡ ዳሩ ግን ምን ያረጋል ይህ በዚህ ሁኔታ ተሟሟቀው እያለ ብዙም ሳይራመድ ድንገት በመሃል ‹‹ታላቁ የአባይ ግድብ›› መጣና የኦህዲድን የልማት ቅስቀሳ አቅጣጫ በቅፅበት አስቀየረው፡፡ይህ ለምን ሆነ?? ከዚሁ ጋር ተያይዘው ‹‹ለህዳሴው ግድብ አበርክቱ፤ ቦንድም ግዙ›› እየተባለ የህዝባችንን አቅም ያለገናዘበ የውዴታ ግዴታ መዋጮ ከደርግ ዘመን ‹‹ኮታ/ሰብል ገበያ›› ምን ልዩነት አለው??

6. ለኦሮሞ ህዝብ የነፃነት ትግል መሠረትና አባት የሆነው አንጋፋውን የመጫና ቱለማ ማህበር በዚህ መንግስት አሁንም በቅርቡ ለሁለተኛ ጊዜ እንድዘጋ መደረጉ ለምን??

7. የአፋን ኦሮሞ ዲፓርትመንትን ቀስ በቀስ ከአ/አ ዩኒቨርስቲው ለማውጣት እየተሰራ ያለው  ሴራ ማለትም “Afan Oromo literature and communication”  ስባል የነበረው “literature” የሚለውን በማስቀረት ከሌሎች ቋን   ቋዎች ጋር ተለጣፊ ለማድረግ የተወሰነው ውሳኔ ተነስተው ወደ መጀመሪያው ስያሜው እንድመለስ እንጠይቃለን፡፡

 1. 8.  በአሁኑ ጊዜ በኦሮሚያ ክልል ያሉት ሁሉም የመንግስት የልማት ፕሮጄክቶች (በገጠር የመጠጥ ወሃን ማስፋፋት፣ መንገድ፣ መብራት፣ጤና፣ የግብርና ፕሮጄክቶች፤ ወዘተ) ግልፅ ባልሆነ ምክንያት ሥራቸውን እንዲያቆሙ ተደርገዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የኦሮሚያ ክልል ሠራተኞች ሲቪል ሰርቪስ በየወሩ በሚሰጠቸው ስልጠናና በየሳምነቱ በመስሪያ ቤታቸው ‹‹አሸባሪነትና ሙስናን›› ዋናኛ አጀንዳ በማድረግ በሚዘጋጁ የተለያዩ ስብሰባና ግምገማዎች ተጠምደው ከሀገራዊ ልማትና የአስተዳደር ሥራዎች በሙሉ እንድርቁ ተደርገዋል፡፡ በመሆኑም ይህ አካሄድ/ሁኔታ የእድገትና የልማት ጉዞ በእጅጉ ስለሚጎዳ እነዚህ የልማት ፕሮጀክቶች በአስቾካይ ወደ ሥራ እንድመለሱ በአፅንኦት እንጠይቃለን፡፡
 2. 9.  በ‘COC’ (የብቃት መመዘኛ ፈተና) ምክንያት የኮሌጅና ዩኒቨርስቲ ተመራቂ የኦሮሞ ተማሪዎች የክልሉ መንግስት በየከተማ ያቋቋማቸው ፈተና ሰጪ አካላት የማይፈልጉትን ተመራቂ ‹‹ወድቀሃል/ሻል›› በማላት አድልዖያዊ ስራ ስለሚሰሩ እንድሁም ‘COC’  ያለው በኦሮሚያ ብቻ መሆኑ ተመራቂ የኦሮሞ ተመራቂዎች ስራ እንዳያገኙ ትልቅ መሰናክል በመሆን የብዙ ወጣቶችን ሞራል እየጎዳ ስለሆነ ይህ ማዕቀብ በአስቾካይ እንድነሳልን እንጠይቃለን፡፡

10. ባጠቃላይ በኦሮሚያ ለዘመናት ያለማቋረጥ እየተደረገ ያለው እስራት፣ግድያ፣ ከሥራ ገበታ መባራር፣ ከትምህርት ገበታ መባራር፣አና የተለያዩ ኢ-ሰብኣዊ ድርግቶች በአስቾካይ እንድቆም አበክረን እንጠይቃለን!!!

ከሠላምታ ጋር!

                                    ተወካዮች

                    ስም                             ፊርማ                   ካምፓስ                         Department

 1. ኢብራሂም ሁሴን     ______________                FBE                     Public Admn.   3rd yr.
 2. አዳኔ ጅሩ                _____________                    ኮቶቤ               Maths Education. 3rd yr.
 3. አብደታ ታደሳ             _____________                 6  ኪሎ                  Plotical Science 1st yr.

ግልባጭ

 • ለጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባዔ ጽ/ቤት
 • ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እንቨስትመንት ቢሮ
 • ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አከባቢ ጥበቃ ቢሮ
 • ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ
 • ለኦሮሚያ ከተማና ልማት ቢሮ
 • ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ኮሚንኬሽን ቢሮ
 • ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ቢሮ

ፊንፊኔ

 

 • ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ካንቲባ ጽ/ቤት
 • ለህዝብ ተወካዮች አፈ-ጉባኤ ጽ/ቤት
 • ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ጽ/ቤት

አዲስ አበባ

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s