የአዲስ አበባ አውደ አመት የገበያ ግርግር ተዳክሟል

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በኑሮ ውድነትና በብር የመግዛት አቅም መዳከም የተነሳ  ብዙዎች  ከበዓል ገበያው ይልቅ የዕለት ተዕለት ፍጆታቸውን መግዛት ላይ አተኩረዋል; በበዓል ጊዜ የሚታየው የ አውደ አመት የገበያ ግርግር ተዳክሟል።

ለወትሮው በኢትዮጵያ በፋሲካ በዓል አቅራቢያእና ዋዜማ የዶሮና እንቁላል፣ የበግና ፍየል፣ ለቅርጫ ሥጋ ክፍፍል የሚሆን የወይፈንእና በሬ፣ እንዲሁም የሽንኩርትና የዳቦ ዱቄት ግብይት ይደራ ነበር።

በዘንድሮው በዓል ግን በሸቀጦች ላይ የዋጋ ተመን ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ከገበያ የጠፉትን ዘይትና ስኳር በኮታ ለማግኘት በቀበሌ፣ በሸማቾች ማህበራትና በኢትፍሩት ኮንቴነር ሱቆች ላይ በጠራራ ፀሐይ ረጃጅም ሰልፎች ላይ ወረፋ ይዘው ሲጠብቁና ሲጨቃጨቁ ነው የሚታየው፡፡

ቀደም ሲል በሊትር 15 እና 16 ብር ሲሸጥ የነበረው የሀገር ውስጥ የኑግ ዘይት በአሁኑ ጊዜ ከገበያ የጠፋ ሲሆን በሊትር እስከ 45 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡ የዘይትን ዋጋ ለማረጋጋት ከውጭ የማስመጣቱን ተግባር ሙሉ ለሙሉ ከነጋዴዎች የነጠቀው የኢህአዴግ- መንግሥት የፓልም ዘይቶችን በማስመጣት በሊትር 24 ብር ከሃምሳ ሣንቲም በማከፋፈል ላይ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጂ ፓልም ዘይት በገበያ ውስጥ በሊትር እስከ 40 ብር  ለፋሲካ በዓል በጣም ተፈላጊ የሆነው  ሸኖ ለጋ ቂቤ በኪሎ በዓይነት ከ140 ብር እስከ 170 ብር ድረስ በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡ በአንፃሩ ሸኖ በሳል ቂቤ ደግሞ ከ120 ብር እስከ 150 ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል፡፡

Kormaa Indaanqoo

በመርካቶ ዶሮ ተራ የዶሮዎች ዋጋ ከ110 ጀምሮ የዋጋ ጥሪ የሚደረግበት ቢሆንም ከ80 ብር እስከ 100 ብር ድረስ በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡ በአንፃሩ የኤልፎራና መሰል የዶሮ እርባታ “ዲቃላ” ዶሮዎች ግን በ65 ብር፣ አንድ እንቁላልም በ1ብር ከ50 ሣንቲም እየተሸጠ ነው፡፡

በበግ ተራ አካባቢ አነስተኛ የተባለ ጠቦት  እንደ ውፍረቱ እና የትውልድ ቦታው ከ700 ብር እስከ 900 ብር ድረስ ሲሸጥ፣ መካከለኛ በግ 1350 ብር ድረስ ይገኛል፤ ሙክት  የፈለገ ሰው ግን ከ2000 ሺህ ብር በላይ በኪሱ መያዝ ይጠበቅበታል፡፡

ዘረኛው የትግራይ ገዢ ጉጂሌ ባለስልጣናት፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኦነግ አባል ናቺሁ በማለት በፓርላማ ምክር ቤት ለረጂም ጊዜ ሲሳተፉ የነበሩ የመድረክ አባላትን፣ ህዝባዊ አመጽ ለማነሳሳት ትቀሰቅሳላቺሁ በማለት በርካታ የሆኑ ወጣቶችን ፣ እንዲሁም የተለያዩና ፍጹም ከባለጉዳዩቹ ጋር ተያያዥነት የሌላቸውን ውንጀላዎች በመፈብረክ በርካታ ዜጎችን ወደ እስር ቤት እየወረወሩ እንደሆነ በስፋት ሲዘገብ መቆየቱ አይዘነጋም፣ ፣

ከዚህም በተጨማሪ የዘረኛውና አምባገነኑ አገዛዝ ቁንጮ የአንድነት ፓርቲ አባላትን ህዝባዊ አመጽ እንዲነሳ እየሰሩ ለመሆኑ መረጃዎች አሉን እናም ርምጃ እንወስድባቺሁአለን በማለት በምክር ቤት ተብየ ስብሰባ ላይ መዛቱ አይዘነጋም።

በአፈና፣ በጭቆና፣ በነጻነት ዕጦት፣ በሙስና የተዘፈቀ አሠራር፣ ሥራ አጥነት እና የጥቂቶች ተጠቃሚነት የአብዛኛዎቹ በአምባገነን የሚመሩ አገራት መገለጫዎች ናቸው።

1 thought on “የአዲስ አበባ አውደ አመት የገበያ ግርግር ተዳክሟል

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s